ፈልግ

በሱዳን የሚካሄደውን ጦርነት በመሸሽ ወደ ቻድ የሚሰደዱ ስደተኞች በሱዳን የሚካሄደውን ጦርነት በመሸሽ ወደ ቻድ የሚሰደዱ ስደተኞች   (ZOHRA BENSEMRA)

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በጦርነት በምትታመሰው ሱዳን ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደረግ ተማጽነዋል!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሱዳን የሚገኙ መሪዎች ለተሰቃዩ ሰዎች ሰብዓዊ ርዳታ እንዲያገኙ እንዲያመቻቹ እና የእርስ በርስ ጦርነትን ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር በመሆን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እንዲሰሩ ልባዊ ጥሪ አቅርበዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሱዳን እየተካሄደ ባለው የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት የተከሰተውን አሳሳቢ ሰብዓዊ ቀውስ ትኩረት ሰጥተው ነበር ይህም ግጭት ምንም ዓይነት የመቀነስ ምልክት አላሳየም።

በእሁዱ ኅዳር 2/2016 ዓ.ም የመልአከ ሰላም ጸሎት ማጠቃለያ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የተፈናቀሉ እና በአጎራባች ሀገራት ያሉ ስደተኞችን ጨምሮ ብዙ ተጎጂዎችን እያፈናቀለ ያለውን ጦርነት አውግዘዋል።

"እኔ ለእነዚያ ውድ የሱዳን ህዝቦች ስቃይ ቅርብ ነኝ፣ እናም ለሀገር ውስጥ መሪዎች ሰብአዊ እርዳታን እንዲያመቻቹ እና ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ አስተዋፅዖ ጋር ሰላማዊ መፍትሄዎችን ለመፈለግ እንዲሰሩ ልባዊ ጥሪዬን አቀርባለሁ። እነዚህን በችግር ላይ ያሉትን ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን አንርሳ!” ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ UNHCR እንደዘገበው በሱዳን ያለው የእርስ በርስ ጦርነት እ.አ.አ በሚያዝያ 2023 ከተጀመረ ወዲህ ወደ ስድስት ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎችን ከቤት ንብረታቸው እንዲፈናቀሉ አድርጓል። የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር ዶሚኒክ ሃይዴ በቅርቡ ሀገሪቱን ጎብኝተው ከፍተኛ ስጋት ሊፈጠር እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። በሰዎች ስቃይ ውስጥ፣ “ከአለም እይታ እና ከዜና ዘገባዎች ርቆ፣ የሱዳን ግጭት መቀጠሉን ቀጥሏል። በማያቋርጥ ውጊያው የሚፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ በመላ ሀገሪቱ ሊታሰብ የማይችል ሰብዓዊ ቀውስ እየተፈጠረ ነው” ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።

 

 

13 November 2023, 14:48