ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ለ21 የቤተ ክርስቲያን አባቶች የካርዲናልነት ማዕረግ በሰጡበት ወቅት ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ለ21 የቤተ ክርስቲያን አባቶች የካርዲናልነት ማዕረግ በሰጡበት ወቅት  (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

ር. ሊ. ጳ. ፍራችስኮስ አዲሶቹ ካርዲናሎች በሲኖዶሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በጋራ እንዲሠሩ አሳሰቡ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፥ ቅዳሜ መስከረም 19/2016 ዓ. ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በተካሄደው መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት ላይ ለ21 የቤተ ክርስቲያን አባቶች የካርዲናልነት ማዕረግ ሰጥተዋል። በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባሰሙት ስብከትም፥ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት በማስታወስ አዲስ የተሾሙት ካርዲናሎች በሲኖዶሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአንድነት እንዲሠሩ በማሳሰብ፥ የኅብረት ጉዞ አስተማሪ በሆነው መንፈስ ቅዱስ የሚመራ የሲኖዶስ አስፈላጊነትን ተናግረዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የካርዲናሎች አንድነት የቤተ ክርስቲያንን ሲኖዶሳዊነት እንደሚገልጽ ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ቅዳሜ መስከረም 19/2016 ዓ. ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በተካሄደው ሥነ-ሥርዓት ለ21 የቤተ ክርስቲያን አባቶች የካርዲናልነት ማዕረግ በሰጡበት ወቅት ተናግረዋል።

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፥ ለቤተ ክርስቲያን አባቶች የካርዲናልነት ማዕረግ በሰጡበት ወቅት
ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፥ ለቤተ ክርስቲያን አባቶች የካርዲናልነት ማዕረግ በሰጡበት ወቅት

በአንዲት እና ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለው ልዩነት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አዲስ የተሾሙ 19 ሊቀ ጳጳሳትን፣ ጳጳሳትን እና 2 ካህናትን ጨምሮ ለመላው የካርዲናሎች ኅብረት ባሰሙት ስብከት፥ በሐዋርያት ሥራ ምዕ. 2:1-11 ላይ እንደተጻፈው፥ ሐዋርያት ከመንፈስ ቅዱስ በተቀበሉት ስጦታ በልሳን እየተናገሩ ከተለያየ አገራት ወደ ኢየሩሳሌም ለመጡት አይሁዶች ወንጌልን እንደሰበኩ እና እንደ አይሁዳውያኑ የዘመናችን ጳጳሳት እና ካርዲናሎችም ከዓለም ዙሪያ ከተለያዩ አገራት የመጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በተለምዶ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ከሐዋርያት ጋር የሚያመሳስላቸው የተለየ አመለካከት እንዳለ የገለጹት ቅዱስነታቸው፥ የወንጌል መልካም ዜና የተሰበከላቸው የኢየሩሳሌም ሕዝቦች የድነትን ምሥጢር የተቀበሉት ሁሉንም ቋንቋዎች የምትናገር የሁላዊት ቤተ ክርስቲያን አካል መሆናቸውን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አስረድተዋል።

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ለቤት ክርስቲያን አባቶች የካርዲናልነት ማዕረግ በሰጡበት ወቅት
ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ለቤት ክርስቲያን አባቶች የካርዲናልነት ማዕረግ በሰጡበት ወቅት

በራስ ቋንቋ የወንጌል ምስክርነትን የመስማት ስጦታ

በኢየሩሳሌም የወንጌል መልካም ዜና የተበሰረላቸው ሰዎች፥ ሐዋርያት፣ ካህናት፣ ጳጳሳት፣ ካርዲናሎች እና የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ከመሆናቸው በፊት ከዘመናዊው የኢራን ግዛት የጳርቴና፣ የሜድ እና የኢላሜጤም የመጡ መሆናቸውን በማስታወስ፥ ወደ ክርስትና የተመለሱት አይሁዶች የወንጌልን ጸጋ ያገኙት በራሳቸው ቋንቋ ከአያቶቻቸው፣ ከወላጆቻቸው፣ ከትምህርተ ክርስቲያን መምህራን፣  ከካህናት እና ከገዳማዊያን በመሆኑ ሊያመሰግኑ ይገባል ብለዋል።

ወንጌልን በልባችን ውስጥ እየተንከባከብን አድናቆትን እና ምስጋናን ማቅረብ እንደሚገባ፥ ይህም ሁል ጊዜ የሚገኝ ስጦታ መሆኑን በማስታወስ እምነት ያለማቋረጥ መታደስ ይኖርበታል ብለዋል። የሞተውንና ከሞት የተነሣውን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሥጢር ለሕዝቦች የመመስከር አስደናቂ ሥራ በመንፈስ ቅዱስ እንደተካሄደ እና ይህም ለእኛ የተነገረን በራሳችን ቋንቋ መሆኑን ገልጸው፥ እምነትን ወደ ሌሎች ማስተላለፍ የሚቻለው በእናቶች እና በአያቶች ቋንቋ መሆኑን አስረተዋል።

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ለቤተ ክርስቲያን አባቶች የካርዲናልነት ማዕረግ በሰጡበት ወቅት
ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ለቤተ ክርስቲያን አባቶች የካርዲናልነት ማዕረግ በሰጡበት ወቅት

በዓለ ሃምሳ ያለፈ ክስተት ሳይሆን ነገር ግን እግዚአብሔር ሳያቋርጥ ዘወትር የሚያድሰው ተግባር እንደሆነ፥ ቤተ ክርስቲያን እና እያንዳንዱ የተጠመቀ አባል ዛሬን የሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ እገዛ መሆኑን ተናግረዋል። የቤተ ክርስቲያን ማዕረግ የተቀበሉት ካርዲናሎች አዲሱ ሥራቸው በቤተ ክርስቲያን እና ለቤተ ክርስቲያን ያላቸውን ጥሪ እና ተልዕኮ እንደሚያድስላቸው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ  አስታውሰዋል።

የበለጠ አንድ እና ሲኖዶሳዊት ለሆነች ቤተ ክርስቲያን መሥራት

ተልዕኮን፥ በተመሳሳይ ጊዜ ልዩነትን እና አንድነትን ከያዘ የኦርኬስትራ ድምጽ ጋር ያመሳሰሉት ቅዱስነታቸው፥ ተልዕኮ የቤተ ክርስቲያን ስምምነት እና ሲኖዶሳዊነት የሚወክል እንደሆነ አብራርተዋል።

“ልዩነት አስፈላጊ እና የማይቀር ነው” ያሉት ቅዱስነታቸው፥ እያንዳንዱ የኦርኬስትራ ድምጽ ለጋራ ንድፍ አስተዋፅኦ ማድረግ እንዳለበት እና የጋራ መደማመጥ አስፈላጊ የሆነበት ምክንያትም ለዚህ እንደሆነ ገልጸው፥ የኦርኬስትራ መሪ እያንዳንዱ ሙዚቀኛ እና መላው የኦርኬስትራ አባላት ታላቅ የፈጠራ ብቃታቸውን እንዲያዳብሩ ለመርዳት የተጠራ መሆኑን አስረድተዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ስብከታቸውን ሲያጠቃልሉ፥ ሲኖዶሳዊት በሆነች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንድነትን በሚፈጥር በመንፈስ ቅዱስ በመመራት፥ የካርዲናሎች ኅብረት ሲኖዶሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ለመገንባት እንዲሠሩ ጥሪያቸውን አቅርበው፥ “እራሳችንን ለመንፈስ ቅዱስ ጠንካራ መሪነት እና ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንክብካቤ አደራ እንሰጣለን” ብለዋል።

 

30 September 2023, 23:32