ፈልግ

POLAND BELIEF EUROPEAN YOUTH MEETING

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለታይዜ ወጣቶች፡ 'የተለየ ዓለም ለመገንባት ደፋር' ሁኑ ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለ46ኛው የአውሮፓ የታይዜ ስብሰባ ተሳታፊዎች ሰላምታ ማቅረባቸው የተገለጸ ሲሆን ወጣቶች የማዳመጥን ልምድ እንዲቀበሉ እና በህብረተሰቡ ተገፍተው ዳር ላይ ያሉትን እንዲቀበሉ አሳስበዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በታኢዜ ማህበረሰብ ጥላ ስር ለተሰበሰቡ ወጣቶች ሰላምታ ልከዋል፣ “የአካባቢውን ህዝብ እና የቤተክርስቲያን ማህበረሰቦችን ህይወት ለመካፈል” በሉብልጃና፣ ስሎቬንያ ለተሰበሰቡ ወጣቶች መልእክት ማሰታለፋቸው ተገልጿል።

ከተለያዩ ሀገራት እና ቤተ እምነቶች የተውጣጡ ወጣቶች የተሳተፉበት 46ኛው የታይዜ አውሮፓ ስብሰባ እ.አ.አ ከታህሳስ 28-2023  እስከ ጥር 1/2024 ዓ.ም በመካሄድ ላይ ያለ እና “የጋራ ጉዞ” በሚል መሪ ሃሳብ ላይ ያተኮረ ስብሰባ እየተካሄደ ይገኛል።

"የተለየ ዓለም ለመገንባት ደፋር" መሆን ያስፈልጋል

የቫቲካን ዋና ጸኃፊ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ባስተላለፉት መልእክት፣ ተሳታፊዎች እንደ ቤተ ክርስቲያን እና እንደ ማኅበረሰብ “ከእግዚአብሔር እና ከሌሎች ጋር ያለውን ውብ የወዳጅነት ልምድ” እንዲኖሩ ዕድል የሚፈጥረውን ዝግጅት በመካፈላቸው አመስግነዋል።

"ከሙታን የተነሳው የጌታ አካል በአለም ውስጥ እንዳለ" ወጣቶች የመደማመጥ ጥበብን እንደገና እንዲያገኙ ተጋብዘዋል ይህም በመተማመን ልብ ውስጥ ያለ የፍቅር ተግባር ነው። በመደማመጥ እጦት ምክንያት ግጭቶችና ጦርነቶች በቀጣይነት በሚነሱበት ዓለም ውስጥ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ወጣቶች “የተለየ ዓለም፣ የመደማመጥ፣ የመነጋገር እና ግልጽነት ያለው ዓለም ለመገንባት እንዲደፍሩ” አሳስበዋል።

ለ‹ጥራት ለውጥ› መስራት

ፈተናው ይላል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን በኩል ያስተላለፉት መልእክት  ፈተናው “በሕይወታችን ውስጥ በጥራት ለውጥ ለማምጣት መሥራት” ነው፣ በተለይም ሁሉንም ዓይነት የሰዎች ምድቦች “መገለል፣ መዘጋት፣ ማግለልና አለመቀበል”ን ማስወገድ ያስፈልጋል ብለዋል።

በዚህ መንገድ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት፣ ወጣቶች “ባህሎችና ሃይማኖቶች የተረጋጋና ክፍት ዓለም እንዲኖር” ገንቢዎች ሊሆኑ ይችላሉ ሲሉ በመልእክታቸው ውስጥ አስፈረዋል።

እንደ ኢየሱስ ሆናችሁ ኑሩ

ማንንም እንዳላገለለው ይልቁንም በህብረተሰቡ ዳር ባሉ ሰዎች ውስጥ የእግዚአብሔርን መገኘት እውቅና እንደሰጠው እንደ ኢየሱስ እንዲኖሩ ራሳቸውን እንዲሰጡ በመልእክታቸው ያበረታቱት ቅዱስነታቸው ይህ በብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን በኩል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ያስተላለፉት መልእክት “በእናንተ እንደሚተማመኑ እና እንደሚያምኗችሁ እና ቤተክርስቲያንም እንደምታምናችሁ” በማረጋገጥ መልእክታቸውን ያጠናቅቃሉ። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በቃላቸው እና በተግባራቸው “ደካማዎችን ለማይቀበለው ለዓለማችን ጠንከር ያለ መልእክት እንዲሰጡ፣ የፍቅር፣ የፍትህ እና የሰላም ህልሞቻችሁን ተጨባጭ እውነታ አድርጉ… ህልማችሁ እንዳይሰረቅ እና ‘ስሙ የሚገባውን ማህበረሰብ ለመገንባት’ አስተዋፅዖ አድርጉ ሲሉ ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው አክለው ገልጸዋል።

29 December 2023, 12:48