ፈልግ

PORTUGAL-VATICAN-POPE-RELIGION-WYD

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ 'የሚቀጥለው የዓለም ወጣቶች ቀን በደቡብ ኮሪያ ሴኡል' እንደሚከበር ገለጹ!

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለዓለም ወጣቶች ቀን ማብቅያ ላይ በተዘጋጀው የመስዋተ ቅዳሴ ማጠቃለያ ላይ “ይህን በጸጋ የተሞላ ዝግጅት” ላደረጉት ሁሉ ያላቸውን ጥልቅ ምስጋና ገልጸው የእስያ አገር እ.አ.አ በ2027 ቀጣዩ የዓለም ወጣቶች ቀን ማክበሪያ ሥፍራ እንደሆነች አስታውቀዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ 2023 ዓ.ም የሊዝበን የዓለም ወጣቶች ቀን በተሳካ ሁኔታ እንዲከበር ላደረጉት ሁሉ ምስጋና አቅርበው የሚቀጥለው የዓለም የወጣቶች ቀን በደቡብ ኮሪያ ሴኡል እንደሚካሄድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን ዜና ከማስታወቃቸው በፊት “ከአውሮፓ ምዕራባዊ ጫፍ ወደ ሩቅ ምሥራቅ እየተሸጋገርን” ነው ብለዋል።

በእነዚህ ቀናት ውስጥ በተደጋጋሚ የሰማነው አገላለጽ አለ፡- “አመሰግናለሁ” ወይም ይልቁንስ በፖርቹጋል ቋንቋ “ኦብሪጋዶ” በማለት ለአዘጋጆቹ ምሥጋና አቅርቧል።

የምስጋና መስዋዕተ ቅዳሴ ከተጠናቀቀ በኋላ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ የእግዚአብሔር መልአክ ማርያምን ያበሰረበት የመልአክ እግዚአብሔር ጸሎት አቅርበዋል።

በምላሹ የመስጠት ፍላጎት

“ያ ኦብሪጋዶ (አመሰግናለሁ) ለተቀበልነው የምስጋና ስሜት ብቻ ሳይሆን በምላሹም ለመስጠት ያለንን ፍላጎት የሚያስተላልፍ ነው” በማለት ቅዱስ አባታችን ገልፀው እያንዳንዱ ምዕመናን “በዚህ በጸጋ የተሞላ ዝግጅት” ምን ያህል እንዳገኘ ገልፀዋል ።

አሁን ወደ ቤት ስንመለስ ጌታ በተራው እንድናካፍል እና እንድንሰጥ እንደሚገባ እንዲሰማን፣ እግዚአብሔር በልባችን ስላፈሰሰው በጎ ነገር በደስታ እና በጉጉት እንድንመሰክር ያደርገናል ብሏል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለሊዝበን ፓትርያርክ ብፁዕ ካርዲናል ክሌሜንቴ፣ ለቤተ ክርስቲያን እና ለመላው የፖርቹጋል ሕዝብ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

"ኦብሪጋዶ ለሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት፣ በእነዚህ ቀናት ክስተቶች ወቅት አብሮን ለነበሩት፣ የሊዝበን ከተማን ጨምሮ ለሀገር አቀፍ እና ለአካባቢው ተቋሞች ለድጋፋቸው እና ላደረጉት እርዳታ ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የገለጹ ሲሆን አክለውም “እነዚህ ወጣቶች ሁል ጊዜ እንደ 'ወንድማማች ቤት' እና 'የህልም ከተማ' አድርገው የሚያስታውሷት ነው፣” ካርዲናል ፋሬል እና ይህንን የዓለም ወጣቶች ቀን ያዘጋጁትን ሁሉ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ ብሏል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ምስጋናቸውን ለሁሉም በጎ ፈቃደኞች እና “የዓለም ወጣቶች ቀንን ከላይ ሆነው ለተከታተሉ ማለትም የዝግጅቱ ደጋፊ ለሆኑት ቅዱሳን በተለይም እነዚህን የዓለም ወጣቶች ቀን ወደ ሕይወት ላመጣው ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ” አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

“እና ሁላችሁንም አመሰግናለሁ ውድ ወጣቶች! መልካም እንደሆናችሁ እግዚአብሔር ያያል:: በልባችሁ ውስጥ የዘራውን እርሱ ብቻ ያውቃል። እባካችሁ ውድ አድርጉት። ልነግራችሁ እፈልጋለሁ፡ ምርጥ የሆኑትን ጊዜያት በማስታወስ የነዚህን ቀናት ትውስታ አጥብቃችሁ ያዙ” ሲሉ ተናግሯል።

"በእውነት ማን እንደሆናችሁ አትርሱ"

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ወጣት ምዕመናን “የእነዚህን ቀናት ልምምዶች እና ፀጋዎች እንደገና እንዲቀጥሉ” “በማይቀረው የድካም እና የተስፋ መቁረጥ ጊዜ” “እራሳችሁን የመተው ወይም የመዝጋት ፈተና” ሲገጥማችሁ የማበረታቻ ቀናትን እና ጊዜያትን አስቡ ብሏል።

የሰላም ህልም

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለዓለም ወጣቶች ቀን በአካል ሊሳተፉ ላልቻሉ ወጣቶች ሁሉ የመጨረሻ ሃሳባቸውን ገልፀው በተለያዩ የአለም ሀገራት በሀገረ ስብከቶች እና ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች በተዘጋጁ የሀገር ውስጥ ዝግጅቶች ላይ ለተገኙት እንደ “ከሰሃራ በታች ያሉ ወንድሞቻችን” ሰላምታ ሰጥተዋል።

ውድ ጓደኞቼ ፣ እንደ ትልቅ ሰው ፣ በውስጤ የተሸከምኩትን ህልም ለእናንተ ወጣቶች እንዳካፍላችሁ ፍቀዱልኝ ፣ የሰላም ህልም ነው ፣ ወጣቶች ስለ ሰላም የሚፀልዩበት ፣ በሰላም የመኖር እና የወደፊት ሰላም የመገንባት ህልም ነው ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "ለስር መሰረቶቻችን፣ ለአያቶቻችን እምነትን ለእኛ ያስተላለፉልን የህይወት አድማስን ያስተላለፉልንን" እነርሱን ማመስገን እፈልጋለሁ ብሏል።

"ወደፊት!"

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የወደፊቱን የሰው ልጅ "የሰላም ንግሥት ማርያም" በእጆቿ ጥላ ሥር እንድታስገባ ጸሎታቸው እንደ ሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው ወጣት ተጓዦች ወደ ቤታቸው ሲመለሱ "ስለ ሰላም መጸለይን እንዲቀጥሉ" አሳስበዋል።

“ከዚህም በላይ የተለያዩ ብሔረሰቦች፣ ቋንቋዎችና ታሪኮች ከመከፋፈል ይልቅ እንዴት እንደሚዋሃዱ የሚያሳይ የሰላም ምልክት ናችሁ። እናንተ የሌላ ዓለም ተስፋ ናችሁ። ለዚህ አመሰግናለሁ። በተስፋ ወደ ፊት ሂዱ!” ሲሉ ተናግሯል፡፤

ቀጣዩ የዓለም የወጣቶች ቀን በደቡብ ኮሪያ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ንግግራቸውን ከማጠቃለላቸው በፊት እ.አ.አ በ2025 በሮም የሚከበረውን ኢዩበሊዩ ላይ በዓለም ዙሪያ ያሉ ወጣቶች እንዲሳተፉ ጋብዘው ሲኦል፣ ደቡብ ኮሪያ ቀጣዩ የዓለም ወጣቶች ቀን መዳረሻ ቦታ እንደሆነች ይፋ አድርጓል። ዝግጅቱ እ.አ.አ በ2027 ይካሄዳል።

እ.አ.አ ለ2025 የኢዮቤልዩ ዓመት ወደ ሮም እንዲመጡም “የወጣቶች ኢዮቤልዩ” ማክበር እንዲችሉ በማለት በቦታው የተገኙትን ወጣቶች ጋብዟል።

የመጨረሻው ምስጋና  “ከሁሉ የሚበልጠው” ጌታ ኢየሱስ እና “እናታችን ብፅዕት ማርያም” ነች ሲሉ የተናገሩት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ከእኛ ጋር እዚህ ነበሩ፣ እና ሁልጊዜም ከእኛ ጋር ናቸው፣ ሕይወታችንን ፈጽሞ አይተዉም እና እኛንም ይወዱናል” ሲሉ ንግግራቸውን ቋጭተዋል።

06 August 2023, 16:51