ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እግዚአብሔር በሌለበት ዓለም ውስጥ የወደፊት ጊዜ እንደማይኖር ገለጹ!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ዩኒቨርሲዳድ ካቶሊካ ፖርቱጌሳ” በመባል በሚታወቀው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጥላ ሥር የሚድተዳደር ዩኒቬርስቲ ተማሪዎች ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸው የተገለጸ ሲሆን “እግዚአብሔር በሌለበት ዓለም ውስጥ የወደፊት ጊዜ ሕይወት የለም” በማለት በምርጫቸው እምነታቸውን እንዲያምኑ ጋብዘዋቸዋል። ስብሰባው የተካሄደው ሐሙስ ሐምሌ 27/2015 ዓ.ም የዓለም ወጣቶች ቀን ለማክበር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ ፖርቱጋል ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉዞ በሁለተኛው ቀን ላይ ነበር።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በፖርቱጋል የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በምርጫቸው ለእምነታቸው ታማኝ እንዲሆኑ አስጠንቅቀዋል፡ “እግዚአብሔር በሌለበት ዓለም ውስጥ መጭው ጊዜ አይኖርም” ብሏል።

የቅዱስ አባታችን ማሳሰቢያ የመጣው 37ኛውን የዓለም ወጣቶች ቀን ምክንያት በማድረግ ወደ ፖርቱጋል ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉዞ በሁለተኛው ቀን በዩኒቨርሲዳድ ካቶሊካ ፖርቱጌሳ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከተማሪዎች ጋር በተገናኙበት ወቅት ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱም እምነታቸውን እንዲቀበሉ እና ዓለምን ለመለወጥ እንዲተጉ እና እንዲጥሩ አበረታቷቸዋል፣ በሁሉም ደረጃዎች የሰብዓዊ ወንድማማችነትን መንፈስ ማስፋፋት ያስፈልጋል ብሏል። በስብሰባው ላይ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እ.አ.አ በ2015 የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ በተመለከተ በላቲን ቋንቋ “ላውዳቶ ሲ” (ውዳሴ ለአንተ ይሁን) የተሰኘው ሐዋርያዊ መልእክት በእርሳቸው የተቋቋመው የዓለም አቀፍ የትምህርት ስምምነት እና በኢኮኖሚው መስክ ስምምነት ላይ የተሳተፉትን የስደተኛ ተማሪዎች፣ በዩኒቨርሲቲው አቀባበል የተደረገላቸውን እና የተማሪዎቹን ምስክርነት አድምጠዋል።

በምታደርገው ምርጫ ላይ እምነትህን በተጨባጭ ግለጽ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ በንግግራቸው ላይ “እውነተኛ የተቀናጀ ሥነ ምህዳር ያለ እግዚአብሔር እውን ሊሆን አይቻልም” “እግዚአብሔር በሌለበት ዓለም የወደፊት ጊዜ ሊኖር አይችልም” በማለት በህይወት ውስጥ በመረጡት ምርጫ በእምነታቸው እንዲታመኑ ጋብዟቸዋል።

"እኔ እላለሁ: በምርጫችሁ እምነታችሁን በተጨባጭ ግለጹ” ሲሉ አክለው ተናግሯል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "እምነት አሳማኝ የአኗኗር ዘይቤዎችን ካልሰጠ በስተቀር በዓለም ላይ "እርሾ" አይሆንም ያሉ ሲሆን እኛ ክርስቲያኖች “እኛም አሳማኝ መሆን አለብን” በማለት አሳማኝ መሆናችን በቂ አይደለም ሲሉም ተናግሯል።

ተግባራችን አሉ ቅዱስነታቸው እና የጠራነው በደስታ እና በጥልቅ የወንጌልን ውበት እንድናንጸባርቅ ነው ያሉ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ “ክርስትና በዓለም ላይ ምሽግ የሚፈጥር በረጃጅም ግንብ የተከበበ ምሽግ ሆኖ መኖር አይቻልም” ሲል አበክሮ ተናግሯል።

በክርስቶስ ውበት ተገረሙ

በእያንዳንዱ ዘመን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደ ተናገሩት ለክርስቲያኖች በጣም አስፈላጊ ከሆኑት ተግባራት መካከል አንዱ የምስጢረ ሥጋዌ (ቃል የነበረው ኢየሱስ ሥጋ መልበሱ) ትርጉም መመለስ መሆኑን አስታውሰዋል፣ ያለ ምስጢረ ሥጋዌ ትርጉም ክርስትና ርዕዮተ ዓለም ይሆናል ሲል አስጠንቅቋል።

"በእያንዳንዱ ወንድምና እህት፣ ወንድና ሴት ሁሉ በኩል በተገለጠው የክርስቶስ ውበት እንድንደነቅ የሚያስችለን በሥጋ መገለጥ ነው" ያሉ ሲሆን በዚህ ረገድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ፍራንቸስኮ ኢኮኖሚ” የተሰየሙትን አዲሱን የትምህርት መስክ በቅድስት ክሌር ስም መስጠታቸው ጠቃሚ ነው ብለዋል።

ቅዱሳንን በማስታወስ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “የሴቶች አስተዋፅዖ በእርግጥ አስፈላጊ” እንዴት እንደሆነ አብራርተዋል።

"በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የቤተሰቡ ኢኮኖሚ በአብዛኛው ለሴቶች እንዴት እንደተሰጠ እናያለን። እነሱ እውነተኛ የቤተሰብ መሪዎች ናቸው፣ ለጥቅም ብቻ ሳይሆን ለመንከባከብ፣ አብሮ ለመኖር፣ እና አካላዊ እና መንፈሳዊ ጥበብ ያላቸው ናቸው። ድሆችን እና እንግዶችን ጨምሮ የሁሉንም ደህንነት" የሚሸከሙ በአብዛኛው እነርሱ ናቸው ብሏል።

"ሴቶች ለጥቅም ብቻ ሳይሆን ለመተሳሰብ፣ አብሮ ለመኖር እና ለሁሉም መንፈሳዊ ደህንነት የታለመ ጥበብ አላቸው” ሲሉ የሴቶችን ባህሪይ አሞካሽተዋል።

የዓለም አቀፍ የትምህርት ስምምነት ልምድ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል ሰባት ዋና ዋና መርሆች ያሉት የዓለም አቀፍ የትምህርት ስምምነት በርካታ ቁልፍ ጉዳዮችን ያካተተ መሆኑን አስታውሰው ለዚህም ተማሪዎች የጋራ ቤታችንን ከመንከባከብ ጀምሮ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ፍላጎት ትኩረት እንዲሰጡ እና እንዲሁም  ለኢኮኖሚክስ፣ ፖለቲካን፣ እድገትን እና ብልጽግና በአዲስ የፈጠራ ዜዴ ለመረዳት የሚያስችል መንገዶችን እንዲቀይሱ ጠይቋል።

"ዓለም አቀፍ የትምህርት ስምምነት እንድታጠኑ እና ስለ ይዘቶቹ እንድትጓጉ አበረታታችኋለሁ" ብሏል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ አንዱ ስለ ተቀባይነትና ስለ መደመር ማስተማር አስፈላጊ መሆኑን በማስታወስ እንዲህ ብለዋል:- “በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 25 ላይ ኢየሱስ የተናገረውን እንዳልሰማን ማስመሰል አንችልም:- እንግዳ ሆኜ ተቀብላችኋል ወይ?' የሚለው እንደ ሆነ ገልጿል።  

የአካባቢ ጥበቃ አስደናቂ አጣዳፊነት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወጣቶቹ አካባቢን እንዲጠብቁ ተማጽነዋል። የጋራ ቤታችን የሆነችውን ምድራችን የመንከባከብ አስደናቂ አጣዳፊነት መገንዘብ አለብን ሲሉ ተማጽኗል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "ደስተኛ ሚድያዎች ስለአደጋው የሚነግሩን በጣም ትቂት የሆኑ ነገሮችን ብቻ ነው፣ ይህ በምድራችን ላይ እየደረሰ ያለው አደጋ እንደ ቁብ የሚቆጠር እንዳልሆነ በሚያሳዝን ሁኔታ ይነግሩናል። እድገት እና ዝግመተ ለውጥ ብለን የምንጠራው ምን መሆናቸውን ለይተን እንደገና የመወሰን አስፈላጊነትን አንርሳ" በማለት አሳስበዋል።

"ምክንያቱም በዕድገት ስም ብዙ ወደኋላ ቀርቷል፤ የምላችሁን በደንብ አጥኑ፤ በእድገት ስም ብዙ ማፈግፈግ ታይቷል" ብሏል።

የሶስተኛው የዓለም ጦርነት ቁርጭራጭ በሆነ መልኩ መታየት ጀምሯል

ከግጭቱ በፊት ከዩክሬን ወጣት መንፈሳዊ ነጋዲያን ጋር የተገናኙት ቅዱስ አባታችን ዓለምን እያስጨነቀ ያለውን ጦርነቶችም ጠቁመዋል።

"ሦስተኛውን የዓለም ጦርነት እያየን ነው" ሲሉ ሥጋታቸውን የገለጹ ሲሆን "ነገር ግን በህመም ላይ ሳይሆን በወሊድ ጊዜ እንደሆንን የማሰብ አደጋን እንቀበላለን፣ መጨረሻ ላይ ሳይሆን በታላቅ ትዕይንት መጀመሪያ ላይ ነው፤ ይህንን ለማሰብ ድፍረት ይጠይቃል” ሲሉ ተናግሯል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በፍርሀት ሽባ እንዳይሆኑ ይልቁንም ፍርሃታቸውን ወደ ህልም እንዲቀይሩ ካሳሰቡ በኋላ ንግግራቸውን አጠናቋል።

04 August 2023, 13:16