ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በስፔን ሙርቺያ ከሚገኘው የሳንትአንቶኒዮ የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ አባላት ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በስፔን ሙርቺያ ከሚገኘው የሳንትአንቶኒዮ የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ አባላት ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት   (Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በሁሉም ዘርፍ እግዚአብሔርን መስክሩ ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በስፔን ሙርቺያ ከሚገኘው የሳንትአንቶኒዮ የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ አባላት ጋር ባደረጉት ንግግር ምእመናን በሚሠሩት ሁሉ እና ባሉበት የእግዚአብሔርን ፍቅር እንዲመስሉ ጋብዘዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የትም ብትሆኑ የእግዚአብሔርን ፍቅር መስክሩ እና በመልካም ተግባራችሁም የእርሱን መቀራረብ አርአያ አድርጉ፣ በማለት የተናገሩት ቅዱስነታቸው ይህንን የተናገሩት ደግሞ ሐሙስ ታኅሳስ 25/2016 ዓ.ም ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቫቲካን የስፔን የሙርቺያ ሳንት አንቶኒዮ የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ አባላት ባደረጉት ንግግር ላይ ነበር።

ከቤተክርስትያን እምብርት የተወለደ

እ.አ.አ በጥር ወር 2023 ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የዩኒቨርሲቲው መስራች ሆሴ ሉዊስ ሜንዶዛ ፔሬዝ ያፈሩትን ትሩፋት በማስታወስ በቫቲካን ክሌሜንጢኖስ አዳራሽ ለተገኙ ከ600 በላይ ሰዎች የወንጌል አገልግሎት እንዲሰጡና የሚስዮናውያን መንፈስ እንዲኖራቸው ቅዱስ አባታችን ጋብዘዋል።

አባ ሆሴ ሉዊስን በተመለከተ የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንደ ትሩፋታቸው “ሚሲዮናዊ፣ ወንጌላዊ እና ጥልቅ ህልውና የነበራቸው”፣ “ከቤተክርስቲያኗ ልብ የተወለዱ” እና “በእግዚአብሔር ፍቅር ኃይል የታነፀ” ዩኒቨርሲቲን ትተው መሄድ እንደሚፈልጉ አስታውሰዋል።

የእግዚአብሔርን ፍቅር እና መልካምነት መመስከር

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ክርስቲያኖች ሥራዎቻቸው ሁሉ እንደ ክርስቶስ አባላት እና እናታችን የሆነችው የቤተክርስቲያን አባላት መሆን እንዳለበት እንዲገነዘቡ አስታውሰዋል።

ስለዚህም፣ በእምነት እና በፍቅር በመነሳሳት ለቤተክርስቲያኗ ሚስዮናዊ እና ወንጌላዊ ተልእኮ በተጨባጭ ማበርከት አለብን ሲሉ አሳስበዋል፣ በመጨረሻም ቅዱስነታቸው የአባላቱን ቁርጠኝነት አመስግነዋል።

 

 

 

05 January 2024, 12:42