ፈልግ

TOPSHOT-FRANCE-PAKISTAN]-RELIGION-RIGHTS-POLITICS

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፡ እስያ ቢቢ ‘የማያቋርጥ ሰማዕትነት’ ተምሳሌት ናት ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ቅድስናን በተመለከተ በተካሄደው ጉባኤ ላይ ተሳታፊዎችን ባነጋገሩበት ወቅት “የእኛን ጊዜ ጨምሮ ሰማዕታት የታጡበት ጊዜ የለም” ማለታቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

"እግዚአብሔር አንድን ግለሰብ ሲጠራ ሁል ጊዜ ለሁሉም የጥቅም ብሎ ነው" ያሉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ቅዱስነታቸው ይህንን የተናገሩት ደግሞ ሐሙስ ኅዳር 06/2016 ዓ.ም ጥዋት በቫቲካን ተካሂዶ በነበረው ጉባኤ ላይ 'የቅዱሳን ሁለንተናዊ ይዘት' በሚል ርዕስ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ነበር።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በንግግራቸው ውስጥ ስለ ቅድስና ሦስት አስፈላጊ ገጽታዎች ተናግረዋል፣ አንድነትን የመፍጠር ኃይል ፣ በቤተሰብ ውስጥ ስላለው ቦታ እና ሰማዕትነት ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።

የእስያ ቢቢ "ቀጣይ ሰማዕትነት"

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሰማዕትነት “ኃይለኛ አብነት” የቅድስና ምሳሌ ነው፣ ለዚህም “በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ብዙ ምሳሌዎች አሉን” ብለዋል።

"አሁን ያለንበትን የራሳችንን ጊዜ ጨምሮ ሰማዕታት የሌሉበት ዘመን የለም" ሲሉ ቅዱስነታቸው አጽንዖት ሰጥው የተናገሩ ሲሆን "እነዚህ ሰማዕታት እንደሌሉ አድርገን እናስባለን፣ ነገር ግን በተከታታይ በሰማዕትነት ስለኖሩት የክርስትና ህይወት ጉዳይ እናስብ የእስያ ቢቢ ጉዳይ" ማሰብ እንችላለን ብለዋል።

በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ተናግራላች በሚል ክስ የሞት ፍርድ የተፈረደባት ፓኪስታናዊቷ ካቶሊካዊት ቢቢ በእዚህ ምክንያት የተነሳ ለብዙ ዓመታት በእስር ላይ ቆይታላች፣ በመጨረሻም ከእስር ተፍታ ወደ ካናዳ ከቤተስቦቿ ጋር ወደ መሄዷ ይታወቃል።

"ወደ ዘጠኝ ዓመታት የሚጠጋ የክርስቲያን ምስክርነት!" ሲሉ በጉዳዩ ላይ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አስምረውበታል። "ለእምነት እና ለበጎ አድራጎት የሚመሰክሩ ብዙ፣ እንደ እሷ ያሉ ብዙዎች አሉ" ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

የአንድነት ኃይል

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ይህም በመጀመሪያ በበጎ አድራጎት ተግባር የሚፈጸም ነው። ስለዚህም ከወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ጋር አንድ ያደርገናል እና የግል ክስተት ብቻ ሳይሆን የማህበረሰብ ጉዳይ ነው" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

“እግዚአብሔር አንድን ሰው ሲጠራ፣ እንደ አብርሃምና ሙሴ፣ ጴጥሮስና ጳውሎስ፣ ሁልጊዜም ለሁሉም የሚጠቅም ነው” ብለዋል ሊቀ ጳጳሱ።

ለኢየሱስ ፍቅር ብቸኛው ህጋዊ ምላሽ ልክ ማቴዎስን ኢየሱስ እንደጠራው ጓደኞቹ ደግሞ መሲሑን እንዲገናኙት እንደጠራቸው፣ ወይም ጳውሎስ፣ ኢየሱስ ማን እንደሆነ ለሌሎች ለማካፈል መፈለግ ብቻ ነው ብሏል። ከሙታን የተነሣውን አግኝቶ የአሕዛብ ሐዋርያ ሆነ እኛም በእዚህ መልኩ ተግባራችንን ማከናወን እንችላለን ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።

የቤተሰብ ቅድስና

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የመጨረሻ ርዕሰ ጉዳይ በቤተሰብ ውስጥ የሚከሰተውን ቅድሳን በተመለከተ ተናግረዋል።

ምንም እንኳን ይህ ዓይነቱ ቅድስና “በናዝሬት ቅዱሳን ቤተሰብ ውስጥ ከምንም በላይ በግልጽ የሚታይ” ቢሆንም “ቤተ ክርስቲያኗ ሌሎች ብዙ ምሳሌዎችን ትሰጠናለች” በማለት ተናግረው በተለይም “ቅዱስ የሆነ ጋብቻ የሚኖሩ ጥንዶች፣ እያንዳንዱ የትዳር ጓደኛ ሌላውን የመዳኛ መሣሪያ ሆኖ የተገኘባቸው ቅዱሳን ጥንዶች ናቸው” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የተጋቡ ጥንዶች ቅድስና የእያንዳንዱ ግለሰብ ቅድስና ድምር ብቻ አይደለም ብለዋል። ይልቁንም የእያንዳንዳቸው ቅድስና የትዳር አጋራቸውን ለማባዛት አስተዋጽኦ ያደርጋል ያሉ ሲሆን ለዚህ ዓይነቱ ቅድስና ምሳሌ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሲሰጡ ፖላንዳዊያን ጥንዶች ዮሴፍ እና ቪክቶሪያ ኡልማን እና ሰባት ልጆቻቸውን አቅርበዋል። የአይሁድ ቤተሰቦችን በቤታቸው በመደበቅ ከናዚዎች ለማዳን ሞክረዋል፣ነገር ግን በመጨረሻ ተይዘው ተገደሉ ሲሉ ቅዱስነታቸው አክለው ገለጸዋል።

ይህ የፖላንድ ቤተሰብ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንደ ተናገሩት ከሆነ "መቀደስ የማህበረሰብ ጉዞ መሆኑን ያስታውሰናል፣ ብቻውን ሳይሆን ጥንድ ሆኖ የሚከናወን ነው። ሁልጊዜም በማህበረሰብ ውስጥ" ቤተሰብ የቅድስና ሁሉ ምንጭ ሆኖ ያገለግላል ብለዋል።

 

17 November 2023, 15:53