ፈልግ

በካቶሊክ ትምህርት ላይ የተካሄደ የማድሪዱ ጉባኤ በካቶሊክ ትምህርት ላይ የተካሄደ የማድሪዱ ጉባኤ 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፥ “ትምህርት የተሻለ ማኅበረሰብን ለመገንባት የሚያስችል የተስፋ ተግባር ነው"

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በስፔን መዲና ማድሪድ በተካሄደው ጉባኤ ላይ ቤተ ክርስቲያን በስፔን ውስጥ ያላትን ቁርጠኝነት በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት፥ ካቶሊክ ተቋማት ትምህርትን ለሁሉ ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ አመላክተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለጉባኤው ተካፋዮች ባስተላለፉት መልዕክት፥ ቤተ ክርስቲያ ሁሉን አቀፍ ትምህርት እንድታበረታታ የተጠራች መሆኗን ለካቶሊክ መምህራን አሳስበው፥ ሁሉም ተማሪዎች የአስተዳደግ ሁኔታቸው ምን ይሁን ምን አቅማቸውን እንዲያሳዩ ዘወትር ማገዝ የትምህርት ተልዕኮ ወሳኝ አካል መሆኑን አስታውሰዋል።

ቅዱስነታቸው የስፔን ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ቤተ ክርስቲያን በትምህርት ላይ ያላትን ቁርጠኝነት በማስመልከት በማድሪድ ከተማ ባዘጋጁት ጉባኤ ላይ ለተገኙት አባላት ቅዳሜ የካቲት 16/2016 ዓ. ም. ባስተላለፉት መልዕክት፥ "ትምህርትን ማዳረስ ከሁሉም በላይ ለአዳጊ ወጣቶች የሚውል የተስፋ ተግባር እንደሆነ አስረድተዋል።

ጉባኤው ጥቅምት ወር 2016 ዓ. ም. የተጀመረውን የአራት ወራት ሂደት ያጠቃለለ ሲሆን፥ በዚህም ከመላው ስፔን የመጡ ብጹዓን ጳጳሳት፣ ምሁራን እና የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች መምህራን ተገኝተው፥ በስፔን የምትገኝ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በትምህርት ዘርፍ ያከናወናቸውን ተግባራት የገመገሙበት እንደ ነበር ተነግሯል።

ማንኛውም ሰው የመማር መብት አለው!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለጉባኤው ተካፋዮች ባስተላለፉት መልዕክት፥ ጅምራቸውን በደስታ ተቀብለው የካቶሊክ ተቋማት ትምህርት ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ አመላክተው፥ “ማንም ሰው ሳይገለል ሁሉም የመማር መብት አለው” ሲሉ ተናግረዋል።

በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የትምህርት ዕድል የሌላቸው፣ ጭቆና የሚደርስባቸው አልፎ ተርፎም በጦርነት እና በዓመፅ ውስጥ የሚገኙ ብዙ ሕጻናት እና ወጣቶች መኖራቸውንም በማስታወስ፥ የጉባኤው ተሳታፊዎች በዘመናዊው የንቅት ባሕል ምክንያት የተፈጠረውን አዲሱን የማግለል ባሕልን ችላ እንዲሉ ቅዱስነታቸው አደራ ብለዋል።

አክለውም፥ በሕዝቦች መካከል ፍትሃዊ ግንኙነቶችን መፈጠር፣ የተቸገሩትን እና አቅመ ደካሞችን መርዳት እንዲሁም የጋራ መኖሪያ መድራችንን መንከባከም የሚቻለው በእነዚያ ዛሬ በተማሩት ሰዎች ልብ፣ አእምሮ እና እጆች አማካይነት መሆኑን በጭራሽ መዘንጋት የለብንም” ብለዋል።

የካቶሊክ ትምህርት ልዩ ባህሪ እውነተኛ ሰብዓዊነት ነው!

በሁሉም አካባቢዎች የሚገኝ የካቶሊክ ትምህርት ልዩ ባህሪ፥ ከእምነት የሚመነጭ እና ባሕልን የሚያሳድግ እውነተኛ ሰብዓዊነት መሆኑን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በማስታወስ፥ የስፔን ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በትምህርት ላይ ያላትን ቁርጠኝነት በማስታወስ፥ ቤተ ክርስቲያን በአገሪቱ ውስጥ ልዩ ባሕላዊ ማንነትን ለመገንባት ትልቅ አስተዋፅዖ ማበርከቷንም ገልጸው፥ እንዲሁም መላዋ ቤተ ክርስቲያንን እንደሚያበለጽጋት ተናግረዋል።

የካቶሊክ ትምህርት ለግኑኝነት ባሕል መንገድ መክፈት አለበት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መልዕክታቸውን ሲያጠቃልሉ፥ የጉባኤው ተሳታፊዎች በኅብረት መጓዝን እና አብረው ማሰላሰልን እንዲቀጥሉ አሳስበው፥ ማንነታቸውን እና እምነታቸውን ከፍ አድርገው እንዲመለከቱ፣ ራስን ከማሞገስ እንዲርቁ እና ም የሰላም መሣሪያዎች እንዲሆኑ አበረታተዋል።

“ለነጻነት፣  ለማኅበራዊ ወዳጅነት እና ለግንኙነት ባሕል መንገድ ካልተከፈተ ትምህርትን ማዳረስ አይቻልም" ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረው፥ ትምህርት ዘወትር ትብብርን እና ትስስርን የሚፈልግ የጋራ ተግባር እንደሆነ ገልጸው፥ ከብቸንነት እና ራስን ከማሞገስ እንዲቆጠቡ አደራ ብለዋል።

28 February 2024, 16:31