ፈልግ

03-04-2022 Viaggio Apostolico a Malta - Incontro con i Migranti nel Centro Migranti Giovanni XXIII Peace Lab

ር.ሊ.ጳ. ፍራንችስኮስ፡- የሰው ልጅ የስደት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሰሜናዊ ጣሊያን ለሚካሄደው 8ኛው የስደተኞች ፌስቲቫል መልእክት መላካቸው የተገለጸ ሲሆን የቤተክርስቲያን መሪዎች እና ፖለቲከኞች በጉዞ ላይ ያሉ ሰዎችን በመንከባከብ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ህጋዊ የስደት መንገዶችን እንዲያቀርቡ ጋብዘዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

8ኛው የስደተኞች ቀን ፌስቲቫል በጣሊያን በምትገኘው ሞዴና “በነፃነት መጓዝ፣ በነጻነት መኖር” በሚል መሪ ቃል ተጀመረ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጣሊያን ጳጳሳት ጉባኤ የስደተኞች ፋውንዴሽን ባዘጋጀው ዝግጅት ላይ ለተሳተፉት ሰዎች ረቡዕ ጥቅምት 14/2016 መልእክት ልከዋል።

መሪ ቃሉ ለ109ኛው የአለም የስደተኞች እና የጥገኝነት ጠያቂዎች ቀን እ.አ.አ በ2023 ባስተላለፉት መልእክት እና “ለመሰደድ ወይም ለመቀመጥ የመምረጥ ነፃነት” በሚል ርእስ ስር መያዙን ጠቁመዋል።

የሰው ልጅ ማዕከላዊነት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የስደትን ተግዳሮቶች ለማሰላሰል የጉባዔውን አላማ አድንቀዋል፣ “ከአደጋ ጊዜ በላይ ወደ  ገላጭ፣ ዓለም አቀፋዊ እና የረጅም ጊዜ ክስተት ፊት ራሳችንን እንደምናገኝ ግንዛቤ ውስጥ እንድንገባ ያደርገናል” ብለዋል።

አክለውም “በዛሬው እለት ለስደት ተግዳሮቶች የምንሰጣቸው ምላሾች በእኩልነት በደንብ የተገለጹ፣ ዓለም አቀፋዊ እና ረጅም ጊዜ የሚቆዩ መሆን አለባቸው ሲሉ የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በስደት ጉዳይ ላይ የተሳተፉትን ሁሉ “በፖለቲካዊ ውይይቱ ውስጥ የሰው ልጅ ማዕከላዊነት፣ በተለይ ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ እንደ ሴቶች እና ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች ልዩ ትኩረት በመስጠት” እንዲያረጋግጡ ጋብዘዋል።

ለ 2018 የአለም የስደተኞች ቀን ያቀረቡትን መልእክት በማስታወስ "የሰው ልጅ ቀዳሚነት መርህ እና የማይገረሰስ ክብር 'ሁልጊዜ ከብሄራዊ ደህንነት ይልቅ ለግል ደኅንነት ቅድሚያ እንድንሰጥ ያስገድደናል" ብለዋል።

ደህንነቱ የተጠበቀ እና ህጋዊ ስደትን መደገፍ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የቤተክርስቲያን መሪዎች እና ፖለቲከኞች ለአስተማማኝ እና ህጋዊ ስደት የሚጠቅሙ ሀሳቦችን እንዲያቀርቡ አበረታቷቸዋል፣ በህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች እና የተደራጁ ወንጀሎችን ለመዋጋት ሕጋዊ የሆነ የስደት መንገዶችን ማበጀት መልካም ነው ብለዋል።

"እንዲሁም ደህንነታቸው የተጠበቀ መንገዶችን መጠቆም አስፈላጊ ነው" ብሏል። "ይህ ማለት መደበኛ የስደት መንገዶችን ለማስፋት ጥረት መደረግ አለበት ማለት ነው" ሲሉ አክለው የገለጹት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በተጨማሪም በየትኛውም ቦታ ያሉ ወንዶች እና ሴቶች ወደ ስደት ላለመሄድ የመምረጥ መብት ሊኖራቸው እንደሚገባ አስታውሰው መንስኤዎቹን በማስወገድ ለሰዎች ዋስትና ለመስጠት ጥረት እንዲደረግ ጠይቀዋል።

“የጦር መሳሪያ እሽቅድድምን፣ የኢኮኖሚ ቅኝ ግዛትን፣ የሌሎች ሰዎችን ሃብት መዝረፍ እና የጋራ ቤታችን ውድመት ለማስቆም የተቻለንን ጥረት ማድረግ አለብን” ሲሉ ተናግሯል።

25 October 2023, 13:32