ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ በሲኖዶስ የመክፈቻ ስነ-ስረዓት ላይ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እንጓዝ ማለታቸው ተ

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ 16ኛ የጳጳሳት ሲኖዶስ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተካሄደውን መስዋዕተ ቅዳሴ በመምራት ያስጀመሩ ሲሆን በወቅቱ በስፍራው ለተገኙ ምዕመናን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት “በእምነትና በደስታ” እንዲጓዙ ጋብዘዋል። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ሲኖዶስ 16ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ጥቅምት 23/2016 ላይ በተደረገው የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት የተጀመረ ሲሆን የእግዚአብሔርን ጥበቃ እና በረከት ለቤተክርስቲያኗ በመማጸን ነበር ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በይፋ ያስጀመሩት።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን ስብከት ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

አሁን የሰማነው ቅዱስ ወንጌል በኢየሱስ ተልእኮ ውስጥ ስላለው አስቸጋሪ ጊዜ ቀደም ብሎ የተነገረ ነገር ነው፥ እሱም “ሐዋርያዊ ተግዳሮት” ብለን ልንጠራው እንችላለን። መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስ በእርግጥ መሲሕ መሆኑን ተጠራጠረ፣ በጣም በብዙ ከተሞች አልፏል፣  ምንም እንኳን ድንቅ ስራዎች ቢሰሩም መንፈሳዊ ለውጥ ሕዝቡ አላመጣም ነበር፣ ሰዎች ሆዳም እና ሰካራም ብለው ይከሱታል፣ ነገር ግን መጥምቁ በጣም ኮስታራ ስለነበር ቅሬታ ያሰሙ ነበር (ማቴ. 11፡2-24)። ሆኖም ኢየሱስ ራሱን በሐዘን እንዲሸነፍ እንዳልፈቀደ፣ ይልቁንም ዓይኖቹን ወደ ሰማይ አንሥቶ አብን ሲባርክ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር እንዲህ ሲል ለአላዋቂዎች ገልጿል፡- “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፤ ይህን ከጥበበኞችና ከዐዋቂዎች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ” (ማቴ 11፡25)። በሐዘን ጊዜ ኢየሱስ ከዚህ በላይ ማየት የሚችል እይታ አለው፡ የአብን ጥበብ ያወድሳል የማይታየውንም መልካም ነገር ማስተዋል የሚችል የቃሉን ዘር በቅን ልቦና የተቀበለው የመንግሥቱ ብርሃን ነው። በሌሊትም መንገዱን የሚያሳይ የእግዚአብሔር እንደ ሆነ ይናገራል።

ውድ ወንድሞቼ ብፁዕ ካርዲናሎች፣ ወንድሞቼ ጳጳሳት፣ እህቶችና ወንድሞች፣ የሲኖዶሱ ጠቅላላ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ነን። እዚህ ላይ በሰዎች ስልቶች፣ በፖለቲካ ስሌት ወይም በርዕዮተ-ዓለም ጦርነቶች የተዋቀረ ፍፁም የተፈጥሮ እይታ አያስፈልገንም። እኛ የመጣነው የፓርላማ ስብሰባ ወይም የተሃድሶ እቅድ ልናካሂድ አይደለም። አይደለም፣ አብን የሚባርክ እና የደከሙትን እና የተጨቆኑትን የሚቀበል የኢየሱስን እይታ ይዘን አብረን ልንሄድ ነው እዚህ የተሰበሰብነው። ስለዚህ ከኢየሱስ እይታ እንጀምር ይህም የበረከት እና የአቀባበል እይታ ነው።

1. በመጀመሪያ የሚባርክ እይታ ነው። ምንም እንኳን የተጣለበትን እና በዙሪያው ብዙ የልብ መደንደንን አይቶ፣ ክርስቶስ በጭንቀት እንዲታሰር አልፈቀደም፣ አይማረርም፣ ማመስገንን አያቋርጥም፣ በአብ ቀዳሚነት ላይ የተመሰረተው ልቡ በማዕበል ውስጥ እንኳን ጸጥ ይላል።

ይህ የሚባርከው የጌታ እይታ በደስታ ልብ የእግዚአብሔርን ተግባር የምታሰላስል እና የአሁኑን የምታስተውል ቤተክርስቲያን እንድንሆን ይጋብዘናል። እናም በዘመናችን አልፎ አልፎ በተቀሰቀሰው ማዕበል ውስጥ የማይታክተው፣ የርዕዮተ ዓለም ክፍተቶችን የማይፈልግ፣ ከታሰበው አስተሳሰብ ጀርባ የማይገታ፣ ለሚመቹ መፍትሄዎች የማይሰጥ፣ ዓለም አጀንዳውን እንዲወስን የማይፈቅድ ነው። በቅዱስ ዮሐንስ 23ኛ ረጋ ብሎ የተገለጸው የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ጥበብ ይህ ነው፡- “ከሁሉም በፊት ቤተክርስቲያን ቀድሞ ከነበሩ ከአባቶች ከተቀበለችው የእውነት ቅዱስ ርስት ፈጽሞ መለየት የለባትም። ነገር ግን ለካቶሊክ ሐዋሪያት አዲስ መንገዶችን የከፈቱትን አዳዲስ ሁኔታዎችን እና አዳዲስ የሕይወት ዓይነቶችን አሁን ያለውን ሁኔታ መመልከት አለባት” (እ.አ.አ ጥቅምት 11/1962 የሁለተኛው የቫቲካን ጉባሄ የመክፈቻ ስነ-ስረዓት ላይ ካደረጉት ስብከት የተወሰደ)።

የሚባርከው የኢየሱስ እይታ የዛሬን ተግዳሮቶች እና ችግሮች በከፋፋይ እና በክርክር መንፈስ የማትጋፈጠው ነገር ግን በተቃራኒው ዓይኖቿን ኅብረት ወደ ኾነው ወደ እግዚአብሔር የምትመልስ ቤተ ክርስቲያን እንድንሆን ይጋብዘናል እናም በፍርሃትና በትሕትና እርሱን የምትባርክና የምታከብረው ቤተክርስቲያን እንድንሆን ይጋብዘናል። እርሱን ብቸኛ ጌታ መሆኑን በመገንዘብ ማለት ነው። እኛ የእሱ ነን እና - እናስታውስ - የምንኖረው እሱን ወደ ዓለም ለማምጣት ብቻ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደነገረን “ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ክብር የለንም” (ገላ 6፡14)። ይህ ለእኛ በቂ ነው፣ እርሱ በቂያችን ነው። እኛ ምድራዊ ክብር አንፈልግም፣ እኛ እራሳችንን በአለም ፊት ማራኪ ማድረግ አንፈልግም፣ ነገር ግን በወንጌል መጽናናት ወደ እሱ እንድንደርስ፣ የእግዚአብሔርን ወሰን የለሽ ፍቅር በተሻለ መንገድ እና ለሁሉም ለመመስከር ነው። በእርግጥም በነዲክቶስ 16ኛ ከእዚህ ቀደም ለሲኖዶስ ጉባኤ ሲናገሩ “የእኛ ጥያቄዬ ይህ ነው፣ እግዚአብሔር ተናግሯል፣ በእውነትም ታላቅ ዝምታውን ሰበረ፣ ራሱን አሳይቷል፣ ነገር ግን ይህንን እውነታ ዛሬ ለህዝቡ እንዴት እናስተላልፈው? መዳን ይሆን ዘንድ? (እ.አ.አ በጥቅምት 8/2012 ዓ.ም 13ኛው  ጠቅላላ ጉባኤ የጳጳሳት ሲኖዶስ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ካደረጉት አስተንትኖ የተወሰደ) ይህ መሰረታዊ ጥያቄ ነው። እናም ይህ የሲኖዶስ ተቀዳሚ ተግባር ነው፡ ትኩረታችንን በእግዚአብሔር ላይ ማድረግ፣ የሰውን ልጅ በምሕረት የምትመለከት ቤተክርስቲያን መሆን ነው። አንድነቷና ወንድማማችነቷ የምትሰማና የምትወያይ ቤተክርስቲያን የምትባርክ እና የምታበረታታ ቤተክርስቲያን፣ ጌታን የሚሹትን የምትረዳ፣ ግድየለሾችን በፍቅር የምታነቃቃ፣ ሰዎችን ወደ እምነት ውበት ለመሳብ መንገዶችን የምትከፍት መሆን ይኖርባታል። እግዚአብሔር በማዕከሏ ውስጥ ያላት ቤተክርስቲያን በውስጧ አትከፋፈልም፣  በውጪም ጨካኝ አትሆንም። ኢየሱስ ቤተክርስቲያን፣ ሙሽራዋ እንድትሆን የሚፈልገው እንደዚህ ነው።

2. የሚባርከውን እይታ ካሰላሰልን በኋላ፣ አሁን የክርስቶስን የአቀባበል እይታ እንመልከት። ራሳቸውን ጥበበኞች አድርገው የሚያስቡ የእግዚአብሔርን ሥራ ማወቅ ቢያቅታቸውም፣ ኢየሱስ ግን ራሱን ለታናናሾች፣ ለትሁቶች፣ በመንፈስ ድሆች ለሆኑ ሰዎች ስለሚገልጥ በአብ ደስ ይለዋል። ስለዚህ፣ በህይወቱ በሙሉ፣ ወደ ደካማው፣ ወደ ስቃይ እና ወደተጣሉት ይህንን እንግዳ ተቀባይ እይታ ይመለከታል። በተለይ ለእነርሱ፣ የሰማናቸውን ቃላት ሲናገር፡- “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ” (ማቴ 11፡28) ይላቸዋል።

ይህ የኢየሱስ አቀባበል እይታ እንግዳ ተቀባይ ቤተክርስቲያን እንድንሆን ይጋብዘናል። እንደኛ ባለው ውስብስብ ጊዜ ውስጥ ያለ ፍርሃት እርስ በርስ እንድንጋፈጥ ሞቅ ያለ እና ደግነት የተሞላበት ውስጣዊ አመለካከት የሚጠይቁ አዳዲስ ባህላዊ እና ሐዋርያዊ ተግዳሮቶች ይፈጠራሉ። በሲኖዶሳዊ ውይይት፣ በዚህ ውብ “በመንፈስ ቅዱስ ጉዞ” እንደ እግዚአብሔር ሕዝብ አብረን እያደረግን ያለነው፣ የዛሬን ፈተናዎች በአይናችን ለማየት ከጌታ ጋር በአንድነትና በወዳጅነት ማደግ እንችላለን። በመሆኑም የቅዱስ ጳውሎስ ስድስተኛን ጥሩ አገላለጽ በመጠቀም፣ “ራሷን ለንግግር ክፍት ያደረግች” ቤተክርስቲያን መሆን ይኖርባታል።  “ቀንበሯ ልዝብ የሆነ ቤተክርስቲያን” (ማቴ. 11፡30)፣ ሸክም የማትጭን “እናንተ ደካሞችና ተጨቋኞች ኑ፣ መንገዳችሁን የጠፋችሁ ወይም የራቃችሁ ኑ። ተስፋ ለማድረግ በሮችን የዘጋችሁ ኑ፡ ቤተክርስቲያን ለናንተ መጥታለች!"

3. ወንድሞች እና እህቶች፣ ቅዱሳን የእግዚአብሔር ሰዎች፣ ከፊት ለሚጠብቀን ችግሮች እና ተግዳሮቶች፣ የኢየሱስ በረከት እና የአቀባበል እይታ ወደ አንዳንድ አደገኛ ፈተናዎች እንዳንወድቅ ያደርገናል፡ ግትር የሆነች ቤተክርስቲያን እንዳትሆን፣ እራሷን ከዓለም ተጻራሪ በሆነ መልኩ የምታስታጥቅ እና ለዓለም ፋሽኖች እጅ የምትሰጥ ለብ ያለች ቤተ ክርስቲያን፣ የደከመች ቤተክርስቲያን ትሆናለች ማለት ነው።

ትሁት፣ ቀናተኛ እና ደስተኛ በሆነ መልኩ አብረን እንራመድ። በአሲዚው ቅዱስ ፍራንችስኮስ የድህነት እና የሰላም ቅዱስ ጋር አብረን በመጓዝ “የእግዚአብሔር ሞኝነት” በሰውነቱ ላይ የኢየሱስን የስቃይ ምልክት የተሸከመውን እና እርሱን ለመልበስ ሲል ሁሉንም ነገር ከእራሱ ያራቀውን የእርሱን ፈለግ እንከተል።  ቅዱስ ቦናቬንቸር ሲጸልይ ሳለ፣ የተሰቀለው ኢየሱስ “ሂድና ቤተ ክርስቲያኔን ጠግን” እንዳለው ገልጿል። ሲኖዶሱ ይህንን ለማስታወስ ይጠቅመናል፡ እናታችን ቤተክርስቲያናችን ሁል ጊዜ የመንጻት፣ "መጠገን" ትፈልጋለች። ወንጌሉን ለሁሉም ለማዳረስ እራሳችንን ወደ መንፈስ መንገድ እንመለሳለን። የአዚዚው ቅዱስ ፍራንችስኮስ በታላቅ ችግርና መከፋፈል፣ በጊዜያዊ እና በሃይማኖታዊ ኃይሎች መካከል፣ በተቋማት ቤተ ክርስቲያን እና በመናፍቃን ሞገድ መካከል፣ በክርስቲያኖች እና በሌሎች አማኞች መካከል፣ ማንንም አልነቀፈም ወይም አልዘነፈም። የወንጌልን ትጥቅ ብቻ ወሰደ ትህትና እና አንድነት፣ ጸሎት እና ልግስና። እኛም እንዲሁ እናድርግ!

የእግዚአብሔር ቅዱሳን ሕዝቦች በዓለም ውስጥ ከሚገኙት እረኞቻቸው ጋር እየጀመርነው ስላለው ሲኖዶስ የሚጠብቁት፣ ተስፋ አልፎ ተርፎም አንዳንድ ፍርሃቶች ካላቸው፣ በመንፈስ የተደረገ ጉባኤ እንጂ የፖለቲካ ስብሰባ አለመሆኑን እናስታውስ፣ ዋልታ ረገጥ የሆነ ፓርላማ ሳይሆን የጸጋና የኅብረት ቦታ ነው። መንፈስ ቅዱስ ከትንቢታችን እና ከአሉታዊነታችን በላይ የሆነ አዲስ ነገር ለመፍጠር ብዙ ጊዜ የምናደርገውን ጥረት የምንጠብቀውን ነገር ብትንትኑን ያወጣል። ለእርሱ ራሳችንን እንከፍት እና እርሱን ዋና ገፀ ባህሪ የሆነውን መንፈስ ቅዱስን እንጥራው። በእርሱም በመታመንና በደስታ እንመላለስ።

 

04 October 2023, 16:30