ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የመጽሐፍ ቅዱስ የምርምር ሥራ ተባባሪዎን በቫቲካን ሲቀበሉ ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የመጽሐፍ ቅዱስ የምርምር ሥራ ተባባሪዎን በቫቲካን ሲቀበሉ   (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የመጽሐፍ ቅዱስ የምርምር ሥራ ከምን ጊዜውም በላይ የከበረ መሆኑን ገለጹ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ፍራንችስካዊ የመጽሐፍ ቅዱስ የምርምር ሥራ ተባባሪ አባላትን ጥር 6/2016 ዓ. ም. በቫቲካን ተቀብለው ሰላምታ አቅርበውላቸዋል። ቅዱስነታቸው በተጨማሪም የመጽሐፍ ቅዱስ የምርምር ሥራ ተባባሪዎች ማኅበሩ ከተመሠረቱ ከመቶ ዓመታት ወዲህ ቅዱሳት መጻሕፍትን ከአርኪዮሎጂ ጥናት ጋር በማዋሃድ የሚያካሂዱትን ጥልቅ ሥራ አወድሰዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፥ የመጽሐፍ ቅዱስ የምርምር ሥራ ተባባሪ አባላትን ሰኞ ጥር 6/2016 ዓ. ም. በቫቲካን ተቀብለው ባስሙት ንግግር፥ ማኅበሩ ከተመሠረተ ከአንድ መቶ ዓመታት ወዲህ ያካሂድ የነበረውን አንዳንድ ገፅታዎች አስታውሰዋል።

ቅዱሳት መጻሕፍት እና የአርኪኦሎጂ ጥናት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የማኅበሩ የመጀመሪያው ተግባር፥ ቤተ-መጽሐፍትን እና ሙዚየሞችን በማስተባበር በተለያዩ ቅዱሳት ሥፍራዎች የአርኪኦሎጂ ቁፋሮዎችን በማካሄድ ጠቃሚ የሆኑ ግኝቶችን ማቅረብ መቀጠሉን አስታውሰዋል።

ቅዱስነታቸው አባላቱ ለመጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች ያላቸውን ፍቅር ገልጸው፥ በቅዱስ ፍራንችስኮስ ተመሳሳይ ፈቃድ ላይ የተመሠረተ ነው በማለት ተናግረዋል። ለቅዱስ ፍራንቸስኮስ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ማወቅ እና ጥናት ማድረግ እንዲሁ ተራ ዕውቀት ሳይሆን፣ መንፈሳዊ ተሞክሮዎች እንደሆነ፥ ዓላማውም በእምነት ሰዎች ወንጌልን በተሻለ ሁኔታ እንዲኖሩ ለመርዳት እንደሆነም አስረድተዋል።

የቅዱሳት መጻሕፍት አቀራረብ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የቅዱስ ቦናቬንቱራ መንፈሳዊ ትምህርቶችን በማስታወስ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስጦታ ለመቀበል በቀላል እምነት ወደ እግዚአብሔር አብ ብርሃን  መቅረብ እና በትሕትና ልብ መጸለይ እንደሚያስፈልግ መጻፉን አጽንኦት ሰጥተዋል። ቅዱስ ቦናቬንቱራ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ የኢየሱስ ክርስቶስን እውነተኛ እውቀት እና ፍቅር እንዲሰጠን በማለት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመጽሐፍ ቅዱስ የምርምር ሥራ መቶኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ያሰሙት ንግግር በመቀጠል፥ አባላቱ እንዲህ ዓይነቱን የቅዱሳት መጻሕፍት አቀራረብ ሳይዘነጉ እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በንግግራቸው ማጠቃለያ ላይ፥ በአዳራሹ የተገኙት በሙሉ የእግዚአብሔርን ቃል እንዲያዳምጡ እና እንዲያውቁ ጋብዘው፥ ቃሉም በዓለም ላይ ይበልጥ ለመረዳት በሚያስችል ሁኔታ እንዲያሰማ በማሳሰብ፥ አስተዋይ እና ጥልቅ ስሜት ያለው ሥራቸው ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ውድ እንደሆነ ተናግረዋል።

ቅድስት አገርን በጸሎት ማስታወስ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመጨረሻም የቅዱሳት መጻሕፍት የምርምር ሥራ የሚገኝባትን ቅድስት አገር በጸሎታቸው አስታውሰው፥ አሁን ያለው የቅድስት ሀገር ሁኔታ እና በውስጧ የሚኖሩ ሕዝቦች ጉዳይ ያሳትፈናል፣ ያመናልም” ብለው፥  “ይህ አደጋ እንዲያበቃ ልንጸልይ እና ሳንታክት እርምጃ መውሰድ አለብን” ብለዋል።

 

16 January 2024, 16:05