ፈልግ

የቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ ባዚሊካ የቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ ባዚሊካ  

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የብርቱ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ትንቢታዊ ሥራ አወድሰዋል!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከ26ኛው የጳውሎስ ለክርስቲያን ሕብረት በምሁራን የሚደርገው ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች ጋር ተገናኝተው የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት በአምላክ ተስፋዎች ላይ እምነት እንዲኖራቸው አሳስበዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የቅዱስ ጳውሎስን ቅዱሳት መልእክቶች ለመከታተል የወሰኑትን የሊቃውንት ቡድን ሥራ አወድሰው “ታላቅ አስተዋጽዖ” ሊባል የሚችለው በመካከላቸው የተለያዩ ቢሆኑም በጳውሎስ ትምህርት ጥበብ አንድነት ባላቸው ክርስቲያኖች መካከል ያለው ግንኙነት ነው” ሲሉ አስረድተዋል።

ቅዱስ አባታችን ለ26ኛው የጳውሎስ ለክርስቲያን ሕብረት በምሁራን የሚደርገው ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች ባደረጉት ንግግር፣ “የሐዋርያው መልእክት ውበት እና ለክርስቲያናዊ እና ለቤተክርስቲያን ሕይወት ያላቸው ጠቀሜታ” እንዲወጣ የሚያስችለውን “ጠንካራ እና ምሁራዊ የትርጓሜ ልውውጥ” በምሁራን መካከል ግንኙነት እጅግ የላቀ ጠቀሜታ እንዳለው አጽንዖት ሰጥተው ተናግሯል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ለተሳታፊዎች ንግግር ሲያደርጉ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ለተሳታፊዎች ንግግር ሲያደርጉ

ደፋር እና ትንቢታዊ ተነሳሽነት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ተነሳሽነቱ "የመከላከያ እንቅፋቶችን" ለማሸነፍ ደፋር እንድንሆን እንደ ሚርዳን ገልፀዋል፣ እናም "ጤናማ 'የመንፈስ ትዕግሥት ማጣት'" ለአንድነት ሙላት እና ለመመሥከር ቁርጠኝነትን በማስተዋወቅ ረገድ ትንቢታዊ ነው ብሏል።

“በታሪክ ዘመናት ሁሉ መለያየቶች የመከራ ምንጭ ከሆኑ ዛሬ ራሳችን በመጸለይ፣ በመማር እና በጋራ በመስራት በአንድነትና በወንድማማችነት ጎዳና ላይ ለመጓዝ ራሳችንን መስጠት አለብን” ብሏል።

እግዚአብሔር የገባውን ቃል ከሟሟላት አይታክትም

የምሁራዊው ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕራፍ 9-11 እያተኮሩ መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሮሜ 11፡29 የተገለጹትን “የማይሻሩ” ስጦታዎችን እና የእግዚአብሔርን ጥሪ አጉልተዋል።

እዚህ ላይ ቅዱስ ጳውሎስ “እግዚአብሔር የማዳን ተስፋውን አይስትም እናም በሚያስደንቅ ሁኔታም እንኳ በትዕግሥት ይፈጽማል” የሚለውን መሠረታዊ ጠቃሚ መልእክት አስረክቦናል ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንዳሉት ከሆነ ለምሁራዊ ሥራ የሚያደርጉት ድጋፍ “በእግዚአብሔር ምሕረት እና ተስፋዎች” ላይ ባለን እምነት መሠረት ላይ ነው ያሉ ሲሆን የወንድማማችነትና የምሁራዊ ውይይታቸውን እንዲቀጥሉ ሲያበረታቷቸውም “ከሁሉም በላይ” ለክርስቲያን ማህበረሰቦች 'አዲስ ቃላትን' ለመስጠት በጳውሎስ መልእክቶች ውስጥ በተካተቱት ስፍር ቁጥር በሌላቸው መንፈሳዊ ሀብቶች እንዲደነቁ ጋብዟቸዋል። የአብን መሐሪ ቸርነት፣ የክርስቶስን አዲስ የመዳን እና የመንፈስን የመታደስ ተስፋን ማሳወቅ የሚችላው በእዚሁ መልኩ ነው ሲሉ አክለው ገልጿል።

“ጌታን ለመፈለግ ለጋራ ጉዟችን” አጋዥ በመሆኑ ሥራቸው በአማኞች መካከል ያለውን “የተዋሕዶ መንፈስ” እንደሚያሳድግ ተስፋ በማድረግ ደምድሟል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከ26ኛው የጳውሎስ ለክርስቲያን ሕብረት በምሁራን ጋር
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከ26ኛው የጳውሎስ ለክርስቲያን ሕብረት በምሁራን ጋር
15 September 2023, 11:36