ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ መንፈስ ቅዱስ ወደ ስምምነት እና ወደ በአክብሮት መደማመጥ ይመራናል አሉ።

በመስከረም 23/2016 ዓ.ም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን 16ኛ መደበኛ ጠቅላላ የሲኖዶ ጉባኤ መጀመሩ የሚታወቅ ሲሆን በሲኖዶሱ መክፈቻ ላይ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ባደረጉት ንግግር መንፈስ ቅዱስ የሲኖዶሱ ዋና አካል ነው፣ ሁሉም ሰው መንፈስ ቅዱስን በአክብሮት እንዲያዳምጡ ጠይቀዋል።

የእዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ "የሲኖዶሱ ዋና ተዋናይ እኛ አይደለንም መንፈስ ቅዱስ ነው" ያሉት ሲሆን  መንፈስ ቅዱስ የሚመራ ከሆነ ጥሩ ሲኖዶስ ነው፣ እሱ መሪ ካልሆነ ግን በጣም አስቸጋሪ ነው ብሏል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ይህንን ጠንካራ ማሳሰቢያ የሰጡት መከረም 23/2016 ዓ.ም በጀመረው 16ኛ የጳጳሳት ሲኖዶስ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ ነው።

16ኛው የጳጳሳት ሲኖዶስ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በሁለት ክፍለ ጊዜዎች በአንድ ዓመት ልዩነት የሚካሄድ ሲሆን የመጀመሪያው እ.አ.አ ከጥቅምት 4 እስከ 29 ቀን 2023፣ ሁለተኛው በጥቅምት 2024 ይካሄዳል።

ቅዱስ አባታችን ንግግራቸውን የጀመሩት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ጳውሎስ ስድስተኛ ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በኋላ የሲኖዶሱን ዋና ጽህፈት ቤት በማቋቋም የጳጳሳት ሲኖዶስ ምክክር ለማድረግ መነሳታቸውን በማስታወስ የጉባሄው ተሳታፊዎችን እናኳን ደህና መጣችሁ በማለት ነበር ንግግራቸውን የጀመሩት። ቤተክርስቲያኗ ይህንን ውይይት ለማድረግ ሁል ጊዜ ዝግጁ እንዳልነበረች፣ ነገር ግን በመላው ዓለም ውስጥ ለሚገኙ ጳጳሳት እና የእግዚአብሔር ሕዝቦች፣ አሁን ስለ ሲኖዶሳዊነት ለመናገር የበለጠ አስፈላጊ እየሆነ እንደመጣ ያመኑ ሲሆን "ቀላል አይደለም ነገር ግን ውብ ነው፣ በጣም ቆንጆ ነው" ብሏል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳጳሳት ሲኖዶሳዊ ጉዟቸውን ሲጀምሩ የሚረዷቸውን ከእዚህ ቀደም የተደርጉትን የሲኖዶስ ጉባሄ መጻሕፍት ስብስብ እንዲያነቡ ልዩ ምክረ ሐሳብ ሰጥተዋል።

የቤተክርስቲያን ዋና ተዋናይ በእጃችን ይዞ ይመራናል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አክለው እንደ ገለጹት ከሆነ መንፈስ ቅዱስ "የቤተ ክርስቲያን ሕይወት ዋና ተዋናይ" "ቤተ ክርስቲያንን ወደ ፊት የሚመራ" እና እንደ እናት ሆኖ ይመራናል ብሏል። መንፈስ ቅዱስ በእጃችን ይዞ ይመራናል እና ያጽናናል በማለት አክለው ገልጿል።

በሁሉም ነገር መስማማት አንችልም፣ ለ"ልዩነት" ክፍተት መፈጠሩ የማይቀር መሆኑን በማሳየት ወደ "ስምምነት" መድረስ እንድንችል ቅዱስ አባታችን ጠይቀዋል።

ሲኖዶሱንም በተመሳሳይ መንገድ ከጨረስነው፣ “ያለ ነገሩ ሲኖዶስ አይደለም” በማለት ሐሳብ አቅርበዋል።

"በመንፈስ ቅዱስ የተደረገ እንጂ እኛ አይደለንም"

“ልዩነት፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መካተት አለበት” በማለት፣ “ይህ በእኛ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ መከናወን አለበት” በማለት አጽንዖት ሰጥቷል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሲኖዶሱ ላይ የሚፈጸሙ የተዛቡ ድርጊቶችን አስጠንቅቀዋል፣ “ፓርላማ አይደለም”፣ “የቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ጉባሄ  ነው” ብለዋል።

ለሚያደርጉት መልካም ሥራ ሲያሞግሱ፣ አንዳንድ ጊዜ በትኩረት በሚታዩ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩሩ ገልጸው፣ “ማዳመጥ ቅድሚያ የሚሰጠው ነው” የሚለውን የቤተ ክርስቲያንን ፍላጎት ለማስተላለፍ እንዲሠሩ አሳስበዋል።

"ሁሉም ሰው ሃሳቡን በነጻነት መግለጽ አለበት" ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መንፈስ ቅዱስ በእምነታቸው ሊያጸናቸው በመንገዳው ላይ ነው ሲሉ ተናግሯል።

"የክርስቶስ መሀል መሆን - የሲኖዶስ መሪ"

ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሱ ንግግር በፊት በቫቲካን በሚገኘው ጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ የተካሄደው ሥነ ሥርዓት የተጀመረው በግብፅ የአሌክሳንድርያ ኮፕቲክ ካቶሊካዊ ፓትርያርክ ኢብራሂም ይስሐቅ ሴድራክ ፕሬዝደንት ልኡካን ሰላምታ በመስጠት ጌታ ለቤተክርስቲያን ያለውን ፍቅር እንዴት እንደሚቀጥል እና እንዳሳየ አስመረው በማናገር ሲኖዶሱን አነሳስቷል።

ፓትርያርክ ሰድራክ ይህ ሲኖዶሳዊ ሂደት ሁል ጊዜ ቀላል እንዳልሆነ አምነዋል፣ በተለይም ሲጀመር፣ ምክንያቱም ይህ ሲኖዶሳዊ ሲኖዶስ የተዘጋጀው “የእግዚአብሔር ሕዝብ በማማከር ከእያንዳንዱ የተጠመቁ ሰዎች በማመከር፣ የየራሳቸው የግል መክሊት ያላቸው ሰዎችን ያሳተፈ፣ ይበልጥ ሕያው፣ እውነተኛ እና ተጨባጭ በሆነ መንገድ ዝግጅት ከተደረገበት በኋላ የተካሄደ ሲኖዶስ ነው ብሏል።

ዓለም፣ “ከሙታን የተነሳው የክርስቶስ የሕይወትና የተስፋ ምስክር ከእኛ ይጠብቃል” ብሏል።

“ስለዚህ የክርስቶስ ማዕከላዊነት የዚህ ሲኖዶስ መሪ ይሁን። የውይይታችን አልፋና ኦሜጋ ይሁን፣ ክርክራችንን የሚያበራ ብርሃን ይሁን፣ የጥረታችን ሁሉ የመጨረሻ ክፍል ይሁን። ሲኖዶሱ የራሱን ዓላማ እንዲያሳካ እየጸለይኩ ነው ሲሉ አክለው ገልጿል።

05 October 2023, 11:25