ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ባለፈው ሐሙስ በቫቲካን ከንጉሥ ፊሊፕ እና ከቤልጂየም ንግሥት ማቲልዴ በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ባለፈው ሐሙስ በቫቲካን ከንጉሥ ፊሊፕ እና ከቤልጂየም ንግሥት ማቲልዴ በተገናኙበት ወቅት   (Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከቤልጂየም ንጉሥ ፊሊፕ እና ንግሥት ማቲልዴ ጋር ተገናኙ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ባለፈው ሐሙስ በቫቲካን ከንጉሥ ፊሊፕ እና ከቤልጂየም ንግሥት ማቲልዴ ጋር ባደረጉት ውይይት ውስጥ የክርስትና እምነት እና የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሚና እና የዩክሬን ጦርነት እንደ ሚገኝበት ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሐሙስ እለት ጠዋት የቤልጂየም ንጉስ ፊሊፕ እና ንግሥት ማቲልዴ በቫቲካን መቀበላቸውን የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት መግለጫ አስታወቀ።

ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የተገኙትን ታዳሚዎች ተከትሎ፣ የቤልጂየም ንጉሥ እና ንግሥት ያድረጉትን ግንኙነት በተመለከተ ቫቲካን ከሌሎች አገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን ግንኙነት በበላይነት የሚከታተለው የቅድስት መንበር ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ካርዲናል ፖል ሪቻርድ ጋላገርን ስለግንኙነቱ መግለጫ መስጠታቸው ተገልጿል።

በስብሰባው ወቅት መግለጫው “በቅድስት መንበር እና በቤልጂየም መካከል ባለው መልካም ግንኙነት የክርስትና እምነት እና የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሚና በማሳየት እርካታ ታይቷል” ብሏል።

ውይይቶቹ በዋናነት በጋራ ጉዳዮች እና በአንዳንድ አለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ሲሆን በተለይም አፍሪካን በተመለከተ በዩክሬን ያለውን ጦርነት እና በህዝቦች መካከል ሰላም እንዲሰፍን ቁርጠኝነትን በማሳየት ላይ ያተኮረ ነበር።

የቤልጂየም ንጉሣዊ ቤተሰብ እ.ኤ.አ. ታኅሣሥ 31 ቀን 2022 ከዚህ ዓለም በሞት በተለዩት የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት ወደ ቫቲካን በጥር ወር መጀመሪያ ላይ መገኘታቸው ይታወሳል።

15 September 2023, 11:55