ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከቤኔዲክት ማሕበር መንፈስ ተከታይ ምዕመናን ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከቤኔዲክት ማሕበር መንፈስ ተከታይ ምዕመናን ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት   (Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፡ የቤኔዲክትን መንፈስ በፍቅር የተስፋፋ ልብ ተለይቶ ይታወቃል ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከቤኔዲክት ማሕበር መንፈስ ተከታይ ምዕመናን ጋር በቫቲካን መገናኘታቸው የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባደረጉት ንግግር የቤኔዲክት መንፈስ “በማይነገር የፍቅር ጣፋጭነት የሰፋ ልብ” ተለይቶ ይታወቃል ማለታቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የቤኔዲክት ማሕበር መንፈሳዊነትን የሚከተሉ ምዕመናን አባላት መንፈሳዊነት “በቅዱስ ቤኔዲክት አስደናቂ አገላለጽ ተከታዮቹን ‘በማይነገር የፍቅር ጣፋጭነት ልባቸው እንዲሰፋ’ የጋብዛል” በማለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አርብ ዕለት መስከረም 04/2016  የቤኔዲክት ማሕበር መንፈሳዊነትን የሚከተሉ ምዕመናን አባላት ባደረጉት ንግግር የገለጹ ሲሆን የማሕበሩ አባላት በአምስተኛው የዓለም ኮንግረስ ከተሳተፉ በኋላ ነበር ከቅዱስነታቸው ጋር የተገናኙት።

“የተስፋፋ ልብ” አለ፣ “በዘመናት ሁሉ የጸጋ መንፈስን የሚያበስር ነው፣” ምክንያቱም “ሥሩ በጣም ጽኑ ስለሆነ ዛፉ በደንብ ስለሚያድግ፣ የጊዜን ጥፋቶች በመቋቋም እና የወንጌልን ጣፋጭ ፍሬዎች በማፍራት ነው” ይቀጥላል ሲሉ ቅዱስነታቸው የተናገሩ ሲሆን ቅዱስ አባታችን በዚህ “የልብ መስፋፋት” ሦስት ገጽታዎች ማለትም እግዚአብሔርን መፈለግ፣ ለወንጌል ያለን ጉጉት እና መስተንግዶ በማሰብ አጋጣሚውን ተጠቅመዋል።

እግዚአብሔርን መፈለግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "የቤኔዲክቲን ሕይወት በመጀመሪያ ደረጃ እግዚአብሔርን፣ ለፈቃዱ እና ለሚሰራው ተአምራት በተከታታይ ፍለጋ ይታወቃል" ብለዋል። ይህ “በዋነኝነት” የሚጀምረው በእግዚአብሔር ቃል፣ በተለይም ቅዱሳት የሆኑ መጽሐፍትን በማንበብ ውስጥ፣ በፍጥረት ላይ ማሰላሰል፣ በእለት ተእለት ህይወት ፈተናዎች፣ በጸሎት የስራ ልምድ እና በተለይም በሌሎች ሰዎች አማካይነት ይከናወናል ብሏል።

ለወንጌል ቅንዓት

የቤኔዲክት መነኮሳትን ምሳሌ በመከተል የቤኔዲክቲን ማሕበር መንፈስ የሚከተሉ ምዕመናን ሕይወት እና መስህብነትም “ለወንጌል ባለው ጉጉት” ተለይቷል ያሉት ቅዱስነታቸው “እንደ መነኮሳት፣ የሚኖሩበትን ቦታ ፍሬያማ የሚያደርግ እና ዘመናቸውን በትጋት እንደሚያከብሩ፣ እናንተም በዚህ መንገድ ተጠርታችኋል፣ በምትኖሩበት ቦታ ሁሉ እንደ እርሾ በሊጥ ውስጥ በመሆን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችሁን እንድትቀይሩ ተጠርታችኋል። በክህሎት እና በሃላፊነት እንዲሁም በእርጋታ እና በርህራሄ መንፈስ እንድትጓዙ ተጠርታችኋል ብሏል።

ከጥንታዊው ዓለም ወደ መካከለኛው ዘመን ኅብረተሰብ የተሸጋገረበት ተመሳሳይ ቅንዓት ዛሬም ቤኔዲክትን ሊያመለክት ይገባዋል። በዘመናዊው ዓለም “ወንጌልን የሚያሰራጩ ቀናተኛ ምስክሮች እንጂ ጣታቸውን የሚቀሥሩ ክርስቲያኖች አያስፈልጉም” ሲሉ አበክሮ ተናግሯል ቅዱስነታቸው።

እንግዳ ተቀባይነት

በመጨረሻም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በ "እንግዳ ተቀባይነት" ባህሪ ላይ አንፀባርቀዋል፣ በቅዱስ ቤኔዲክት ህግ ውስጥ ቅዱሱ የማሕበሩ መስራች መነኮሳት በገዳሙ ውስጥ እንግዶችን - በተለይም ምዕመናን እና ድሆችን - ኢየሱስን እንደሚቀበሉት መነኮሳትን ይጠይቃል ብሏል።

እንደ የቅዱስ ቤኔድክት ማሕበር መፈስ ተከታይ ምዕመናን “የናንተ ሰፊ ገዳም ዓለም፣ ከተማና የሥራ ቦታ ነው፤ ደጃችሁን ለሚያንኳኳ ሁሉ የእንኳን ደህና መጣችሁ አርአያ እንድትሆኑ የተጠራችሁበትና ለድሆች  ፍቅር አብነት እንድትሆኑ የተጠራችሁበት ስለሆነ ነው” በማለት ተናግሯል። ከዚሁ ጎን ለጎን ራሳቸውን እንዳይዘጉ አስጠንቅቋቸዋል፣ በተለይም በሌሎች ላይ መጥፎ የመናገር ፈተናን አውግዟል።

ፍቅርን መፈለግ፣ መመስከር እና መቀበል

በመጨረሻም ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የቅዱስ ቤኔዲክት ማሕበር መንፈስ የሚከተሉ ምዕመናን “ልባችሁን ማስፋትን እንድትቀጥሉ እና በየቀኑ ለእግዚአብሔር ፍቅር አደራ እንድትሰጡት፣ መፈለግን ሳታቋርጡ፣ በጉጉት እንድትመሰክሩት እና ህይወት እንድታገኛቸው በሚያደርጉት በጣም ድሆች እንድትቀበሉ እጋብዛችኋለሁ ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቋል።

15 September 2023, 13:40