ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን ከስኮትላንድ የሴልቲክ እግር ኳስ ክለብ ጋር በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን ከስኮትላንድ የሴልቲክ እግር ኳስ ክለብ ጋር በተገናኙበት ወቅት  (Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ለእግር ኳስ ተጫዋቾች ማሸነፍ ማለት ሁሉም ነገር ማለት እንዳልሆነ ተናገሩ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ረቡዕ ኅዳር 19/2016 ዓ.ም ከስኮትላንድ የሴልቲክ እግር ኳስ ክለብ ጋር በተገናኙበት ወቅት እንደ ተናገሩት የእግር ኳስ ተጫዋቾቹ ጥሩ ምሳሌ እንዲሆኑ እና ገንዘብን ብቻ የሚያሳድዱ እንዳይሆኑ የማበረታቻ መልእክታቸውን ቅዱስነታቸው አስተላልፈዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ረቡዕ ኅዳር 19/2016 ዓ.ም ከግላስኮ የሴልቲክ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋጮች ጋር በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተገናኙበት ወቅት “በስፖርት… በጣም ቆንጆው ነገር ያለምክንያታዊነት፣ አብሮ የመጫወት ውበት ነው” ብለዋል።

ስለ ስፖርት በጣም ቆንጆው ነገር

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለቡድኑ ያደረጉት ንግግር በአንድ ረዳት ከተነበበ በኋላ ቅዱስነታቸው በአጭሩ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጣሊያንኛ ቋንቋ ሲናገሩ ተጫዋቾቹ አማተር መንፈሳቸውን እንዳያጡ፣ ለራሳቸው ሲሉ የስፖርት ፍቅር እንዳያጡ ጋብዘዋል። አትሌቶች ሁል ጊዜ የሚጫወቱት ለማሸነፍ መሆኑን ቢያስታውሱም፣ በሜዳው ማሸነፍ የመጨረሻው ግብ እንዳልሆነ ገልጿል። ይህ “በስፖርት ውስጥ በጣም ቆንጆው ነገር ነው” ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በተዘጋጀው ንግግራቸው በሜዳም ሆነ ከሜዳ ውጪ ጥሩ አርአያ መሆን ከማሸነፍ በላይ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን ጥሩ ምሳሌ “ድፍረትን፣ ጽናትን፣ ልግስናን እና አምላክ የሰጠንን የሌሎችን ክብር ማክበርን ያጠቃልላል” ብሏል።

ጥሩ አርአያ መሆን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የሴልቲክ ክለብ የተመሰረተው በተለይ “በስኮትላንድ ግላስኮ ከተማ ድህነትን ለመቅረፍ የተቋቋመ መሆኑን” አስታውሰው “በእውነቱ… በጣም ለተቸገሩ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የሚደረገውን የበጎ አድራጎት ተግባር” አወድሰዋል። በተመሳሳይ ጊዜ "ቆንጆ ጨዋታ" እንዴት እንደተለወጠ እና አሁን ለገንዘብ ትርፍ ብቻ የመጫወት አደጋ ተጋርጦበታል ሲሉ ያላቸውን ስጋት አክለው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለተጫዋቾቹ እንደተናገሩት “የክለባችሁ ውድ ትሩፋት በትከሻችሁ ላይ ከባድ ኃላፊነት ስለሚጥል በተለይ ለወጣቶች ጥሩ አርአያ እንድትሆኑ በማሳሰብ ነው። ለአትሌቲክስ የላቀ ብቃት እንዲጥሩ ብቻ ሳይሆን ሰዎች “የደግነት ሰዎች፣ ለብዙ ጥቅሞች ጥበበኛ መጋቢዎች እንዲሆኑ የሚያውቁ ትልቅ ልብ ያላቸው ሰዎች” አድርገው እንዲመለከቱት ያሳሰቡ ሲሆን ስለ “ግላዊ አቋማቸው” ብቻ እንዳይጨነቁ አበረታቷቸዋል። በህብረተሰብ ውስጥ ካላችሁ ልዩ የሆነ ሥፍራ ተጠብቆ እንዲቀጥል ማድረግ ይኖርብቻሃል” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ተጫዋቾቹ “ስፖርት ጥሩ እና ክቡር የሚያደርገውን ነገር ሁሉ ማስታወስ እና መመስከርን ቀጥሉ” ካሉ በኋላ  ንግግራቸውን አጠናቅቀዋል።

 

30 November 2023, 13:34