ፈልግ

2023.05.22 Storia Laudato si' Ecuador, progetto Otonga

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የላውዳቶ ሲ ሁለተኛ ክፍል በመጻፍ ላይ የገኛሉ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሰኞ ነሐሴ 15/2015 ዓ.ም ዕለት በላቲን ቋንቋ ‘ላውዳቶ ሲ’ (ውዳሴ ለአንተ ይሁን) የተሰኘው ጳጳሳዊ መልእክት ሁለተኛ ክፍል በቅርብ ጊዜ በተከሰተው የአየር ንብረት ቀውሶች ላይ እንደሚያተኩር የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ዳይሬክተር ተናግረዋል።

የእዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሰኞ ዕለት ከአውሮፓ ምክር ቤት አባል ሃገራት የተውጣጡ የህግ ባለሙያዎች ልዑካንን ባነጋገሩበት ወቅት የላውዳቶ ሲ ጳጳሳዊ መልእክት ሁለተኛ ክፍልን ወደ “ወቅታዊ ጉዳዮች” ለማዘመን እየጻፉ እንደ ሆነ ተናግሯል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አካባቢን ለመጠበቅ ያለመ የሕግ ማዕቀፍ ለማዘጋጀት ጠበቆች ላደረጉት ቁርጠኝነት አድናቆታቸውን እየገለጹ ሲሆን "ወጣቱ ትውድ ውብ እና ለኑሮ ምቹ የሆነ ዓለምን ከእኛ የማግኘት መብት እንዳለው ፈጽሞ መዘንጋት የለብንም፣ ይህ የሚያሳየው ከልግስና ከእግዚአብሔር እጅ የተቀበልነው ፍጥረት ላይ ትልቅ ኃላፊነት እንዳለብን ነው" ብለዋል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ። በእዚህ ረገድ ደግሞ እናንተ እያደረጋችሁት ስለምትገኙት አስተዋጾ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ ብሏል።

የቅድስት መንበር የፕሬስ ቢሮ ዳይሬክተር አቶ ማትዮ ብሩኒ ሰኞ ዕለት በሰጡት መግለጫ፥ አዲሱ የተሻሻለው የላውዳቶ ሲ' እትም በተለይ በአምስት አህጉራት ውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ በተከሰቱት እጅግ በጣም አስከፊ የአየር ንብረት ሁኔታ ክስተቶች እና አደጋዎች ላይ እንደሚያተኩር አብራርተዋል።

ላውዳቶ ሲ' የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሁለተኛው ጳጳሳዊ መልእክት ነው።  ጳጳሳዊ መልእክቱ ይፋ የሆነው እ.ኤ.አ. ሰኔ 18 ቀን 2015 ሲሆን የዚያኑ ዓመት ግንቦት 24 ቀን የጰንጠቆስጤ በዓል ሲከበር በይፋ መሰራጨት የጀመረ ጳጳሳዊ መልእክት ነው።

“የጋራ የመኖሪያ ቤታችንን እንክብካቤ” በሚለው ጭብጥ ዙሪያ ላይ ያተኮረው ጳጳሳዊ መልእክቱ ርዕሰሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የጋራ የመኖሪያ ቤታችን የሆነችውን ምድራችንን ለምን መንከባከብ እንዳለብን በስፋት የገለጹበት ጳጳሳዊ መልእክት ነው።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ከእዚህ በመቀጠል በላቲን ቋንቋ “Laudato si” በአማርኛው ውዳሴ ለአንተ ይሁን በሚል ርዕስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እ.አ.አ በግንቦት 24/2015 ዓ.ም ለንባብ ያበቁ ጳጳሳዊ መልእክት የተጠቀሱትን አብይት ጭብቶች በወፍ በረር እንደ ሚከተለው እናስቃኛችኋለን ተከታተሉን።

1.     ምድራችን በልቅሶ ላይ ናት

በእዚህ መልእክቴ ቀደም ሲል ያደረኩትን ንግግር በድጋሜ በማስታወስ “በእዚህ ምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በመክራ ውስጥ የሚገኙ ድሆችን እና በአከባቢ ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ውድመት በድጋሜ ማስታወስ እፈልጋለሁኝ”። እግዚኣብሔር የተትረፈረፈ የአትክልት ሥፍራን ሰጠን፣ ነገር ግን እኛ ወደ ባድማነት እና የትርኪሚርኪ መጣያ፣ ወደ ተበከለ የቆሻሻ መጣያ ሥፍራነት ቀየርናት”። በምድራችን ስነ-ምዕዳር እና የተመጋጋቢነት ሂደት ላይ ኋላፊነት በጎደለው መልኩ እና በእራስ ወዳድነት መንፈስ እየደረሰ የሚገኘውን ውድመት በግድየለሽነት ስሜት ወይም በዝምታ መመልከት አይኖርብንም። “ምክንያቱም በሺዎች የሚቆጠሩ ዝርያዎች እየጠፉ በሚመጡበት ወቅት በመኖራቸው ምክንያት እነርሱን በማየት ለፈጣሪ የምንሰጠው ምስጋና እየቀነሰ ስለ ሚመጣ እና ይህንን የማድረግ መብትም ስለሌለን ጭምር ነው።

የሰው ልጆች በምያደርጉት እንቅስቃሴ ምክንያት የአለም ሙቀት መጨመሩ ይቀጥላል፣ እ.አ.አ. ባሳለፍነው 2015 ዓ.ም የነበረው የዓለማችን ሙቀት እስካሁን ከተመዘገቡት ሁሉ በጣም የላቀ ሲሆን እ.አ.አ በ2016 ዓ.ም እና በተከታታይ ከእዚያ ቀጥሎ በሚገኙ አመታት ውስጥ ይህ ነገር በቀጣይነት እንደ ሚከሰት እሙን ነው። ይህም ጉዳይ በዓለማችን ድርቅ፣ ጎርፍ፣ ሰደድ እሳት እና ያልተለመደ የአየር ንብረት ለውጥ እዲኖር እያደረገ ይገኛል። የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ለስደተኞች ፍሰት ቀውስ ከፍተኛ የሆነ ድርሻ አበርክቷል። በዓለም ውስጥ የሚኖሩ ድሆች ኋላፊነት በማይሰማቸው ሰዎች አማካይነት ድህነት ከደቀንባቸው መከራ ባሻገር በአለም የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ከድጥ ወደ ማጡ እየወረዱ ይገኛሉ።

 የተመጣጠነ የስነ-ምዕዳር ሂደት እንደ ምያሳየው የሰው ልጆ ከተፈጥሮ ጋር ጥብቅ የሆነ ግንኙነት እንዳለው ነው። ስለዚህ ተፈጥሮን መበደል ማለት የሰው ልጆችን መበደል ማለት ነው። በተመሳሳይ መልኩ እያንዳንዱ ፍጥረት የራሱ የሆነ ተፈጥሯዊ እሴቶች አሉት ይህም ሊከበር ይገባዋል። “ምድራችን እና ድሆች እያሰሙ የሚገኙትን ለቅሶ ችላ አንበል” ተገቢ እና ወቅታዊ ምላሽ እንዲገኝ የተቻለንን ሁሉ ማድረግ ይኖርብናል።

2.     . . .እኛ አጥያትን ስለ ሠራን

እግዚአብሔር ለእኛ ምድርን የሰጠን ተመጣጣኝ በሆነ መልኩ “እንድናለማት እና እንድንከባከባት ነው” (ዘፍ 2፡15)። ከመጠን በላይ መጠቀም እና በጣም አንሰተኛ በሚባል መልኩ መንከባከብ አጥያት ነው።

ወንድሜ ፓትሪያርክ በርቴሌመዎስ ብርታት በተሞላው መልኩ በተፈጥሮ ላይ እየፈጸምነው የምንገኘውን አጥያት ተንብየው ነበር።  አሁን በጋራ የመኖሪያ ቤታችን ላይ እየተከሰተ ካለው እውነታ በመነሳት እና በተለይም ደግሞ በምስጢረ ንስኋ አማካይነት “ውስጣዊ የሆነ ለውጥ ማምጣት ይኖርባናል። በተፈጥሮ ላይ ያደረስነውን ጥፋት ተገንዝበን ይቅርታን መጠየቅ ይኖርብናል። እንዲሁም ይህንን ሁኔታ ለመለወጥ ተጨባጭ እርምጃዎችን መውሰድ እንድያስችልን እስቲ ራሳችንን እንመልከት ምክንያቱም ለስነ-ምዕዳር የምናደርገው አስተዋጾን በግልጽ በማወቅ  ለራሳችን፣ ለጎረቤቶቻችን፣ ለተፈጥሮ እና ለፈጣሪ ማሳየት የሚገባንን ኃላፊነት ማወቅ ያስፈልጋል።

3.     ሕሊናችንን መመርመር እና መጸጸት

ለእዚህ ችግር ቀዳሚ የሆነ መፍትሄ ለማምጣት እንዲያስችለን በቅድሚያ “ማመስገን እንድንችል፣ ዓለማችን የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኗን መረዳት እንድንችል እንዲሁም በጽሞና የእርሱን መልካምነትን በመላበስ በመልካም ሥራችን እራሳችንን መስዋዕት ማድረግ እንድንችል፣ በቅድሚያ እራስን መመርመር ያስፈልጋል። ጠንከር ያለ የሕሊና ምርመራ ካደረግን ቡኋላ በፈጣሪ፣ በፍጥረት፣ እንዲሁም በወንድም እና ሕህቶቻችን ላይ ባደረስነው ጥፋት ተጸጽተን ንስኋ መግባት ያስፈልጋል። “ንስኋን አስመልክቶ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ  እንዳስቀመጠው እውነት ነጻ ያወጣችኋል” “እግዚአብሔር ከአጥያታችን በላይ ነው” ስለሆነም በተፈጥሮ ላይ ላደረስነው በደል ይቅር ይለናል”።

4.     አካሄዳችንን ማስተካከል

ሕሊናን መመርመር፣መጸጸት እንዲሁም አጥያታችን በምሕረት ለተሞላው እግዚአብሔር መናዘዝ ወደ አንድ መሻሻልን ማምጣት ወደ ምያስችለን አንድ ዓላማ ይመራናል። ይህም ዓላማ ተፈጥሮን ማክበር ወደ ምያስችለን ተጨባጭ ሐሳብ እና ተግባር ሊተረጎም ይገባል። ለምሳሌም “ፕላሲቲክ ነክ የሆኑ ነገሮችን መጠቀም አቁመን በምትኩም ወረቀት ነክ ነገሮችን መጠቀም፣ የውሃ አጠቃቀማችንን በቁጠባ ማድረግ፣ ህይወት ያላቸው ፍጥረቶች ሁሉ እንክብካቤ ማሳየት፣ በካይነት የሌላቸውን የመጓጓዣ አገልግሎቶችን መጠቀም፣ ዛፎችን መትከል. . . ወዘተ የመሳሰሉትን ተግባራት መፈጸም ያስፈጋል።

5.     አዲስ የምሕረት ተግባር

“የምሕረትን ተግባር ከማከናወን በተሻለ ሁኔታ ከእግዚአብሔር ጋር የምያዋህደን የተሻለ ነገር የለም፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ኋጥያታችንን ይቅር የሚለን እና ፀጋውን የሚሰጠን እኛም ይህንን የምሕረት ተግባር በስሙ ማከናወን እንድንችል ነው”።

የክርስቲያን ሕይወት ባህል ሰባት አካላዊ እና መንፈሳዊ የምሕረት ተግባራትን መፈጸም እንዳለብን ያስተምረናል። “ብዙን ጊዜ የምሕረት ተግባራት ከግለሰቦች ጋር በተያያዘ ሁኔታ የሚፈጸሙ ለምሳሌ ለታመሙት ሆስፒታል፣ ለተራቡት ምግብ ቤት፣ ቤት ለሌላቸው መኖሪያ ቤት፣ ለተማሪዎች ትምህርት ቤት. . . ወዘተ ብቻ መስሎን ሊታይን ይችላል። ነገር ግን የምሕረት ተግባራትን በጥቅሉ ብንመለከት የምሕረት ተግባራት ዋናው ትኩረት የሰው ነፍስ እና ሰውን ያማከሉ ነገሮች ብቻ እንደ ሆኑ ያመለክታል።

ያለምንም ጥርጥር “የሰው ልጅ ሕይወት እና ይህንንም ያማከሉ ነገሮች ሁሉ” የጋራ መኖሪያችን የሆነውን ቤታችን እንድንከባከብ አደራ ይሉናል ማለት ነው። የጋራ መኖሪያ ቤታችን መንከባከብ የእዚህ የምሕረት ተግባራ አንደኛው አካል ነው።

6.     በመጨረሻም እንጸልይ

ምንም እንኳን ኋጥያተኞች ብንሆንም እና በብዙ መከራዎች ውስጥ እያለፍን ቢሆንም ቅሉ ተስፋ መቁረጥ አይገባንም ምክንያቱም ፈጣሪያችን መቼም ቢሆን ብቻችንን አይተወንም እና ነው። መቼም ቢሆን ፈጣሪያችን መሆኑን አያቆምም ምክንያቱም እርሱ ከምድራችን ጋር የተዋኋደ እና የእርሱ ፍቅር ሁል ጊዜም ቢሆን ወደ ፊት እንድንጓዝ የሚደግፈን በመሆኑ ጭምር ነው።

እንዲህ ብለን ልንጸልይ ይገባናል. . . “የድሆች አምላክ የሆንክ እግዚአብሔር ሆይ የተረሳችሁን እና የተጣለችሁን በአንተ ፊት ግን በጣም ውድ የሆነችውን ምድራችንን መታደግ እንድንችል እርዳን። የፍቅር አምላክ ሆይ በእዚህ ምድር ላይ ለሚገኙ ፍጥረቶች ሁሉ ያንተን ፍቅርን ማሳየት የምንችልበትን ቦታ እና ምንገዱን አሳየን። የምሕረት አምላክ ሆይ ያንተን ምሕረት የተጎናጸፍነውን ምሕረርት የጋራ የመኖሪያ ቤታችን በሆነችው ምድራችን ውስጥ መተግበር እንድንችል እርዳን። የእግዚአብሔር ሥም የተመሰገን ይሆን።

 

22 August 2023, 11:00