ፈልግ

2024.01.11 Membri del Sodalizio "Facchini di Santa Rosa" da Viterbo

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፡- ቤተክርስቲያን ወንጌልን ለመስበክ ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው ቅዱሳን ያስፈልጋታል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከጣሊያናዊው “የቅድስት ሮዝ” ማሕበር አባላት ጋር ተገናኝተው በነበረበት ወቅት ክርስቲያኖች ከአልጋው ወርደው የክርስቶስን ወንጌል ለማዳረስ እንዲሠሩ አበረታተዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

" ዛሬም ቅዱሳን ያስፈልጉናል፡ በሶፋ ላይ ተንጋለው ተኝተው የሚውሉ ሰዎች ሳይሆን ነገር ግን በታላቅ ፍላጎት ለመኖር እና ወንጌልን ለመስበክ ባላቸው ፍላጎት እየተቃጠሉ በቅድስና መንገድ የሚመላለሱ ሰዎች ያሰፍልጉናል” ብለዋል ቅዱስነታቸው። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሐሙስ ዕለት ጥር 02/2016 ዓ.ም “የቅድስት ሮዝ ተከታዮች” ማሕበር አባላት ጋር ቅዱስነታቸው የተገናኙ ሲሆን በወቅቱ ባደረጉት ንግግር ነበር ይህንን ግብዣ ያቀረቡት።

በመካከለኛው የጣሊያን ከተማ ቪቴርቦ ላይ የተመሰረተ፣ ለቅድስት ሮዝ ዘ ቪተርቦ የተሰጠ የጣሊያን ማህበር እ.አ.አ በ1978 ዓ.ም ተመሠረተ ነገር ግን እጅግ ጥንታዊ የሆነ ቅርስ አለው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በተዘጋጁት አስተያየቶች ላይ ማሕበሩ የቅድስት ሮዝ መንፈሳዊ ቅርስ ነው ብለዋል።

"የታሪካችሁ መነሻዎች ቅድስት ሮዝ በቪቴርቦ ወደሚኖሩበት ዘመን ይወስደናል፣ እሷም ለከተማዋ በሙሉ የአምልኮ እና የክርስቲያን ህይወት አራማጅ ያደረጋት ምሥጢራዊ ልምድ ነበራት" ሲሉ ተናግሯል።

ቅዱሳን 'በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ተንቀሳቀሱ'

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ስለ ህይወቷ ሲያሰላስሉ ቅድስት ሮዝ እ.አ.አ (1233-1251) በፍፁም ድህነት ውስጥ ለመኖር እና በበጎ አድራጎት ስራ ለመሳተፍ እራሷን በለጋ እድሜዋ አሳልፋ ሰጠች ያሉ ሲሆን በዚያን ጊዜ የጳጳሱ ግዛት አካል በሆነው በቪቴርቦ የሚኖሩ ብዙ ነዋሪዎችን ለኢየሱስ የላቀ ፍቅር እንዲያሳዩ አድርጋለች፣ በስብከቷም ምክንያት ከቤተሰቦቿ ጋር በግዞት በመቆየት የአካባቢውን ባለስልጣናት “አስቸግረውም ነበር” ሲሉ ጳጳሱ ተናግረዋል።

"እሷ 'የተጨነቀች ቅድስት' ነበረች ልንል እንችላለን፣ በመንፈስ ቅዱስ ተገፋፍታ ውስጣዊ ልምዷ ተደብቆ መቆየት አልቻለም፣ ነገር ግን ቤቱን በሙሉ እንደሚያበራ እንደ መብራት ብርሃን ተሰራጭታለች" ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የእሷን ምሳሌ በዘመናችን ለነበሩ ክርስቲያኖች እንደ ግብዣ አድርገው አቅርበዋል።

“ይህ እንግዲህ ከሁሉም በላይ አስፈላጊው ነገር ነው፡ በቅድስት ሮዝ በኩል ወንጌልን ማሳወቅ። እና በአንድነት እና በመተሳሰብ እሴቶቹን ‘በእምነት፣ በጥንካሬ እና በፈቃድ’ ‘በመከባበር እና በትህትና’ መኖርን በጋራ እና በአንድነት እናድርግ” ብሏል።

 

12 January 2024, 16:23