ፈልግ

2023.10.25 Sinodo dei Vescovi - XVIII Congregazione Generale

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፡ ቤተክርስቲያንን እንደ እግዚአብሔር ታማኝ ሕዝቦች መኖሪያ አድርጌ ማሰብ እወዳለሁ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ረቡዕ ጥቅምት 14/2016 ዓ.ም ከሰአት በኋላ በጠቅላላ የጳጳሳት ጉባሄ መጀመሪያ ላይ ባደረጉት አስተንትኖ ቤተክርስቲያንን የእግዚአብሔር ታማኝ ሕዝብ መኖሪያ መሆኗን አጉልተው ተናግረዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ቤተክርስቲያንን እንደ እግዚአብሔር ታማኝ ሕዝብ፣ ቅዱሳን እና ኃጢአተኛ፣ የሰዎች ስብስብ እና በማቴዎስ 25 ኃይል ብጹዕት እንድትሆን የተጠራች እንደሆነች ማሰብ እወዳለሁ ሲሉ ተናግረዋል።

ኢየሱስ ለቤተክርስቲያኑ በዘመኑ የነበረውን ማንኛውንም የፖለቲካ እቅድ አልመረጠም፣ ፈሪሳውያን፣ ሰዱቃውያን፣ ኤሴናውያን፣ ወይም ቀናተኛዎችን አልመረጠም። "የተዘጋ ማሕበር" አይደለም፣ “ሕዝቤ ትሆኑኛላችሁ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ” የሚለውን የእስራኤልን ወግ በቀላሉ ኢየሱስ ይወስዳል ሲሉ ተናግረዋል።

ቤተክርስቲያንን ይህች ቀላል እና በጌታ ፊት (ታማኝ የእግዚአብሔር ህዝብ) የምትመላለሰውን ህዝብ አድርጌ ማሰብ እወዳለሁ። የአማኝ ህዝባችን ሃይማኖታዊ ትርጉም ይህ ነው። እናም አማኝ ሕዝቦች እላለሁ የእግዚአብሔር ሕዝብ እውነታ "የሚቀንስባቸው" በብዙ ርዕዮተ ዓለም አቀራረቦች እና እቅዶች ውስጥ እንዳንወድቅ መጠንቀቅ ይኖርብናል። በቀላሉ አማኝ ሕዝቦች  ወይም ደግሞ፣ “የእግዚአብሔር ቅዱስ ታማኝ ሕዝቦች” በመንገድ ላይ በቅድስና እና በኃጢአተኛ መንገድ ላይ የሚጓዙ ሕቦች የሚጓዙበት መንገድ፣ ይህች ቤተ ክርስቲያን ናት ሲሉ ተናግረዋል።

የዚህ ታማኝ ህዝብ አንዱ ባህሪው የማይሳሳት መሆኑ ነው፥ አዎ፣ በእምነት ውስጥ የማይሳሳት ነው። በእምነት አለመሳሳት። እኔም እንዲህ በማለት ገለጽኩላቸው፡- “ቅድስት እናት ቤተክርስቲያን የምታምንበትን ነገር ለማወቅ ስትፈልጉ ወደ አስተምህሮዋ ሂዱ፤ የማስተማር ኃላፊነት ስላለባችሁ ነው። ነገር ግን ቤተክርስቲያን እንዴት እንደምታምን ለማወቅ ስትፈልጉ ወደ አማኝ ሕዝቦች  ሂዱ።

አማኝ ሕዝቦች የእግዚአብሔር ቅዱስ ሕዝቦች፣ ነፍስ አላቸው፣ እናም ስለ የሰዎችን ነፍስ ስለምንናገር የትርጉም፣ የዕውነታ፣ የኅሊና መንገድ መናገር እንችላለን። አማኝ ህዝባችን ክብራቸውን ጠንቅቀው ያውቃሉ፣ ልጆቻቸውን ያስጠምቃሉ፣ ሙታናቸውን ይቀብራሉ።

እኛ የሥልጣን ተዋረድ ያለን አባላት ከዚያ ሕዝብ የመጣን ሲሆን የዚያን ሕዝብ እምነት በአጠቃላይ ከእናቶቻችንና ከአያቶቻችን ተቀብለናል፣ “እናትህና አያትህ” ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ እንደነገረው በሴት የአነጋገር ዘይቤ የተጻፈ እምነት፣ ልክ እንደ የመቃባዊያን እናት ለልጆቿ "በአነጋገር ዘይቤ" የምትናገረውን እናት ይመስላል። እናም እዚህ ላይ በእግዚአብሔር ቅዱሳን እና ታማኝ ሕዝቦች መካከል፣ እምነት የሚተላለፈው በአነጋገር ዘይቤ፣ እና አብዛኛውን ጊዜ በእንስት የቋንቋ ዘይቤ መሆኑን ማስመር እወዳለሁ። ይህ ቤተ ክርስቲያን እናት በመሆኗ ብቻ ሳይሆን በትክክል እሷን የሚያንፀባርቁት በትክክል እንስቶች በመሆናቸው ነው። (ቤተክርስቲያኗ እንስት ናት) ግን ደግሞ መጠበቅን የሚያውቁ፣ የቤተክርስቲያኗን ሀብት እንዴት እንደሚያስገኙ የሚያውቁ፣ ታማኝ ሰዎች፣ ከገደቡ በላይ አልፈው ሂደው ራሳቸውን አደጋ ላይ የሚጥሉ፣ ምናልባትም በፍርሃት ግን በድፍረት እና በብርሃን ውስጥ ያሉ እንስቶች በመሆናቸው ነው፣ እናም ቀኑ በሚጀምረው ብርሃናን እና ጥላ መካከል ህይወት ሊኖር ይችላል ብለው በአእምሮ (ገና ተስፋ ሳያገኙ) ወደ መቃብር ቀረቡ።

የእግዚአብሔር ቅዱስ እና ታማኝ ሕዝቦች እንደ መሆናቸው መጠን ሴት የቤተክርስቲያን ነጸብራቅ ነች። ቤተክርስቲያን ሴት ናት ሚስት ናት እናት ነች።

አገልጋዮች ከአገልግሎታቸው በላይ ርቀው የእግዚአብሔርን ሕዝብ ሲበድሉ ጭካኔ በተሞላበት እና በአምባገነን አመለካከት የቤተ ክርስቲያንን ገጽታ ያበላሻሉ (የሲ/ር ሊሊያና ፍራንኮ ጣልቃ ገብነትን ማስታወስ በቂ ነው)። በአንዳንድ ደብር ቢሮዎች ውስጥ የቅዱስ ምስጢራት አገልግሎት መስጫ ሕሳብ ልክ እንደ በሱፐርማርኬት ውስጥ እንደ ሚደርገው ማለት ነው የ"ዋጋ ዝርዝር" የያዘ ወረቀት ማየት በጣም ያማል። ወይ ቤተክርስትያን በመንገድ ላይ ያለች ታማኝ የእግዚአብሔር ሕዝቦች፣ ቅዱስ እና ኃጢአተኛ ነች፣ ወይም ደግሞ የተለያየ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት እስከመሆን ድረስ ደርሳለች። እናም የቤተክርስቲያን አገልጋይ ይህንን ሁለተኛውን መንገድ ከያዘ ቤተክርስቲያን የድነት ሱፐርማርኬት እና ካህናት የአለም አቀፍ ኩባኒያ ሰራተኞች ይሆናሉ። ይህ ወደ ቄሳዊነት የሚመራን ትልቅ ሽንፈት ነው። እናም ይህ በጣም አሳዛኝ እና አሳፋሪ ነው (በሮማ ውስጥ ወደሚገኙ የቤተ-ክርህነት የልብስ ስፌት ሱቆች መሄድ በቂ ነው ወጣት ካህናት ካባ እና ቆብ ....ወዘተ የተለያዩ ልብሶችን ሲሞክሩ ማየት) አሳፋሪ ነው።

ቀሳውስታዊነት አለንጋ ነው፣ መገረፊያ ነው፣ የጌታን ሙሽራ ፊት የሚያረክስና የሚያበላሽ ዓለማዊነት ነው፤ የእግዚአብሔርን ቅዱሳን እና ታማኝ ሕዝቦችን ባሪያ ያደርጋል።

የእግዚአብሔር ሕዝብ፣ የእግዚአብሔር ቅዱሳን ታማኝ ሕዝብ፣ በትዕግሥትና በትሕትና፣ የቀሳውስታዊነት ተቋማዊ የሃይማኖት ሥርዓት የምያስከትለውን ንቀት፣ እንግልት እና መገለል እየታገሠ ይሄዳል። እናም በተፈጥሮ ስለ ቤተክርስትያን መኳንንት ወይም ስለ ኤጲስ ቆጶሳት ማስተዋወቂያዎች እንደ የስራ እድገት አድርገን እንዴት እንናገራለን! የዓለም አስፈሪ ነገሮች፣ የእግዚአብሔርን ቅዱሳን እና ታማኝ ሕዝቦችን የሚበድል ዓለማዊነት።

ቅዱስ አባታችን ንግግራቸውን በስፓኒሽ ቋንቋ ነበር ያደረጉት።

 

27 October 2023, 17:14