ፈልግ

የእስራኤል እና የሐማስ ውጊያ የእስራኤል እና የሐማስ ውጊያ  (AFP or licensors)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የእስራኤል-ሀማስ ጦርነት አብቅቶ ሰላም እንዲሰፍን ተማጽነዋል!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅድስት ሀገር ሰላም እንዲሰፍን ጠይቀው እስራኤል ራሷን የመከላከል መብት እንዳላት ገልጸው፣ ነገር ግን ሁከት በፍትህ ላይ የተገነባ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እንደማይችል አረጋግጠዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ረቡዕ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የጠቃላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ካደረጉ በኋላ በእስራኤል እና በፍልስጤም ውስጥ በሚንቀሳቀሰው እስላማዊ ታጣቂ ድርጅት መካከል ለተነሳው ጦርነት “ሐዘናቸውን እና አሳባቸውን” ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለተገደሉት እና ለተጎዱት ብዙ ሰዎች የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጿል።

"የበዓል ቀን ወደ ሀዘን ቀንነት ተቀይሮ ላዩ ቤተሰቦች እፀልያለሁ እናም ታጋቾቹ በአስቸኳይ እንዲፈቱ እጠይቃለሁ" ብሏል።

አይሁዶች የሲምቻት ቶራ ወይም "የኦሪት ደስታ" በዓልን ሲያከብሩ የሐማስ ታጣቂዎች ቅዳሜ ዕለት በደቡብ የእስራኤል ክፍል ላይ ድንገተኛ ጥቃት ሰነዘሩ።

ሃማስ እስራኤል በገባበት ወቅት በደርዘን የሚቆጠሩ ታጋቾችን የወሰደ ሲሆን እስራኤል በጋዛ ሰርጥ አካባቢ ላይ ጥቃት ካደረሰች ታጋቾቹን እገድላለሁ ሲል ዝቷል።

ብጥብጥ ወደ ሰላም ሊያመራ አይችልም።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በይግባኝ ንግግራቸው "የተጠቁ ሰዎች ራሳቸውን መከላከል መብታቸው ነው" ሲሉ አምነዋል።

ሆኖም “ብዙ ንጹሐን ሰለባዎች ባሉበት በጋዛ ፍልስጤማውያን ላይ የሚደርሰው አጠቃላይ ከበባ” እንዳሳሰባቸው ገልጿል።

እስራኤል የመብራት፣ የምግብ፣ የውሃ እና የጋዝ አቅርቦትን ለመዝጋት የዛተች ሲሆን በጋዛ ላይ “ሙሉ በሙሉ ከበባ” ማደረጉን አስታውቃለች።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሁለቱም ወገኖች ለጦርነቱ መፍትሄ ላይ ለመድረስ ተስፋ በማድረግ እንዲገታ ጋብዘዋል።

"ሽብርተኝነት እና አክራሪነት በእስራኤላውያን እና በፍልስጤማውያን መካከል ላለው ግጭት መፍትሄ ላይ ለመድረስ አይረዱም ነገር ግን ጥላቻን፣ አመጽን እና የበቀል እርምጃን በማቀጣጠል በሁለቱም ወገኖች ላይ መከራን ያስከትላል" ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለመካከለኛው ምስራቅ የሰላም ጥሪ የወንድማማችነት እና የውይይት ጥሪ አቅርበዋል።

"መካከለኛው ምስራቅ ሰላም እንጂ ጦርነት አይፈልግም በፍትህ ላይ የተገነባ ሰላም ውይይት እና የወንድማማችነት ለመገንባት ድፍረት ያስፈልጋል" ብለዋል።

 

12 October 2023, 15:45