ፈልግ

ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች ማሕበር ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች ማሕበር ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት   (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ በቫቲካን እውቅና ለተሰጣቸው ጋዜጠኞች፡ ‘የሰው ልጅን ውደዱ፣ ትሕትናን ተማሩ’ ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቫቲካን እውቅና ከተሰጣቸው ጋዜጠኞች ጋር ተገናኝተው “የመንፈስን ረቂቅነት” ከጋዜጠኝነት ችሎታ ጋር በማጣመር ስለ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና ቅድስት መንበር የተመለከቱ ዜናዎችን በብቃት እንዲያስተላልፉ አሳስበዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

"በጴጥሮስ ዙሪያ ያደረጋችሁት ስራ ውበት በጠንካራ የኃላፊነት አለት ላይ የተመሰረተ ነው እንጂ በሃሜት እና በርዕዮተ ዓለም ትርጓሜዎች ደካማ አሸዋ ላይ አይደለም" ያሉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ያንን ማሳሰቢያ ለቫቲካን እውቅና ለተሰጣቸው 150 ጋዜጠኞች አቅርበዋል፣ ብዙ ጊዜ በውስጥ አዋቂው “ቫቲካኒስቲ” በመባል ለሚጠሩ ጋዜጠኞች ነበር ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን ያስተላለፉት።

በቫቲካን እውቅና ከተሰጠው ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች ማህበር አባላት ጋር ሰኞ ማለዳ ጥር 13/2016 ዓ.ም ላይ ተገናኝተዋል።

ለተልእኮ ለዕለታዊ ቁርጠኝነት ምስጋና

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱም በንግግራቸው ቀደም ብለው እንዲነሱ ስላደረጋቸው በቀልድ ይቅርታ ጠይቀው ወደ ቫቲካን እንኳን ደህና መጣችሁ የ"እዚህ ቤት አባል ብትሆኑም!" ሲሉ ተናግረዋል።

ብዙ የማኅበሩ አባላት ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በሐዋርያዊ ጉዟቸው ብዙ ጊዜ ይጓዛሉ፣ እና እያንዳንዱን እንቅስቃሴያቸውን በመሸፈን ብዙ የነቃ ሕይወታቸውን ያሳልፋሉ።

ከጣሊያን፣ ከአውሮፓ፣ ከሜዲትራኒያን እና ከትውልድ አገራቸው ከሚወጡ ዜናዎች ጎን ለጎን የቫቲካን ዜና ሽፋን በመስጠት፣ “ጥረታችሁን፣ ለምትዘግቡት ዜና ያላችሁን ፍቅር እና እንዲሁም የሚያጋጥማችሁን ተግዳሮት አውቃለሁ” ብሏል።

“ስለ እኔ በተለያዩ መንገዶች የሚነገሩ ዜናዎች ለመዘገብ በምትንቀሳቀሱበት ወቅት ጊዜያችሁን ከቤተሰባችሁ፣ ከልጆቻችሁ ጋር እንዳትጫወቱ እንዲሁም ከባሎቻችሁ ወይም ከሚስቶቻችሁ ጋር እንዳታሳልፉ ስላደረጋችሁ ይቅርታ መጠየቅ አለብኝ” ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋዜጠኛ መሆን እንደ ዶክተር ዓይነት “ሕመሞችን በመንከባከብ የሰውን ልጅ መውደድን የሚመርጥ ሥራ ነው” ብለዋል።

"በአንድ መንገድ አንድ ጋዜጠኛ የህብረተሰቡን እና የአለምን ቁስል በግል ለመንካት በመምረጥ የሚያደረግ ነው" ብሏል። "ከወጣትነት ጊዜ ጀምሮ ወደ መግባባት፣ ብርሃን የፈነጠቀ እና ወደ መተረክ የሚመራ ጥሪ ነው" ሰብአዊነትን መውደድ፣ ትህትናን መማር ያስፈላጋል ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በጋዜጠኛ ማንነት ላይ በማሰላሰል የ80 ዓመቱ የቫቲካን ጋዜጠኛ አቶ ሉዊጂ አካቶሊ የተናገሩትን ጠቅሰዋል።

“በብዙ ዓመታት የቫቲካን የጋዜጠኝነት ሥራዬ፣ የሰውን ልጅ የመውደድ መንገድ የሆነውን የሕይወት ታሪኮችን የመፈለግ እና የመተረክ ጥበብን ተምሬያለሁ” ሲሉ ጽፈዋል። ትህትናን ተምሬአለሁ። እንዳምን እና ሰው እንድሆን የረዱኝን ብዙ የእግዚአብሔር ሰዎች አጋጥመውኛል ማለታቸውን ቅዱስነታቸው ጠቅሰዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አቶ አካቶሊ እንደ ቫቲካኒስት ስለ ህይወታቸው ማጠቃለያ ላይ “ችግር ቢኖርም ይህ በጣም ጥሩ ማበረታቻ ነው፡ የሰውን ልጅ ውደዱ። ትሕትናን ተማሩ” ማለታቸውን ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

የመንፈስ ስውርነት፣ የጋዜጠኝነት ችሎታ

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱም ከቀድሞው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ጳውሎስ ስድስተኛ ከተመረጡ በኋላ እና ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ከመቀጠሉ በፊት ለጋዜጠኞች የሰጡትን ማሳሰቢያ አስታውሰዋል።

ቫቲካንንና ቤተ ክርስቲያንን የሚዘግቡ የጋዜጠኞች ሥራ በዓለማዊና በፖለቲካዊ ምድቦች መመራት የለበትም ብለዋል።

ከዚህ ይልቅ አገልግሎታቸው “የቤተ ክርስቲያንን ሕይወት በትክክል የሚያስታውቀውን ይኸውም ሃይማኖታዊና ሥነ ምግባራዊ ዓላማዋንና ልዩ የሆኑ መንፈሳዊ ባሕርያትን ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል” ሲል አክለው ተናግረዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ቫቲካንን ከመታየት አልፈው ለማየት በመፈለግ እና ስለ ቫቲካን ዜናን ወደ ተራ ትርኢት ለመለወጥ ወይም በፖለቲካ ሽፋን ውስጥ ያለውን ሀሳብ ለማራመድ መንትያ ወጥመዶችን በማስወገዳቸው ጋዜጠኞችን አመስግነዋል።

አሉባልታ ወሬዎችን በአክብሮት መያዝ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ካዘጋጁት ፅሑፍ በመነሳት ለተጎጂዎች ክብርና ስለ ‹ዝምታ› እጅግ አሳፋሪ ዝርዝሮችን በመጥቀስ “ስለ ቤተ ክርስቲያን ያልተገቡ ተግባራት ስትናገሩ ለምያሳዩት ጥንቃቄ” የቫቲካን ጋዜጠኞችን አመስግነዋል።

ስለ ቫቲካን የሚዘግቡ የጋዜጠኞች ሥራ፣ የቫቲካን ዝግጅቶችን “ቃላትን ከመጥቀም በፊት እንኳ በምስክርነት ለማስተላለፍ “የመንፈስን ረቂቅነት” ከጋዜጠኝነት ችሎታ ጋር ማቀናጀትን ይጠይቃል ብለዋል።

ተግባራቸው “እውነታውን እና ችግሮቹን አለመደበቅ፣ ውጥረቶችን አለመሸፈን ሳይሆን በተመሳሳይ ጊዜ አላስፈላጊ ጫጫታ አለመፍጠር፣ ይልቁንም ከቤተክርስቲያን ባህሪ አንጻር አስፈላጊ የሆነውን ነገር ለመያዝ መጣር ነው” ሲል ንግግራቸውን ደምድመዋል።

22 January 2024, 11:34