ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የመልአከ እግዚአብሔር በመምራት ላይ ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የመልአከ እግዚአብሔር በመምራት ላይ   (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፥ ከዓለም ሕጻናት ጋር በቅርቡ እንደሚገናኙ አስታወቁ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመጭው ኅዳር ወር ከአምስቱም አህጉራት ሕጻናት ጋር ለመገናኘት እቅድ እንዳላቸው ገለጸዋል። የግንኑነታቸው ዓላማም ሕጻናቱ ለሌሎች ካላቸው ተቀባይነት እና ለፍጥረት ከሚሰጡት ክብር ለመማር እንደሆነ ተናግረዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ለማቅረብ መስከረም 20/2016 ዓ. ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተሰበሰቡት ምዕመናን ጋር ከፍ ብሎ ከሚገኝ የሐዋርያዊ ሕንጻ መስኮት በኩል የታዩት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፥ ሰኞ ጥቅምት 26/2016 ዓ. ም. ከሰዓት በኋላ፥ “ከወንድ እና ከሴት አዳጊ ሕጻናት እንማር” በሚል መሪ ርዕሥ በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ሕጻናት ጋር እንደሚገናኙ አስታውቀዋል።

“ዛሬ አምስቱን አህጉራት የሚወክሉ አምስት ሕጻናት ከአጠገቤ ይገኛሉ” ያሉት ቅዱስነታቸው፥ በቫቲካን በሚገኘው ጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ውስጥ ጥቅምት 26/2016 ዓ. ም. ከሰዓት በኋላ በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ሕጻናት ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ መያዛቸውን ተናግረዋል።

ከወንድ እና ከሴት ሕጻናት እንማር

ዝግጅቱን ያስተባበረው በቅድስት መንበር የባህል እና የትምህርት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት እንደሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው፥ “ከወንድ እና ከሴት ሕጻናት እንማር” በሚል መሪ ሃሳብ ላይ በማትኮር፥ በጋራ ሕልም ላይ ለማሰላሰል መልካም አጋጣሚ እንደሚሆን ገልጸው፥ ይህ መሪ ሃሳብ ወደ ንፁህ የልጅነት ስሜት የመመለስ ፍላጎት እንዳለ የሚያሳይ መሆኑ በማከል፥ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ ሕፃናት ላሉት እንደሆነ አስረድተዋል።

ልጆች በንጹህ ግንኙነታቸው፥ እንግዳን በድንገት መቀበልን እና ፍጥረትን ማክበርን እንደሚያስተምሩ በመናገር፥ "የተወደዳችሁ ልጆች ሆይ! እኔም ከእናንተ መማር እመኛለሁ" ብለዋል።

 

02 October 2023, 17:45