ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ወደ ሞንጎሊያ ያደረጉትን ሐዋርያዊ ጉዞ አጠናቀቁ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከነሐሴ 25-29/2015 በሞንጎሊያ አድርገውት ነበረውን 43ኛው ዓለም አቀፍ ሐርያዊ ጉብኝት ሲያጠናቅቁ፥ ወደ አገሪቱ አብሮ አቸው ከተጓዙት እንግዶች ጋር ከኡላንባታር ቺንግጊስ ካን ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመነሳት ወደ ሮም በመመለስ ላይ እንደሚገኙ ተልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሞንጎሊያ ያደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት እንዳበቃ ወደ ሮም በመመለስ ላይ እንደሚገኝ ከደረሰን ዜና ለመረዳት ተችሏል። በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ሰኞ አመሻሹ ላይ ወደ 12:30 አከባቢ ሮም ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የምስጋና ስጦታዎች

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመጨረሻው ቀን በሞንጎሊያ ሐዋርያዊ ጽሕፈት ቤት ውስጥ በግላቸው የመስዋዕተ ቅዳሴ ሰሎት ማሳረጋቸው የተገለጸ ሲሆን፥ በጉብኝታቸው ጊዜ ሁሉ አብረዋቸው ለተጓዙ እና ይህ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው የተሳካ እንዲሆን አስተዋጾ ላበረከቱት የኡላንባታር ሐዋርያዊ አስተዳዳሪ እንደራሴ ለብፁዕ ካርዲናል ጆርጂዮ ማሬንጎ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት የሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፥ ቅዱስነታቸው በሞንጎሊያ ለቅድስት መንበር እንደራሴ የቅዱስ ዮሴፍን ሐውልት በስጦታ መልክ ያቀረቡ ሲሆን፥ ምስሉም ቅዱሱን ዝምተኛውን የጌታችን ጠባቂ አድርጎ ያሳያል። "ቅዱስ ዮሴፍ በግራ እጁ ትንሹን የዓለም መድህን በበረከት ደግፎታል፣ በቀኝ እጁ ደግሞ በአዋልድ መጻሕፍት መሠረት የኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ካህናት ሊቃወሙ በሚችሉበት ጊዜ በተአምራዊ ሁኔታ አበቦች ያበበውን በትር መያዙን ያሳያል።

የእግዚአብሔር ምሕረት መግለጫ

ቅዱስነታቸው በሞንጎሊያ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው መጨረሻ ላይ በቤተ ክርስቲያን የሚመራ እና ለድሆች ክሊኒክ፣ የቤት ውስጥ ጥቃት ሰለባ ለሆኑ እና መጠለያ አልባ ለሆኑት ሰዎች ማደሪያ እና "የምሕረት ቤት" የተሰኘውን የበጎ አድርጎት ተቋምን መርቀው ከፍተዋል። ቅዱስነታቸው የበጎ አድራጎት ሥራ ተቋምን መርቀው እና ባርከው የከፈቱት ሲሆን፥ በሞንጎሊያ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በኢኮኖሚያዊ ችግር እና መገለል ለሚደርስባቸው ሰዎች ትልቅ እንክብካቤን እና አሳቢነትን ላሳየች ቤተ ክርስቲያን ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

04 September 2023, 19:25