ፈልግ

SPECIALE/Papa Francesco, i momenti salienti di 10 anni di pontificato

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለስደተኞች አሳዛኝ ሁኔታዎች ግድየለሽ እንዳንሆን ያሳስቡናል።

በሜዲትራኒያን ባህር ውስጥ የተፈጠረውን ሌላ የስደተኞችን አሳዛኝ ክስተት ተከትሎ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሃዘናቸውን በትዊተር ገፃቸው ላይ ያስተላለፉ ሲሆን ሁሉም መልካም ፈቃድ ያላቸው ወንዶች እና ሴቶች በአደገኛ የባህር ማቋረጫዎች እና በተስፋ ጉዞዎች ላይ የሚደርሰውን የስደተኞች ሞት ቸልተኛ እንዳይሆኑ አሳስበዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

“በሜዲትራኒያን ባህር ውስጥ ስደተኞችን በተመለከተ የመርከብ መስመጥ ዜናን በሃዘን ሰማሁ። ለእነዚህ አሳዛኝ ክስተቶች ደንታ ቢስ አንሁን፣ እናም ለተጎጂዎች እና ለቤተሰቦቻቸው እንጸልይ” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ @Pontifex በተሰኘው የትዊተር ገጻቸው ላይ ሐሙስ ነሐሴ 4/2015  በጣሊያን የባህር ዳርቻ ሌላ የስደተኛ ጀልባ መስጠም ምክንያት በማድረግ ሐዘናቸውን ገልጿል።

ከቱኒዚያ ከስፋክስ ከተባለው ቦታ ተነስተው ወደ ጣሊያን ሲትጓዝ የነበረች መርከብ ተገልብጣ አርባ አንድ ሰዎች ረቡዕ ነሐሴ 4/2015 ህይወታቸው አልፏል።

ከሞት የተረፉ አራት ሰዎች በማልታ የጭነት መርከብ ከአደጋው የታደጋቸው ሲሆን በጣሊያን የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ወደ ላምፔዱሳ ተወስደዋል። ከአይቮሪ ኮስት እና ከጊኒ የተረፉት ሰዎች ሶስት ህጻናትን ጨምሮ 45 ሰዎች በጀልቧዋ ላይ ተሳፍረው እንደነበር ተናግረዋል።

የቁጥር ጨምር

የጣሊያን ባለስልጣናት እንደሚሉት በዚህ አመት ከ90,000 በላይ ሰዎች ሜዲትራኒያን ባህርን አቋርጠው ጣሊያን ደርሰዋል። ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከነበረው በእጥፍ ይበልጣል።

እንደ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት ግጭቶችን በመሸሽ፣ በሳህል ክልል እና ከዚያም በላይ ያለውን የጸጥታ ችግር፣ በአፍሪካ ቀንድ ድርቅና ረሃብ፣ በአፍሪካ አህጉር የአየር ንብረት ቀውስ ሰብልን፣ከብቶችን እና ኑሮን በማቃወሱ የተነሳ በርካታ ሰዎች ለስደት እንዲዳረጉ አድርጓል። ይህንን መንገድ በአፍጋኒስታን፣ በሶሪያ እና በሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ እና የእስያ ሀገራት ግጭቶችን እና ሁከት የሚሸሹ ስደተኞች ይጠቀማሉ።

አንዳንዶቹ በሰሜን አፍሪካ የባህር ዳርቻ ላይ በጀልባ በሚጓዙበት ወቅት በባሕር ደህንነት ጠባቂዎች ተይዘው ወደ መጡበት ወደቦች ሲወሰዱ፣ ብዙዎቹ በጣሊያን የባህር ዳርቻ ጠባቂዎች ወይም በጎ አድራጎት ጀልባዎች ወደ መቀበያ ማእከላት ይወስዳሉ።

የአውሮፓ ትልቁ የመቃብር ስፍራ

የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የሜዲትራኒያን መሻገሪያ በአለም ላይ ካሉ የስደተኛ መንገዶች አንዱ እንደሆነ ዘግቧል። እ.አ.አ ከ2014 ጀምሮ ወደ 28,000 የሚጠጉ ሰዎች ባህር ለማቋረጥ ሲሞክሩ ጠፍተዋል ተብሏል።

የሜዲትራኒያን ባህር የአውሮፓ ትልቁ የመቃብር ስፍራ እንደሆነ የገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጉዞ ላይ ያሉትን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችንን ህይወት እና ክብር እንዲጠብቁ መሪዎች እና ፖሊሲ አውጪዎች በተደጋጋሚ ተማጽነዋል።

እርሳቸው ከሚያቀርቡት ሐሳብ መካከል አንዱ “የሰብአዊነት ኮሪደሮችን” ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ስደተኞች የሚደገፉ እና ወደ ተቀባይ አገራት ማህበረሰቦች እንዲቀላቀሉ የሚረዳ ነው። ውጥኑን በእምነት ቡድኖች እና በአንዳንድ የአውሮፓ ህብረት ሀገራት የመንግስት ባለስልጣናት አስተዋውቋል።

እ.አ.አ በመጪው መስከረም 22-23/2023 በሜዲትራኒያን ባሕር አዋሳኝ አገሮች መሪዎች መካከል ውይይትን ለማጎልበት እና በአካባቢው የሚነሱ የጋራ ችግሮችን ለመቅረፍ በጣሊያን ጳጳሳት ጉባኤ በተዘጋጀው እና በማስተዋወቅ “የሜዲትራኒያን ስብሰባዎች” ላይ ለመሳተፍ ወደ ፈረንሣይዋ ማርሴይ ይጓዛሉ። በስብሰባው ላይ ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች እና ወደ 60 የሚጠጉ የሜዲትራኒያን ከንቲባዎች ተወካዮች በተጨማሪ 70 ጳጳሳት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

11 August 2023, 20:24