ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በፋጢማ፡- ማርያም ሁል ጊዜ በደስታ ትቀበለናለች እና በችኮላ ትረዳናለች አሉ!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በፖርቱጋል በፋጢማ ማርያም ቤተ መቅደስ ተገኝተው በእዚያው ቤተ መቅደስ በሚገኘው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በተገለጸችበት የጸሎት ቤት ውስጥ ከሕመምተኞች እና ከብዙ የሕግ ታራሚዎች ጋር በመሆን የጸሎት ሥነ ሥርዓትን ያደረጉ ሲሆን ለምእመናን ማርያም ሁል ጊዜ ለእኛ እንደምትደርስ እና መንገዱን እንደምታሳየን ገልጸዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ማርያም ሁል ጊዜ "በችኮላ" ትረዳናለች እናም ለህይወታችን ወደ ፊት መንገድ ታሳየናለች። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህንን ማሳሰቢያ በሐምሌ 29/2015 ዓ.ም ቅዳሜ እለት በእመቤታችን ፋጢማ ቤተ መቅደስ ለተሰበሰቡ 200,000 ምዕመናን ባደረጉት ንግግር ሲሆን ለዓለም ሰላም ለመጸለይ እና በ37ኛው የዓለም የወጣቶች ቀን ለመካፈል ወደ እዚያው ባቀኑበት በአራተኛው ቀን ነበር ቅዱስነታቸው ይህንን የተናገሩት።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ 100 የሚጠጉ ህሙማን ወጣቶችን እና ከበርካታ የማረሚያ ቤት እስረኞች ጋር በመሆን የመቁጠሪያ ጸሎት መርተው በፋጢማ እመቤታችን ፊት በጸጥታ ጸለዩ፤ በወርቅ የተሰራ መቁጠሪያ በማርያም ምስል በእግሯ ሥር አስቀምጠው ነበር።

ቤተክርስቲያን በሮች የላትም።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ንግግራቸውን የጀመሩት በተለያዩ ቋንቋዎች የተነበቡትን የመቁጠሪያ ጸሎት ምስጢራት ከተነበቡ በኋላ፣ የፋጢማዋ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተገለጸችበት የጸሎት ቤት እንግዳ ተቀባይ እና ክፍት የሆነች ቤተ ክርስቲያንን “ያማረ ምስል” እንደሚያቀርብ በመግለጽ ነበር።

"ቤተክርስቲያኗ ሁሉም ሰው እንዲገባ በሮች የላትም" ብሏል። "እናት ሁል ጊዜ ለልጆቿ፣ ለሁሉም፣ ለሁሉም፣ ለሁሉም፣ ያለ ማግለል የተከፈተ ልብ አላት" ሲል አጥብቆ ተናግሯል።

ማርያም ሁሌም ወደ እኛ ለመምጣት ትቸኩላለች።

ከዚያም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሲናገሩ ማርያም “መንፈሳዊ ተጓዥ ያደረገች የመጀመሪያዋ እርሷ” እንደነበረች በመግለጽ በእዚህ ጭብጥ ዙሪያ ላይ አተኩረው ነበር።

አሮጊቷ የአጎቷ ልጅ ኤልሳቤጥ እርጉዝ መሆኗን እንዳወቀች “በችኮላ ሄደች” በማለት ወንጌል እንደሚነግረን ጳጳሱ አስታውሰዋል። “ማርያም ሁል ጊዜ ችግር በተፈጠረ ቁጥር ወደ እኛ ለመምጣት ትቸኩላለች” ብሏል። "በምንጠራት ጊዜ ሁሉ ወደ እኛ ትመጣለች፣ እሷ እናታችን ናትና ወደ እኛ ልትቀርብ ትቸኩላለች” ብሏል።

ማርያም ኢየሱስን የምንከተልበት መንገድ ታሳየናለች

በተመሳሳይ እሷ ከኢየሱስ ህይወት ጋር ትጓዛለች እና ከትንሳኤው በኋላ፣ ደቀ መዛሙርቱ መንፈስ ቅዱስን እስኪቀበሉ ድረስ እና ከበዓለ ሃምሳ በኋላ ያለውን ቤተክርስቲያንን ማጀቧን ትቀጥላለች ብሏል። ነገር ግን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አስተያየታቸውን ሲሰጡ ማርያም የትኩረት ማዕከል በፍጹም አይደለችም፡ ሁላችንንም ስትቀበል፣ እሷም ኢየሱስን ጠቁማ፣ እንድንከተለው፣ የሚጠይቀንን ነገር ሁሉ እንድናደርግ “እርሱ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ” ትለናለች ሲሉ ገልጿል።  

"ወደዚህ በመጣን ቁጥር (ወደ ፋጢማ) ይህንን ማስታወስ አለብን፡ ማርያም እራሷን በተለየ መንገድ እዚህ እንድትገኝ አድርጋ ነበር፣ ስለዚህም የብዙ ልብ አለመታመን በኢየሱስ ላይ እንዲከፈት፣ ከእርሷ መገኘት ጋር ወደ ኢየሱስ ይጠቁመናል ሲሉ አክለው ተናግሯል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በማጠቃለያው ኮቫ ዳ ኢሪያ በተባለው የውቅያኖስ ዳርቻ ላይ የሚገኙትን ምዕመናን ወደ ማርያም በመጋበዝ እርሷ ወደ ምን እንደምትጠቁመን እና ኢየሱስ ከእኛ የሚፈልገውን እንዲጠይቁ ከጋበዙ በኋላ ንግግራቸውን አጠናቋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በፋጢማ ማርያ የነበራቸው ቆይታ የሚያሳይ ቪዲዮ
05 August 2023, 16:36