ፈልግ

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዩክሬን ላደረጉት የሰላም ጥረት አመስግነዋል! የዩክሬን ፕሬዝዳንት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዩክሬን ላደረጉት የሰላም ጥረት አመስግነዋል!  (Vatican Media)

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዩክሬን ላደረጉት የሰላም ጥረት አመስግነዋል!

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር በስልክ ተነጋግረዋል፤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከ80 በላይ አገሮችን ያሳተፈ የሰላም የማስፈን ጥረት እና ላደረጉት ድጋፍ አመስግነዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ በቅርቡ ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር የተከበረውን የገና እለት አስመልክተው ለዩክሬን ሰላም ባቀረቡት ጥሪ እና ከእዚህ ቀደም ቅዱስነታቸው በተከታታይ በዩክሬይን እና በቀጠናው ሰላም እንዲሰፍን ላቀረቡት የሰላም ጥሪ ያላቸውን አድናቆት ፕሬዚዳንት ቮሎድሚሪ ዘለኒስኪ ለቅዱስነታቸው ምስጋና አቅርበዋል።

ይህ አድናቆት የተላለፈው በቅርቡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እና ፕሬዚዳንት ቮሌድሚር ዘለንስኪ በስክል ባደረጉት ንግግር እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ይህ የስልክ ጥሪ የተካሄደው ትላንት ሐሙስ ታኅሳስ 18/2016 ዓ.ም ሲሆን የስልክ ንግግራቸው ዝርዝር ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ሐሙስ በይፋዊው የፕሬዝዳንቱ ድረ-ገጽ ላይ እና በ X የቲውተር ገጻቸው ላይ አስፍረውት ይታያል።

ፕሬዝደንት ዘለንስኪ እንዳሉት "ለገና ሰላምታ ለዩክሬን እና ዩክሬናውያን፣ ለሰላም ምኞታቸው - ለሁላችን ሰላም ሲሉ ምስጋናን ለመግለጽ ከብፁዕ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር አሁን ተነጋግሬአለሁ"በሰላም እቅዱ ቀመር ላይ በጋራ ስራችን ላይ ተወያይተናል - ከ 80 በላይ አገራት በተወካዮቻቸው ደረጃ ቀድሞውኑ ተሳታፊ ናቸው። ለሥራችን ለተደረገልን ድጋፍ ቫቲካንን አመሰግናለሁ” ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

ተከታታይ የስልክ ውይይቶች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ በግንቦት 13/2022 ለሁለተኛ ጊዜ በአካል ከዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ጋር በቫቲካን ተገናኝተው ነበር። የመጀመሪያው እ.ኤ.አ. የካቲት 24 ቀን 2022 ሩሲያ ጎረቤቷን ከመውረሯ በፊት በ2020 ዓ.ም ነበር።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሁለቱ ሰዎች ብዙ ጊዜ በስልክ ሲነጋገሩ የቆዩ ሲሆን የመጀመሪያው ጦርነቱ ከፈነዳ ከሁለት ቀናት በኋላ እ.አ.አ የካቲት 26 ቀን 2022 ነበር።

የመጀመሪያውን የስልክ ውይይት ተከትሎ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በአውሮፓ ሀገር እየተከሰቱ ባሉት አሳዛኝ ክስተቶች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸው፣ ፕሬዝዳንቱ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለዩክሬን ሕዝብ ላደረጉት መንፈሳዊ ድጋፍ አመስግነዋል።

እ.አ.አ. በመጋቢት ወር  22/2022 እንደገና በስልክ የተነጋገሩ ሲሆን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ስለ አስከፊው የሰብአዊ ሁኔታ ለጳጳሱ እንደነገሯቸው እና በሰው ልጆች ላይ ለሚደርሰው መከራ መፍትሄ ለመፈለግ የቅድስት መንበር የሽምግልና አገልግሎት አቅርቦት በደስታ ተቀብለዋል።

በኋላ እ.ኤ.አ. በነሐሴ 12 ቀን 2022 ዓ.ም በሩሲያ ወረራ ምክንያት የዩክሬን ህዝብ የደረሰባቸውን አሰቃቂ ሁኔታዎች ለመወያየት ሌላ የስልክ ውይይት አደርገን ነበር ሲሉ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ተናግረዋል። እንዲሁም ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለጸሎታቸው አድናቆታቸውን ገልጸው ኪየቭን እንዲጎበኙ ጋብዘዋቸዋል።

29 December 2023, 12:42