ፈልግ

Pope Francis in Lithuania

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ክርስቲያኖች በአንድነት ወንጌልን እንዲመሰክሩ ጥሪ አቅርቧል!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለዘለዓለም የላቀ ሥነ-ምግባራዊነት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ፣ በዚህ ሳምንት በሰሜን ጣሊያን በተካሄደው የዋልዴሲያንስ (በ12ኛው ክፍለ በፈረንሳይ የተጀመረ የክርስቲያን ንቅናቄ አባላት ናቸው፣ ምእመናኑ ክርስቶስን በድህነት፣ ተራ እና ቀላል በሆነ ሕይወት ለመከተል የፈለጉ ክርስቲያኖች ናቸው) እና የሜቶዲስት ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ በቴሌግራም ባስተላለፉት መልእክት ክርስቲያኖች እንዲተባበሩ አበረታተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ክርስቲያን ባልንጀሮቻችን ስለ ቅዱስ ወንጌል አብረው እንዲመሰክሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የቫቲካን ዋና ጸሐፊ በሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን በኩል ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት የሜቶዲስት እና የዋልዴሲያን አብያተ ክርስቲያናት ሲኖዶስ በዚህ ሳምንት በሰሜን ኢጣሊያ በተካሄደው ስብሰባ ላይ በእሳቸው ስም በቴሌግራም በላኩት መልእክት ነው።

የቴሌግራሙ መልእክት የጀመረው ሊቀ ጳጳሱ የሲኖዶስ አባላትን ሰላምታ በመስጠት የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ “ስብሰባው ለእያንዳንዳቸው ከእርሳቸው እና ከወንድሞችም ጋር ወደ ሚኖረው ኅብረት የሚቀበል፣ የሚመራ እና መመዘኛ ጥልቅ የክርስቶስ ልምድ አጋጣሚ ሊሆን ይችላል” በማለት ተስፋቸውን ገልጿል።

መንፈሳዊ ቅርበት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ለሐይማኖት ሕብረት ውይይት ለተሰጡ ስጦታዎች” እንዲሁም በክርስቲያናዊ እምነት መካከል ስላለው “የተስማማ ትብብር” ለእግዚአብሔርን አብ የምስጋና ጸሎት አቅርበዋል።

በተጨማሪም “የኢየሱስን ወንጌል አብረን ለመመሥከር በጋራ ዕውቀት እንድናድግ በዚህ አስፈላጊ ዝግጅት ላይ በመንፈሳዊነት እንድንኖር” ፍላጎታቸው እንደ ሆነም ገልጿል።

ቅዱስ አባታችን በዚህ ሲኖዶሳዊ ጉባኤ ላይ መልካም ምኞታቸውን በመግለጽ፣ የጌታን በረከት በማሳየት አጠቃለዋል።

የሜቶዲስት እና የዋልዴሲያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት እ.አ.አ በ1975 የተመሰረተ የጣሊያን አንድነት ቤተክርስትያን ሲሆን የዋልዴሲያን ወንጌላዊት ቤተክርስትያን እና የኢጣሊያ ወንጌላዊት ሜቶዲስት ቤተክርስቲያንን አንድ ላይ ያሰባሰበ ሕብረት ነው።

ህብረቱ ወደ 50,000 የሚጠጉ አባላት ያሉት ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 45,000ዎቹ ዋልዴሲያዊያን ናቸው፤ በአብዛኛው በጣሊያን፣ በአርጀንቲና እና በኡራጓይም ይገኛሉ። የሜቶዲስቶች ቁጥር 5,000 ያህል ነው።

23 August 2023, 13:52