ፈልግ

2024.01.10 Delegazione del Gruppo DIALOP

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ማርክሲስቶች እና ክርስቲያኖች ሙስናን እንዲዋጉ፣ የሕግ የበላይነትን እንዲያስከብሩ ያበረታታሉ!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሶሻሊስቶችን እና ክርስቲያኖችን ለጋራ ሥነ ምግባር እንዲሰሩ የሚጋብዝ እና ዋልታ ረገጥ የሆነው ዓለማችን ውስጥ የተሻለ የወደፊት ሁኔታን እንዲገነቡ በተመለከተ የዲያሎፕ የሽግግር ውይይት ፕሮጀክት (Dialop Transversal dialogue project) ተወካዮችን አነጋግረዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ድሆች፣ ሥራ አጥ፣ ቤት አልባ፣ ስድተኞች ወይም የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባዎች፣ እንዲሁም ባለፉት ዓመታት በነበሩት አምባገነኖች የተገደሉት እና አሁን ባለው “ተጠቅሞ የመጣል ባህል” እንደ ቆሻሻ ለተቆጠሩ ሰዎች፣ እነዚህን እና እነዚህን በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ በዝርዝር ንግግር ያደረጉት ቅዱስነታቸው የህብረተሰቡ የስልጣኔ ደረጃ የሚለካው ባለበት ሁኔታ ነው፣ አሁን ያለው እውነታ ግን ይህንን አያሳይም፣ ሁኔታው መታከም አለበት ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ተናግረዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በፖለቲካ እና በህብረተሰቡ ውስጥ ያሉትን የሶስትዮሽ "መቅሰፍት" ብለው የጠሯቸውን የሙስና፣ ስልጣንን አላግባብ መጠቀም እና ህገ-ወጥነትን ለመመከት አስፈላጊ መሆኑን ረቡዕ እለት ጥር 01/2016 ዓ.ም ከዲያሎፕ የሽግግር ውይይት ፕሮጀክት ተወካዮች ጋር ባደረጉት ንግግር የተጎጂዎችን ማዕከላዊነት በመጥቀስ እንክብካቤ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ገልጸዋል።

ይህ በሶሻሊስቶች/ማርክሲስቶች፣ በኮሚኒስቶች እና በክርስቲያኖች መካከል የሚደረግ የውይይት ፕሮጄክት ሲሆን ይህም በቤተክርስቲያን ማህበራዊ አስተምህሮ እና በማህበራዊ አስተምህሮ መካከል ወሳኝ ስነ-ምህዳር ያለው ለአውሮፓ ማንነቱን ለመፈለግ እንደ አዲስ ትረካ ሊቀርብ የሚችል የጋራ ማህበራዊ ስነምግባር ለመቅረጽ ያለመ ነው። የማርክሲስት ማህበራዊ ትችት የመሰረቱ ዋንኛ ክፍል ነው።

እ.ኤ.አ. በ2014 የተወለደው ይህ ፕሮጄክት በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እና በወቅቱ የሲሪዛ ፓርቲ ፕሬዝዳንት እና በኋላም የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር እ.አ.አ ከ2015 በኋላ አሌክሲስ ሲፕራስ ፣ የአውሮፓ ግራኝ ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዋልተር ባይየር እና የፎኮላር ንቅናቄ ፍራንዝ ክሮንሬፍ ከተገናኙ በኋላ ነበር ።

"ሕልም ማለማችሁን አታቋርጡ"

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ረቡዕ ጥር 01/2016 ዓ.ም ከእዚህ ፕሮጄክት አንቀሳቃሽ 15 አባላት ጋር የተገናኙ ሲሆን 7 አባላት የግራ ዘመም ፖሌቲካ ደጋፊዎች ሲሆኑ የተቀሩት 8 ደግሞ  ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የተውጣጡ ካቶሊኮች እንደ ነበሩም ተገልጿል።  

ዛሬ "በጦርነት እና በዋልታ ረገጥነት ተከፋፍላ" ለምተገኘው ዓለም የተሰማቸውን ሐዘን አካፍሏል በሌላ በኩል ደግሞ የወደፊቱን ለማየት እና "የተሻለ ዓለም" ለመገንባት እንዲሞክር ማበረታቻቸውን ሰጥተዋል።

"እኛ አርጀንቲናውያን አትሸማቀቁ፣ ወደ ኋላ አትሂዱ እንላለን። እናም ይህ ለእናንተም ያቀረብኩላችሁ ግብዣ ነው፤ ወደ ኋላ አትበሉ፣ ተስፋ አትቁረጡ፣ የተሻለ ዓለምን ማለማችሁን አታቁሙ" ሲሉ ቅዱስነታቸው የማበረታቻ ንግግራቸውን አድርገዋል።

ነፃነት፣ እኩልነት፣ ክብር፣ ወንድማማችነት

“በእውነቱ፣ ብልህነት፣ አእምሮ፣ ልምድ እና ታሪካዊ ትውስታ የሚገናኙት በምናብ ውስጥ ነው፣ ለመፍጠር፣ ለመሰማራት እና ለአደጋ ያጋልጣል” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አሳስበዋል።

ባለፉት መቶ ዘመናት "የነፃነት እና የእኩልነት ፣የክብር እና የወንድማማችነት ፣የእግዚአብሔር ህልም ነፀብራቅ ፣እድገት እና ብልጽግና ያመጡት ታላላቅ ህልሞች ነበሩ" ሲሉ አስታውሰዋል።

ከዚህ አንፃር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ DIALOP ቁርጠኝነቱን እንዲፈጽም ሦስት አመለካከቶችን ጠቁመዋል፡- የሻገተ አስተሳሰብን ለመስበር ድፍረትን፣ ለደካሞች ትኩረት መስጠት እና በሕግ የበላይነት ላይ የተመሰረተ ባህልን ማስተዋወቅ እንደምያስፈልግ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።

የነገሮችን አዝማምያ ማዞር

ቅዱስነታቸው አክለው እንደተናገሩት ከሆነ ሻጋታውን ለመስበር ድፍረት ማግኘት ማለት "በንግግር፣ አዲስ መንገዶች መክፈት" ማለት ነው፣"በተለያዩ እርከኖች ግጭቶችና አለመግባባቶች በታዩበት ዘመን፣ አሁንም መንገዱን ለመቀልበስ ምን መደረግ እንዳለበት መዘንጋት የለብንም" ብለዋል።

"የሚከፋፍሉን ግትር አካሄዶችን በመቃወም ማንንም ስናገል በፖለቲካዊ፣ በማህበራዊ እና በሃይማኖት ደረጃ፣የእያንዳንዱ ሰው አስተዋፅዖ በአዎንታዊ መልኩ እንዲታይ፣ የመነጋገርና መደማመጥን ችሎታችንን እናዳብር። የወደፊት ህይወታችን በተሰጠበት የለውጥ ሂደቶች ተቀባይነትን አግኝተናል” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አሳስበዋል።

የፋይናንስ እና የገበያ ዘዴዎች ትችት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል ለደካሞች የማያቋርጥ ትኩረት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፣ ምክንያቱም የሥልጣኔ መለኪያው በኅብረተሰቡ ዳር ላይ ያሉትን እንዴት እንደምንይዝ ማወቅ ነው ያሉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በወቅቱ ቅዱስነታቸው በሰጡት አስተያየት የቅርብ ጊዜ ያለፈውን ታሪክ አስታውሰዋል። "ታላላቅ አምባገነን መንግስታት - የናዚን አስተሳሰብ ያስታውሱ - አቅመ ደካሞችን ይጥሉ እና ይገድሉ እንደነበር መዘንጋት የለብንም" ብለዋል።

ህብረተሰቡ "በፋይናንስ እና በገበያ ዘዴዎች እንዲመራ መፍቀድ አይገባም" ሲሉ የዓለም መሪዎች "በእውነት ለሰው ልጅ አገልግሎት የሚሰጡ ፖሊሲዎችን እንዲያወጡ አሳስበዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "አንድነት ከሥነ ምግባራዊ ምግባሩ በተጨማሪ የተዛቡ ነገሮችን ማስተካከል እና ፍትሃዊ ያልሆኑ ስርዓቶችን ዓላማዎች ማፅዳትን እንዲሁም በሰዎች እና በሕዝቦች መካከል ተግዳሮቶችን እና ሀብቶችን በማካፈል ረገድ ሥር ነቀል የአመለካከት ለውጦችን የሚጠይቅ የፍትህ መስፈርት ነው" በማለት ተናግሯል።

እናም ለዚህ ዘርፍ ራሳቸውን የወሰኑትን “ማህበራዊ ገጣሚዎች” በማለት ገልጿቸዋል፣ ምክንያቱም “ግጥም ፈጠራ ነው” እና እዚህ ላይ “ፈጠራን በህብረተሰቡ አገልግሎት ላይ ማዋል፣ የበለጠ ሰው እና ወንድማማችነት እንዲኖረው” የሚለው ጥያቄ ነው።

ሙስናን እና ህገወጥነትን መዋጋት

በመጨረሻም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሕግ የበላይነት ላይ የተመሰረተ ባህልን አበረታተዋል።

"ሙስናን፣ ስልጣንን አላግባብ መጠቀም እና ህገወጥነትን መዋጋት" ያስፈልጋል ያሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም "በታማኝነት፣ በተግባር ብቻ ጤናማ ግንኙነት መፍጠር የሚቻለው እና የተሻለ የወደፊት ግንባታ ላይ እምነት እና ቅልጥፍና ልንተገብር እንችላለን" ብለዋል።

ስለዚህም “ፍትሃዊና ሰላም የሰፈነበት ዓለም እንዲኖር” እና “የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሁል ጊዜ ጥናቶቻችሁን እና ድርጊቶቻችሁን እንዲያበረታታ እና እንዲያበራላችሁ እመኛለሁ” ለሚለው ምክር “ድፍረት” ምስጋናቸውን ገልጿል።

በወቅቱ በተደርገው ስብሰባ ላይ የዲያሎፕ ቡድን ለካቶሊክ ባህል እና ትምህርት ጽሕፈት ቤት ድጋፍ በማድረግ ባለፉት አስር ዓመታት ያከናወናቸውን ተግባራት ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቅርበዋል ።

“ከሃይማኖት እና ከርዕዮተ ዓለም ድንበሮች ባሻገር ክርስቲያኖች እና ማርክሲስቶች እንዲሁም በጎ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች በዓለም ላይ ያሉ የትጥቅ ግጭቶችን ለማስቆምና የጸጥታ ኃይሎችን ለማስጠበቅ በጋራ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ይገነዘባሉ” ሲል ማኅበሩ በማስታወሻው አስረድቷል። ለሰብአዊነት ማህበራዊ እኩልነት እና ሰላም ዋስትና ለመስጠት በጣም መሠረታዊ የሰብአዊ መብቶች መከበር እንደሚኖርባቸውም አክለው ገልጸዋል።

11 January 2024, 14:25