ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በአሜሪካ ከሚኖሩ ከእስፓንሺ ማሕበረሰብ ካህናት ጋር በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በአሜሪካ ከሚኖሩ ከእስፓንሺ ማሕበረሰብ ካህናት ጋር በተገናኙበት ወቅት  (Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአሜሪካ ከሚኖሩ የእስፓኒሽ ማሕበረሰብ ካህናት ጋር ተገናኙ!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዩናይትድ ስቴትስ ለሚካሄደው የብሔራዊ የእስፓኒሽ ካህናት ማኅበር (ANSH) ዓመታዊ ኮንፈረንስ ተሳታፊዎችን ሞቅ ያለ ሰላምታ ያቀረቡ ሲሆን እናም በሐዋርያዊ አገልግሎት ሥራቸው በጸሎት እና ራሳቸውን ለክርስቶስ በመስጠት እንዲኖሩ አብረታቷቸዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

"ወንድሞች ሆይ በታላቅ ሐሳቦች ወይም በጥሩ ሁኔታ በተዘጋጀ የእረኝነት ሐሳብ ላይ ብቻ አትታመኑ፣ ጥፋተኞችን ብቻ አትፈልጉ፣ ነገር ግን ራሳችሁን እንድትሰጡ ለጠራችሁ፣ ታማኝነትና ጽናት ብቻ ለሚጠይቃችሁ ራሳችሁን ስጡ። እርሱ ያን ሥራችሁን ወደ ፍጻሜ የሚያደርስ፣ ልፋታችሁንም መልካም ፍሬ የሚያፈራ መሆኑን በማመን በእርሱ በመታመን ነው” ብለዋል።

ይህ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሐሙስ ኅዳር 06-2016 ጠዋት በቫቲካን በዩናይትድ ስቴትስ ለሚካሄደው የእስፓኒሽ ካህናት ብሔራዊ ማኅበር (ANSH) ዓመታዊ ጉባኤ ተሳታፊዎች ያቀረቡት ማበረታቻ ነው።

ቅዱስ አባታችን ንግግራቸውን የጀመሩት ካህናትና የጉባኤው ተሳታፊዎች ላደረጉት ጉብኝት ምስጋናቸውን በማቅረብ ነበር።

ያለማቋረጥ በጸሎት ጌታን ማግኘት አለባችሁ!

ቅዱስ አባታችን ተሳታፊዎች የግል የጸሎት ሕይወታቸውን ማዳበር እና መንከባከብ እንዳለባቸው አበክሮ ገልጿል። "እርሱን ማለት ጌታን በቅዱሳት መጻሕፍት እና በወንጌል፣ በፀጥታ አምልኮ ውስጥ መፈለግ አለባችሁ፣ ምክንያቱም የአምልኮ ስሜት ትንሽ ያጣን ይመስለኛል። ጌታን በአምልኮ ዝምታ ውስጥ ማግኘት አለብን።

አሁን ልጠይቃችሁ "በየሳምንቱ ለስንት ሰአታት አምልኮ ታደርጋላችሁ? ይህ ጥሩ ፈተና ይሆናል። ጥያቄውን ወደዚያ ወደ እናተ እወረውራለሁ ነገር ግን ሁሉም ሰው በራሱ ውስጥ ይመልሳል። ካልጸለይን፣ ካልሰገድን ህይወታችን ትንሽ ትሆናለች” ብለዋል።

ከ‘ሰዓታት’ ውጪም ቢሆን ለሰዎች ለመገኘት ሞክሩ ያሉት ቅዱስነታቸው በተመሳሳይ ካህናት ‘የጊዜ ሰሌዳን’ በመከተል የተቀጠሩ  እንዳልሆኑ እንዲያውቁ፣ ይልቁንም ሕዝቡ በሚፈልግበት ጊዜ መገኘት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

"በዚህ ውስጥ እጠይቅሃለሁ እባካችሁን ተረጋግታችሁ ከመኖር ተጠንቀቁ። አትረጋጉ፣ አትረጋጉ። አንዳንድ ጊዜ ዘመናዊው ዓለም የጊዜ ሰሌዳዎችን ያመጣልናል "አባ እባኮኾን ምስጢረ ንስሐ ለመጋብት እፈልጋለሁ? ብሎ ቢጠይቅ  ... ይህ የጊዜ ሰሌዳው አይፈቅድልኝም ብላችሁ እባካችሁን አትመልሱ። እባካችሁ ሰዎች መጀመሪያ ቅድሚያ ይሰጣቸው፣ ከዚያም የጊዜ ሰሌዳው ይከተል፣ ቅዱሳን ‘ተቀጣሪ’ አትሁኑ፤ የዚህ ባህል አደጋ ነውና ለሰዎች ያደረጋችሁትን ቁርጠኝነት፣ የልባችሁን ግልጽነት ከልሱ” ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።

ቅዱስ አባታችን በቀላል እና በተለመዱ ቃላት እንዲጸልዩ፣ ሌሎችን በወንድማማችነት እንዲቀበሉ እና በሥራቸው እንዲጸኑ አሳስቧቸዋል።

ዛሬ የክርስቶስን ስቃይ ማቃለል

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በዝምታ የማዳመጥ፣ የመጸለይ እና የማስተዋል ምሳሌ በማለት ያመሰገኗቸውን ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለቀጣዩ ዓመት የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ በመዘጋጀት ላይ መሆናቸውን አስታውሰው፣ ብፁዕ ቻርለስ አኩቲስ እና ቅዱስ ኢማኑኤል ጎንዛሌዝ ጠባቂ ቅዱሳን ሆነው መመረጣቸውን አስታውሰዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እነዚህ የቅድስና ምሳሌዎች ለኢየሱስ ቀጣይነት ያለው ስቃይ ምላሽ መስጠት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

እግዚአብሔር የተቸገሩትን ፈጽሞ እንደማይተዋቸው እንደሚጠይቃቸው በመግለጽ እያንዳንዱን ወንድምና እህት እንዴት መርዳት እንደሚችሉ እንዲያስቡ ቅዱስ አባታችን አሳስበዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከቅዱሳኑ መነሳሻን በመውሰድ የእምነት እና የአገልግሎት ጥበብ እና ሞዴሎችን ይሰጣሉ ብለዋል ።

ራሳችሁን ለጌታ ስጡ

ቅዱስ አባታችን ታማኝነታቸውን ብቻ ለሚጠይቃቸው ለጌታ እራሳቸውን እንዲሰጡ ካህናቱን አሳስበዋቸዋል፣ ጥረታቸውንም ወደ ፍጻሜ በማድረስ መልካም ፍሬ እንዲያፈሩ እርሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይረዳችኋል ያሉ ሲሆን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዚህ ምክር ንግግራቸውን ሲያጠናቅቁ እና ሌሎችን ለመርዳት የሚያደርጉት በጎ ሥራ ካህናትን በጣም እንዲደክሙና ሌሊት ለመተኛት እንዳይቸገሩ እንደሚረዳችሁ  ምኞታቸውን ከገለጹ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

17 November 2023, 15:59