ፈልግ

የኢየሩሳሌም ተግዳሮት የተሰኘው በቅርቡ ይፋ የሆነው መጽሐፍ የፊት ገጽ የኢየሩሳሌም ተግዳሮት የተሰኘው በቅርቡ ይፋ የሆነው መጽሐፍ የፊት ገጽ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ክርስቲያኖች ወንድማማችነትን እንዲቀበሉ ተጠርተዋል ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በፈረንሳዊው ጸሐፊ ኤሪክ ኢማኑኤል ሽሜት “የኢየሩሳሌም ፈተና - ወደ ቅድስት ሀገር ጉዞ” በሚል ርዕስ ለጻፉት መጽሐፍ መቅድም የጻፉ ሲሆን የሦስቱ የአብርሃማዊ ሃይማኖቶች አማኞች ወንድማማችነትን እንዲቀበሉ ጋብዘዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቫቲካን ማተሚያ ድርጅት ‘ሊብሪሪያ ኤዲትሪቼ ቫቲካና’  እና ‘ኢዲዝዮኒ ኢ/ኦ በተባሉ ሁለት ማተሚያ ቤቶች ትብብር የታተመውን “የኢየሩሳሌም ፈተና - ወደ ቅድስት ሀገር ጉዞ” በሚል ርዕስ ለተጻፈው መጽሐፍ መቅድም ላይ የወንድማማችነት መንፈስን ማጠናከር እንደ ሚገባ ገልጸዋል።

የጳጳሱ የድህረ ቃል አስቀድሞ የወጣው የኢጣሊያ ጳጳሳት ጉባኤ ኦፊሴላዊ ጋዜጣ በሆነው በጣሊያን ካቶሊካዊ ጋዜጣ አቭቬኒሬ ላይ ነው።

ቅዱስ አባታችን መልእክታቸውን የጀመሩት አቶ ሽሜት የጻፉትን መጽሐፍ አስቀድመው ማንበባቸውን የገለጹ ሲሆን እ.ኤ.አ. በ 2014 ወደ ቅድስት ሀገር ያደረጉት ጉዞ ወደ አእምሮአችን ያመጣ ጉዳይ እንደ ገጠማቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ጳውሎስ ስድስተኛ እና በጊዜው የቁስጥንጥንያው ሊቀ ጳጳስ አትናጎራስ (በወቅቱ በዓለም ዙሪያ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች መሪ የነበሩ) መንፈሳዊ ግንኙነታቸው የተረጋገጠበትን 50ኛ ዓመት ለማክበር ወደ እዚያው አቅንተው እንደ ነበረ እንዲያስታውሱ እንደ ረዳቸው ገልጿል።

ይህ ክስተት “በክርስቲያኖች መካከል ለዘመናት ተከፋፍሎና ተለያይቶ የነበረው የመቀራረብ ጉዞ፣ ግን በትክክል በኢየሱስ ምድር አዲስ አቅጣጫን ያገኘ አዲስ ደረጃ” እንደነበር አስታውሷል።

'ሁሉም ከየት እንደተጀመረ'

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የጎበኟቸው እና የተገለጹት ቦታዎች "በግጥም ጥንካሬ" በሥራው ውስጥ በተለይም ቤተልሔም፣ ቅዱስ መካነ መቃብር፣ ጌቴሴማኒ፣ "በኃይል ወደ እኔ አእምሮ ተመልሰው መጥተዋል" ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በናፍቆት ስሜት፣ ደራሲው የኢየሱስ የልጅነት ሕይወት የጀመረባቸውን እና ያደገባቸውን ቦታዎች በማስታወስ  “ሁሉም ነገር የት እንደተጀመረ” ለማሰብ ስሜት የሚቀሰቅ እንደ ሆነም ገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሌሎች የሥራው ገጽታዎች እርሳቸውን "እንደሚገዳደሩ" አምነዋል፣ እናም ለጉዞ ማስታወሻው የተሰጠውን ርዕስ "የኢየሩሳሌም ፈተና" ስንመረምር ሁላችንም "የሰብዓዊ ወንድማማችነት" ፈተና አለብን ብለዋል።

ቅዱስነታቸው እ.ኤ.አ. በ2014 በስፍራው ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉዞ አርጀንቲናዊ ከሆኑት ጓደኛቸው ረቢ አብርሃም ስኮርካ እና ከአርጀንቲና ሙስሊም ተወካይ ኦማር አብዱድ ጋር ለመጓዝ መፈለጋቸው "ያ ጋጣሚ አይደለም" በማለት እየሩሳሌም ለአይሁድ፣ ክርስትና እና እስልምና እምነቶች ያላትን ትልቅ ትርጉም እና ቦታ አስታውሰዋል።

ወንድማማቾች እንዲሆኑ ተጠርተዋል።

"አማኞች ወንድማማቾች እና ድልድይ ገንቢዎች እንዲሆኑ እንጂ  ጠላቶች ወይም ጦርነት ፈጣሪዎች እንዲሆኑ የተጠሩ እንዳልሆኑ በእይታም ማሳየት ፈልጌ ነበር" በማለት በመጽሐፉ መቅድም ላይ ያሰፈሩት ቅዱስነታቸው ጥሪያችን ወንድማማችነት ነው፤ ምክንያቱም የአንድ አምላክ ልጆች ነን" ብለዋል።

"ጥሪያችን ወንድማማችነት ነው፤ ምክንያቱም የአንድ አምላክ ልጆች ነን" ሲሉ በድጋሚ ቅዱስነታቸው ገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል "እየሩሳሌም ዛሬም በዓለም ላይ ያላት ተግዳሮት በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ሌላውን በአንድ ሰብዓዊ ቤተሰብ ውስጥ እንደ ወንድም የመመልከት ፍላጎትን ማንቃት ነው" ያሉ ሲሆን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዚህ “ንቃተ ህሊና” እና “ግንዛቤ” ብቻ  “የጥፋት እና የጥላቻ መሳሪያዎችን በማጥፋት የእግዚአብሔርን ጣፋጭ የሰላም ጠረን በማዳረስ እና በመላው አለም በመስፋፋት  የወደፊቱን ጊዜ ሳንታክት መገንባት እንችላለን ሲሉ ሐሳባቸውን በመጽሐፉ መቅድም ላይ አስፍረዋል።  

07 September 2023, 11:56