ፈልግ

የካርዲናሎች ሕብረት በቤተክርስቲያን ውስጥ የሴቶችን ሚና እና የአለም ቀውሶችን ጉዳይ ላይ  በተወያዩበት ወቅት የካርዲናሎች ሕብረት በቤተክርስቲያን ውስጥ የሴቶችን ሚና እና የአለም ቀውሶችን ጉዳይ ላይ በተወያዩበት ወቅት 

የካርዲናሎች ሕብረት በቤተክርስቲያን የሴቶች ሚና እና በዓለም ቀውሶች ጉዳይ ላይ ተወያየ

በዚህ ሳምንት በቫቲካን በተካሄደው የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እና የብፁዕን ካርዲናሎች ምክር ቤት ስብሰባ በተለይ በአጥቢያ ደረጃ የቤተ ክርስቲያንን “የሴትነት ገጽታ” ማዳመጥ እንደሚያስፈልግ ተስማምተው “የማሰላሰል እና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች መተኪያ ከሌለው የሴቶች አስተዋጾ እና ጥቅም ጋር ተቆራኝቶ መሄድ እንዳለበት ተወያይተዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የካርዲናሎች ሙሉ ምክር ቤት በቫቲካን በሚገኘው  የቅድስት ማርታ መኖሪያ ቤት በመባል በሚታወቅ ሥፍራ ውስጥ ተገኝተው ነበር፣ ይህም በዋናነት “በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለው የሴት ሚና” በሚል ርዕስ ባደረጉት ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ነበር።

ውይይቱ በጣሊያን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማስተማር ቦታ ካላቸው የነገረ መለኮት ሊቃውንት ሲስተር ሊንዳ ፖቸር፣ ዶ/ር ሉቺያ ቫንቲኒ እና አባ ሉካ ካስቲግሊኒ የሰጡትን ግንዛቤ ተጠቅሟል።

በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ “ሴቶች የማሰላሰል እና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ከማይተካው አስተዋጽዖ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከሁሉም በላይ በግለሰብ ደረጃ የክርስቲያን ማህበረሰቦች የቤተክርስቲያንን የሴቶች ገጽታ ማዳመጥ እንደሚያስፈልግ ምክር ቤቱ ተስማምቷል” በማለት የቅድስት መንበር የፕሬስ ጽ/ቤት መግለጫ አስታውቋል።

መግለጫው እንዳመለከተው ካርዲናል አማካሪዎቹ በተለይ “በዩክሬን እየተካሄደ ባለው ግጭት እና በቅድስት ሀገር ባለው አሳሳቢ ሁኔታ ላይ” እንዲሁም አሁን በዱባይ እየተካሄደ ያለው የCOP28 ሥራ ላይ በማተኮር በተለያዩ የትውልድ ክልሎቻቸው ላይ በመመስረት ወቅታዊውን የዓለም ሁኔታ በመመርመር ጊዜ አሳልፈዋል ። የምክር ቤቱ አባል ብፁዕ ካርዲናል ሴን ኦማሌይ፣ የጳጳሳዊ የሕፃናት ጥበቃ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት በመሆን በኤጲስ ቆጶስ ጉባኤዎች ድርጅታዊ ጉባኤዎች ላይ ገለጻ አቅርበዋል፣ በተለያዩ መላምቶች በምክር ቤቱ አባላት ውይይት ተደርጎበታል።

በመጨረሻም ካርዲናል አማካሪዎቹ በሲኖዶስ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የመጀመርያው ስብሰባ ላይ “በሐዋርያዊ ሕገ ቀኖና መንፈስ መርሆች እና መመዘኛዎች አፈጻጸም ላይ ያለውን ነጸብራቅ ለማስቀጠል” መወያየታቸውን የፕሬስ ጽ/ቤት መግለጫ አመልክቷል።

የካርዲናል አማካሪዎች ምክር ቤት ቀጣዩን ስብሰባ እ.አ.አ በየካቲት 2024 እንደሚያካሂድ ይጠበቃል።

07 December 2023, 11:15