ፈልግ

ከዩክሬን ግሪክ-ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የበላይ ሲኖዶስ አባላት ከዩክሬን ግሪክ-ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የበላይ ሲኖዶስ አባላት   (Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በመጪው በጥቅምት ወር ለዩክሬን ሰላም እንዲጸለይ ጥሪ አቅርበዋል!

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከዩክሬን ግሪክ-ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የበላይ ሲኖዶስ አባላት ጋር ተገናኝተው ክርስቲያኖች እ.አ.አ በጥቅምት ወር በዩክሬን ሰላም እና እርቅ እንዲሰፍን እንዲጸልዩ ጋብዘዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዩክሬን ሰላም እንዲሰፍን “የበለጠ ጸሎት እንዲደረግ፣ መንፈሳዊ ለውጥ እንዲመጣ እና ግጭቶችን ማብቃት እንደሚያስፈልግ አጥብቀው ጠይቀው፣ የዩክሬን ጳጳሳት ለጠየቁት ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “እ.አ.አ በጥቅምት ወር በተለይም በማርያም ስም በተሰየሙ ቤተመቅደሶች የመቁጠሪያ ጸሎት በማድረግ  በዩክሬን ውስጥ ሰላም እና እርቅ እንዲፈጠር ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።

እ.አ.አ በጥቅምት ወር ለዩክሬን ሰላም ጸሎተ እንዲደረግ የተጠየቀው የዩክሬን የግሪክ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት ዓመታዊ ሲኖዶስ በሮም እያካሄዱ ባለበት ወቅት ነው።

የዩክሬን ህዝብ መከራ

ወደ ሁለት አመት የሚጠጋው ዩክሬይን ከራሻ ጋር የምታደርገው ጦርነት መጀመሪያ ላይ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከሊቀ ጳጳስ ሲፊያትስላቭ ሻቭሾክ አቀባበል ተደርጎላቸው እንደ ነበረ የሚታወስ ሲሆን “ሀገራቸው የምትገኝበትን አሳዛኝ ሁኔታ አስታውሰው፣ ቁጥራቸው እየጨመረ የሚሄደው የሞቱ፣ የቆሰሉ እና የሚሰቃዩ ሰዎች ድምጽ ቅዱስነታቸው እያስተጋቡ በመሆናቸው ሕዝቡ እያመሰገናቸው እንደ ሆነ የገለጹላቸው ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በብዙ መንገዶች እና በብዙ አጋጣሚዎች ለዩክሬይን ሕዝብ ያላቸው ቅርበት እና ፍቅር በመግለጻቸው ሊቀ ጳጳሱ ቅዱስነታቸው አመስግነዋል።

የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት መግለጫ እንዳመለከተው ከሊቀ ጳጳስ ሻቭሹክ ጋር የተደረገውን ግንኙነት እና ሰላምታ ተከትሎ በርካታ ጳጳሳት “የዩክሬን ሕዝብ በተለያዩ ቦታዎችና በተለያዩ መንገዶች እየደረሰበት ያለውን መከራ” ታሪካቸውን ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ማካፈላቸውን አስታውሷል።

ከዩክሬን ግሪክ-ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የበላይ ሲኖዶስ አባላት ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት
ከዩክሬን ግሪክ-ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የበላይ ሲኖዶስ አባላት ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለጳጳሳቱ ያላቸውን ቅርበት ገልጿል

የፕሬስ ጽ/ቤት አክሎ እንደ ገለጸው ከሆነ ቅዱስ አባታችን የጳጳሳቱን ምስክርነት “በትኩረት አዳምጠዋል” እናም እርሳቸውም በየማሃሉ ጣልቃ እየገቡ ዩክሬናውያን እያጋጠሟቸው ባለው አደጋ ውስጥ ያላቸውን ቅርበት እና በሐዘናቸው የተሳትፎ ስሜት እንዳላቸው ገልፀው በማይነገር ‘የሰማዕትነት መጠን’ ዋጋ እየከፈሉ መሆናቸውን መግለጻቸውን አክለው እንደ ተናገሩ የገለጸው መግለጫው  ለጭካኔ እና ለወንጀል ድርጊቶች መዳረጋቸውን ቅዱስነታቸው በምሬት መናገራቸውን አክሎ ገልጿል።

በተጨማሪም “በጦርነት ወቅት ባጋጠመን የችግር ስሜት እና ሐዘን ሊያጠፋን የሚፈልገው ዲያብሎስ” እየታተረ ይገኛል ሲሉ ተናግሯል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመቀጠል ሐሳባቸውን በተለይም ወደ በወቅቱ ያገኟቸው የዩክሬን ልጆች አዙረዋል። “ወደ እናተ ሕጻናቱ ይመለከታሉ፣ ነገር ግን ፈገግ ማለት ረስተዋል” ሲሉ በምሬት ተናግሯል ። “ይህ ከጦርነት ፍሬ አንዱ ነው-የህፃናትን ፈገግታ ከነሱ ማራቅ ነው” ብሏል።

የኢየሱስን መንገድ በመከተል

በመጨረሻም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሕማማቱ ወቅት የተናገረውን ኢየሱስን በማስታወስ የስድብ፣ የእንግልትና የመስቀል ሰላባ ቢሆንም ነገር ግን እውነትን ለመናገር ድፍረትን አላጣም ነበር፣ ከሕዝቡ ጋር ለመቀራረብም ጭምር፣ በእዚህ የተነሳ እናንተም ጳጳሳት ወንድሞቼ ተስፋ እንዳትቆርጡ” በማለት ተናግሯል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "ይህ ቀላል አይደለም" ብለዋል። ሆኖም በእመንት በመቀጠል ሕያው ልናደርገው እንችላለን፣  “ይህ ቅድስና ነው፣ እናም ህዝቡ ኢየሱስ ባስተማረን በዚህ መንገድ ቅዱሳን እና አስተማሪዎች እንድንሆን ይፈልጋሉ” ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

በስብሰባው ማጠቃለያ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለኤጲስ ቆጶሳት "በድንግል ማርያም ምስል ፊት በጸሎታቸው ዕለት ተዕለት ዩክሬናውያንን እንደሚያስታውሱ" ከገለጹ በኋላ ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

07 September 2023, 11:59