ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በሁሉም ቅዱሳን በዓል ላይ ወደ ቅድስና ስጦታ እና ጉዞ ሁላችንም አብረን ተጠርተና

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ስለ ቅድስና ጥሪ እና የእግዚአብሔር ስጦታ እንዴት እንደሆነ እና ከወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እንዲሁም በመንገድ ላይ ካሉ ቅዱሳን ሁሉ ጋር ይህንን የቅድስና ጉዞ አንድ ላይ ለማድረግ ስለቀረበው ጥሪ ባለፈው ረቡዕ ጥቅምት 21/2016 ዓ.ም የሁሉም ቅዱሳን ቀን በተከበረበት ወቅት ከመላከ እግዚአብሔር ጸሎት በፊት ባደረጉት አስተንትኖ ገልጸዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ረቡዕ ጥቅምት 21/2016 ቀን የሁሉን ቅዱሳን ክብረ በዓል ለማክበር በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ላይ ለተገኙ ምዕመናን እና የአገር ጎብኝዎች ሰላምታ ካቀረቡ በኋላ የቀትር ሰዓት የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከመድገማቸው  በፊት በሁሉም ቅዱሳን ቀን በዓል ላይ የቅድስና ጥሪያችንን እናስታውሳለን ብለዋል። የምንቀበለው የእግዚአብሔር ስጦታ እንዴት እንደሆነ እና አብረን በጋራ ከሁሉም ቅዱሳን ጋር በመተባበር ሁልጊዜም በመንገድ ላይ አብረውን እንደምንጓዝ አብራርተዋል።

የቅድስና ስጦታ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የቅድስና ስጦታ ከጥምቀታችን ጋር እንዴት እንደመጣ፣ እንደሚያድግ እና ህይወታችንን እንዲለውጥ ልንከባከበው ይገባል ብለዋል ። ቅዱሳኑ እንደ እኛ ነው የሕይወት ጎዞዋቸውን የጀመሩት በማለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱም ጠቁመው የተቀበልነውን አይነት ስጦታ እየተቀበሉ፣ እናም በጉዞአችን አብረውን የሚሄዱ ለእኛ በጣም ቅርብ የሆኑ ወዳጆቻችን ናቸው ብለዋል።

በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ውስጥ አንዳንድ ቅዱሳን አጋጥመውናል ያሉት ቅዱስነታቸው ክርስቲያናዊ ጥሪን በቁርጠኝነት እና በቅንነት የሚመራ ጻድቅ ሰው፣ “በጎረቤት ያሉ ቅዱሳን” ብሎ ሊጠራቸው የሚወዳቸው ሰዎች እንዳሉ ቅዱስነታቸው የገለጹ ሲሆን ቅድስና ደግሞ “ለደስተኛ ሕይወት” ለሁሉም የተሰጠ ስጦታ ነው ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

“ስጦታ ስንቀበል የመጀመሪያ ምላሽ ምንድን ነው? በትክክል ደስተኞች መሆናችን ነው፣ ምክንያቱም አንድ ሰው ይወደናል ማለት ነው፣ የቅድስና ስጦታ ደግሞ ደስ ይለናል ምክንያቱም እግዚአብሔር ስለወደደን” ሲሉ ተናግረዋል።

እንደማንኛውም ስጦታ ለመቀበል ስንመርጥ እና ምስጋናችንን ስናሳይ፣ የእግዚአብሔርን የቅድስና ስጦታ ስንቀበል፣ የተቀበልነውን ቅድስና የመጠበቅ እና የማጠናከር ኃላፊነት እንወጣለን ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አስረድተዋል።

በጥሩ እጀባ ውስጥ የሚደረግ ጉዞ

"ቅድስና ደግሞ ጉዞ ነው፣ አንድ ላይ የምናደረገው ጉዞ፣ የምንረዳዳበት፣ ከእነዚያ ከቅዱሳን ምርጥ አጋሮች ጋር አንድ መሆን ነው" ሲሉ ቅዱስነታቸው አክለው የተናገሩ ሲሆን ቅዱሳን ምንጊዜም ልንተማመንባቸው የምንችልባቸው ታላላቅ ወንድሞች እና እህቶቻችን መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተው ሲናገሩ ስህተት ስንሠራና እንደገና ወደ ትክክለኛው መንገድ እንዲንሄድ ሊረዱን ስለሚችሉ፣ እንደ “ቅን ወዳጆች አድርገናቸው ልንቆጥራቸው ይገባል፣ ምክንያቱም እነርሱ እምነት ሊሰጡን ይችላሉ፣ ደህንነታችንን ይመኛሉ” ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

በእምነት ሕይወታቸው እና ምስክርነታቸው መነሳሻን ይሰጡናል ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እናም "በጸሎታቸው ረድኤትን እንቀበላለን" ከእነሱ ጋር አንድ ሆነን "በወንድማማች ፍቅር ማሰሪያ" እርስ በርሳችን እንተቃቀፋለን ሲሉ ተናግረዋል።

የቅዱሳን ሕይወት

በማጠቃለያውም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እያንዳንዱ ሰው ስለ ቅዱሳን ሕይወት የበለጠ እንዲያውቅ እና የራሳቸውን የሕይወት ፈተናዎች እንዴት መቋቋም እንደሚችሉ እንዲማሩ አበረታተዋል። በተጨማሪም የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ስንቀበል ለቅድስና የተጠራን እና ሁልጊዜም የምንደግፈው እና የምንረዳው መሆኑን በማስታወስ የግል አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን ቅዱሳን ለእኛ ቅርብ ናቸው፣ ወደ እነርሱ በጸሎት፣ ከእነሱ ጋር በመገናኘት፣ ለሰጠን ነገር ሁሉ እና ለሚጠራን ዘላለማዊ ደስታ ለእግዚአብሔር ባለን ምስጋና ከእነሱ ጋር ልንገናኝ እንችላለን ብለዋል።

"የቅዱሳን ሁሉ ንግሥት ማርያም፣ የተቀበልነውን የጸጋ ስጦታ ደስታ እንዲሰማን ትርዳን እና ወደ ዘላለማዊው መድረሻ ያለንን ፍላጎት ታሳድግልን” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው አስተንትኖዋቸውን አጠቃለዋል።

 

01 November 2023, 18:58