ፈልግ

የጣሊያን መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር አባላት ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በተገናኙበት ወቅት የጣሊያን መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር አባላት ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በተገናኙበት ወቅት   (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔርን ቃል መመገብ አለባቸው አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከጣሊያን የመጽሐፍ ቅዱስ ማህበር አባላት እና በኢጣሊያ ብሔራዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ሳምንት ተሳታፊዎች ጋር ተገናኝተው ቤተክርስቲያን ምእመናን በቃሉ ወደ እግዚአብሔር እንዲቀርቡ እንድትረዳቸው ጠይቀዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ምእመናንን የእግዚአብሔር ቃል እንዲመገቡ እርዷቸው፣ በተለይም በዚህ ወሳኝ ወቅት፣ ሁሉም ቅዱሳት መጻሕፍትን ለማስፋፋት በጋራ መሥራት አለባቸው ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህንን ማበረታቻ የሰጡት የጣሊያን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማህበር አባላትን እና የቅዱሳት መጻሕፍት ፕሮፌሰሮችን ተቀብለው በቫቲካን ካስተናገዱ በኋላ በኢጣሊያ 47ኛው ብሄራዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ሳምንት ላይ በሮም ለተሰበሰቡት አባላት ንግግር ባደረጉበት ወቅት ሲሆን  የዘንድሮው መሪ ቃል “ቃል ኪዳን፣ አለማቀፋዊነት እና ልዩነት” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው ስብሰባ ላይ እየተሳተፉ ካሉ ሰዎች ጋር ተገናኝተዋል።

"ውድ ጓደኞቼ፣ መጽሐፍ ቅዱስ የሁሉ ውርስ ይሆን ዘንድ ለመሥራት ውጡ፣ የእግዚአብሔር ህዝብ ከቃሉ እንዲመገቡ በመርዳት በተልእኮአችሁ ቀጥሉ” ብሏል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ።

መጽሐፍ ቅዱስ “የእግዚአብሔር ሕዝብ መጽሐፍ ነው፣ እርሱን ሰምቶ ከመበታተንና ከመከፋፈል ወደ አንድነት የሚሻገር ነው” በማለት አጥብቆ የተናገሩት ቅዱስነታቸው “ይህ በመጠኑም ቢሆን፣ ሁልጊዜም የጌታ ኃይል ነው፤ እርሱ ይልከናል፣ ከዚያም በኋላ በአንድነት ይሰበስባበናል ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከጣሊያን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማህበር አባላት ጋር ተገናኙ

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደ ተናገሩት የዘንድሮው መሪ ቃል ለልባቸው የቀረበ እና የቤተክርስቲያኒቱ ዋነኛ ጉዳይ እንደሆነ ገልጸው፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከወቅታዊው ዓለም ጋር ያላትን ግንኙነት በቅርበት የሚያካትት ቃል ኪዳኖችን በመመርመር አመስግነዋል።

በቃሉ አገልግሎት በጋራ መስራት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ስብሰባቸው አጽንዖት እንዲሰጥ የፈለጉትን ሌላ እሴት እንደፈጠረ ጠቁመው፣ “በቃሉ አገልግሎት ተባብሮ መሥራት” ያስፈልጋል ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር በጣሊያን ለምትገኘው ቤተ ክርስቲያን በቋሚነት የሚያቀርበውን ሰፊ የትብብር ሥራ ማዕከል መሆኑን አመስግነዋል።

ድርጅቱ በአገሪቱ ከመጀመሪያዎቹ የነገረ መለኮት ማኅበራት አንዱ እንደነበርና አሁንም በተለያዩ አህጉረ ስብከት ውስጥ በተለይም በሀገረ ስብከቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ሳምንታት እንቅስቃሴ አማካኝነት ከጣሊያን ጳጳሳት ጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ሐዋርያ ጋር መተባበር እንደሚደግፈው አስታውሰዋል።

"እኔ ተስፋ አደርጋለሁ" ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "ይህ መገኘት በግዛቱ ውስጥ እያደገ፣ ሁሉንም ዓይነት ቁንጮ የመሆን ፍላጎት እና ጉዳዮች እንዳይፈጸሙ እንቅፋት መሆንን በማስወገድ" ሊፈጸም ይገባዋል ብሏል።

08 September 2023, 09:47