ፈልግ

2023.09.06 locandina Building Bridges

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ "ድልድይ መገንባት” በሚል አርዕስት የሚከናወነውን ውይይት ሊያስተናግዱ ነው ተባለ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንችስኮስ ከደቡብ እስያ የተውጣጡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በሚያገናኝ "ድልድይ መገንባት” በሚል መሪ ቃል እና ተነሳሽነት ለሦስተኛ ጊዜ በበይነ መረብ በሚከናወነው ስብሰባ ላይ ሊሳተፉ መሆናቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

"ድልድይ መገንባት" በሚል መሪ ቃል እና ተነሳሽነት በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እና በደቡብ እስያ በሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል በበይነ መረብ የሚያደርጉት ስብሰባ ሊቀጥል ነው።

ሦስተኛው የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአህጉሪቱ ካሉ ወጣቶች ጋር የሚያደርጉት ውይይት እ.አ.አ በመስከረም  26/2023 ከሰአት በኋላ ይካሄዳል።

ስብሰባው "በደቡብ እስያ በኩል ያሉ ድልድዮችን መገንባት" የሚል መለያ ተሰጥቶታል፣ እናም በቺካጎ በሚገኘው በሎዮላ ዩኒቨርሲቲ የዓለማቀፍ እና የማህበረሰብ ተሳትፎ ጽህፈት ቤት የላቲን አሜሪካ ጳጳሳዊ ኮሚሽን እና የሐዋርያዊ ጥናት ተቋም "ድልድይ መገንባት" በሚል መሪ ቃል እና ተነሳሽነት የሚካሄደው ስብሰባ ስፖንሰር ተደርጓል።

ሲኖዶሳዊ ቤተ ክርስቲያን መገንባት

የስብሰባው ዋና ግብ ጳጳሱ የበለጠ ሲኖዶሳዊ ቤተክርስቲያን እንድትሆኑ ላቀረቡት ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ነው።

ዝግጅቱ ቀደም ብሎ እ.አ.አ በየካቲት 24 እና ሕዳር 1/2022 በጳጳሱ፣ በአሜሪካ እና ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ተማሪዎች መካከል የተደረጉትን ሁለት ስብሰባዎች ተከትሎ የሚካሄድ ሦስተኛው በበይነ መረብ የሚካሄድ ስብሰባ ነው።

በዚህ ጊዜ ከተለያዩ የደቡብ እስያ አካባቢዎች የመጡ ወጣት ተማሪዎች ተራ ነው። ዝግጅቱ በቀጥታ በዩቲዩብ ይለቀቃል እና በሶስት ቋንቋዎች እንግሊዘኛ፣ ስፓኒሽ እና ሂንዲ ቋንቋዎች ይካሄዳል።

በትላልቅ ጭብጦች ላይ የሚያሰላስሉ ትናንሽ ቡድኖች

በበይነ በመረብ ስብሰባ ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች ከፓኪስታን እስከ ህንድ እስከ ኔፓል ባሉ ሀገራት ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች የተውጣጡ ይሆናሉ።

ተማሪዎቹ ከሳይኮሎጂ፣ ከኮምፒዩተር ሳይንስ፣ ፊዚክስ እና ኢኮኖሚክስ እና ከሌሎችም ጨምሮ ከተለያዩ የትምህርት ክፍል ዳራዎች የተውጣጡ ናቸው።

በክልላቸው ውስጥ ባሉ የጋራ ማህበራዊ ችግሮች ላይ በወያየት እና በማስተዋል በማዳመጥ በ12 ትናንሽ ቡድኖች ተከፋፍለው ነው በበይነ መረብ የሚከናወነውን ስብሰባ የሚካፈሉት።  

“ወደ ማይጠቅምና ፍሬያማ ወደ አልሆነ ውይይቶች እንዳይወርዱ” ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ራሳቸው እንደ ሲኖዶሳዊ መስተጋብር ዘዴ "እንዲገናኙ፣ እንዲያዳምጡ እና በማስተዋል ጥበብ የተሞላ አስተውሎት እንዲያሳዩ ተሳታፍዎችን ጋብዟል።

እ.አ.አ ማክሰኞ መስከረም 26/2023 ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር በሚያደርጉት የበይነ መረብ ስብሰባ የእያንዳንዱ ቡድን ተወካዮች እንደ ቃል አቀባይ ሆነው ያገለግላሉ።

ተስፋን ማዕከል ያደረገ ሲኖዶሳዊ ቤተክርስቲያን

የ‹‹ድልድይ ግንባታ›› መነሻ ዓላማው የሚያጠነጥነው ብዙውን ጊዜ የተለያዩ ሕዝቦችና ባህሎችን ከሚለያዩት የመለያያ ነጥቦች በመነሳት ሲሆን፣ እነዚህን ክፍተቶች “የእምነት ድልድዮችን በመገንባት” ለማሸነፍ ታቅዶ ለሦስተኛ ጊዜ የሚከናወን ስብሰባ ነው።

ይህ የጋራ የልምድ ልውውጦችን ማጎልበት፣ የአስተያየት ጥቆማዎችን መጋራት እና ለጋራ ዓለም አቀፋዊ ዓላማዎች በሚያበረክቱት በአሁኑ እና ወደፊት በሚደረጉ ጥረቶች ላይ መተባበርን፣ እንደ የአካባቢ ዘላቂነት፣ ኢኮኖሚያዊ ፍትህ እና አጠቃላይ የሰው ልጅ ልማትን ያካትታል።

የበይነ መረብ የስብሰባ ይዞታ እና አቀራረብ በመልካምድራዊ ምክንያቶች ርቀው የሚገኙ ክልሎችን አንድ ለማድረግ ያስችላል፣ የተለያዩ የተገለሉ ማህበረሰቦችን እንደ ሥራ አጥነት፣ ድህነት እና ብጥብጥ ያሉ ተግዳሮቶችን የሚጋፈጡ ሰዎችን በአንድ ላይ ለማሰባሰብ ያስችላል።

ይህ በእነዚህ ማህበረሰቦች ውስጥ ያሉ ሰዎች ድምፃቸው የሚሰማበት እና ራዕያቸውን እና ተስፋቸውን ለአለም የሚያቀርቡበት አዲስ የነፃነት ቦታዎችን እንዲለማመዱ ያስችላቸዋል።

 

07 September 2023, 13:09