ፈልግ

 ለጋዛ ሰብአዊ ርዳታ ይዘው ወደ ራፋህ መሻገሪያ የሚሄዱ መኪኖች ለጋዛ ሰብአዊ ርዳታ ይዘው ወደ ራፋህ መሻገሪያ የሚሄዱ መኪኖች  (ANSA)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለተሰቃዩ ፍልስጤማውያን እና እስራኤላውያን ያላቸውን ቅርበት ገለጹ!

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በየእለቱ እየተሰቃዩ ያሉትን ፍልስጤማውያን እና እስራኤላውያንን እንደሚያስታውሷቸው፣ ስለ እነርሱ እንደሚጸልዩላቸው እና በዚህ “ጨለማ ጊዜ” ከእናተ ጋር ነኝ ሲሉ የተናገሩት ቅዱስነታቸው ሁከቱ እንዲቆም፣ አፋጣኝ የነፍስ አድን ጥረት እንዲደረግ እና ለሁሉም ሰብዓዊ ዕርዳታ ተደራሽ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እሁድ ኅዳር 02/2016 ዓ.ም ያደረጉትን የመልአከ ሰላም ጸሎትን ተከትሎ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰበው ሕዝብ ንግግር ያደረጉት በእስራኤል እና በፍልስጤም ያለውን እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ በመግለጽ ለተሰቃዩት ፍልስጤማውያን እና እስራኤላውያን ያላቸውን ቅርበት ጠቁመዋል። በየቀኑ እንደሚያስታውሳቸው እና እንደሚጸልይላቸው ተናግሯል፣ እናም “በዚህ የጨለማ ጊዜ” ለእነርሱ ያላቸውን ቅርበት ቅዱስነታቸው ገልጿል።

“የጦር መሳሪያው ይቁም፡ መቼም እርሱ ማለትም የጦር መሣሪያ ወደ ሰላም አይመራም፣ ግጭቱም አይሰፋ! ይበቃል! በቃ ወንድሞቼ! በጋዛ፣ የቆሰሉት በአስቸኳይ ይታደጉ፣ ሲቪሎች ይጠበቁ፣ ለተጎዳው ሕዝብ የበለጠ ሰብዓዊ ዕርዳታ ይፈቀድ። ታጋቾቹ አዛውንቶችን እና ህጻናትን ጨምሮ ይፈቱ። ማንኛውም ሰው፣ ክርስቲያን፣ አይሁዳዊ፣ ሙስሊም፣ የየትኛውም ሕዝብ ወይም ሃይማኖት፣ ማንኛውም ሰው የተቀደሰ ነው፣ በእግዚአብሔር ፊት ውድ ነው በሰላም የመኖር መብት አለው። ተስፋ አንቆርጥ፡ እንጸልይ እና ሳንታክት እንስራ የሰው ልጅ ስሜት የልብ ጥንካሬን እንዲያሸንፍ እንጸልይ”።

13 November 2023, 14:43