ፈልግ

2023.08.04 Viaggio Apostolico in Portogallo in occasione della XXXVII Giornata Mondiale della Gioventu' - Confessione di alcuni giovani della GMG

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሊዝበን ሶስት ወጣቶችን ምስጢረ ንስሐ ማስገባታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለዓለም ወጣቶች ቀን ወደ ፖርቱጋል ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉዞ በሦስተኛው ቀን ሶስት ወጣት ምዕመናንን ከእግዚአብሔር እና ከባልንጀሮቻችን ጋር ብሎም ከራሳችን ጋር እርቅ የምንፈጥርበት ምስጢረ ንስሀ ማስገባታቸው ተገለጸ።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በፖርቱጋል ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉዞ በሶስተኛው ቀን ማለዳ በሊዝበን ከተማ ከሶስት ወጣት ምዕመናን ጋር የዕርቀ ሰላም ምስጢር የሆነውን ምስጢረ ንስሐ መፈጸማቸው ተገልጿል። ዝግጅቱ የተካሄደው በቫስኮ ዳ ጋማ ፓርክ ሲሆን እ.አ.አ በ1940 የፖርቹጋልን ታሪክ ለማክበር የተገነባው በአይቤሪያ ባሕረ ገብ መሬት ትልቁ አደባባይ ከፕራካ ዶ ኢምፔሪዮ አጠገብ በሚገኘው የሕዝብ ፓርክ ወይም የአትክልት ስፍራ ነው።

የበዓል ዝማሬዎች

ወደ ምስጢረ ንስሐ ሲቃረብ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከሕዝቡ በተሰበሰቡ የደስታ ዝማሬዎች ሞቅ ያለ አቀባበል ተደረጎላቸው ነበር።

የእርቅ ምስጢር የሆነው ምስጢረ ንስሐ የተከናወነው በግለስብ ደረጃ በግል ነው። በፓርኩ ውስጥ የተገኙት የዓለም ወጣቶች ቀን መንፈሳዊ ተጉዦች በጥብቅ ጽሞና እና ጸጥታ ለተወሰኑ ሰዓታት ከተቀመጡ በኋላ በመቀጠልም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለቀጣይ ተሳትፎው ሲሄዱ በደስታ ዝማሬዎች መፈንደቃቸው ተገልጿል።

ቅዱስ አባታችን በፓሮኪያል ዳ ሴራፊና ወደ ሚገኘው ማዕከል በመኪና ከመመለሳቸው በፊት የበጎ አድራጎት ስጪ ሰዎችን እና የበጎ አድራጎት ማዕከላት ተወካዮችን በመገናኘት ጥቂት ጊዜ ወስደው በሥፍራው የሚገኙ ሰዎችን ሰላም ብሏል።  

እምነትህን ተጨባጭ አድርግ

ቀደም ሲል በሐዋርያዊ ጉዟቸው በሁለተኛው ቀን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በሊዝበን ለተገኙት ወጣት ምዕመናን በርካታ የተስፋ ቃል እና የማበረታቻ ቃላት አቅርበዋል።

ቅዱስ አባታችን የፖርቹጋል የካቶሊክ ዩኒቬርስቲ ተማሪዎችን በመጋበዝ ወደፊት ከእግዚአብሔር ጋር በመካከላቸው ሊኖር የሚችለውን ማህበረሰብ እንዲገምቱ እና እምነታቸውን በምርጫቸው “ተአማኒነት ያለው” በማድረግ “እምነት አሳማኝ የአኗኗር ዘይቤዎችን እስካልተሰጠው ድረስ በዓለም ውስጥ እንደ እርሾ ሆኖ መኖር ይገባል” በማለት ሊቀ ጳጳሱ አረጋግጠዋል።

ቤተክርስቲያን የሁሉም ናት።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በፖርቱጋልኛ የምልክት ቋንቋ የሙዚቃ ግጥሞችን በድምቀት በመቅረጽ በፓርክ ኤድዋርዶ ሰባተኛ ክብረ በዓል ላይ በተካሄደው ፌስቲቫላዊ እና ሁሉን አቀፍ የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተው ነበር።

ከ500,000 በላይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን፣ ወጣቶችና ሽማግሌዎች፣ ጤነኞችና ሕሙማን፣ ጻድቃንና ኃጢአተኞች፣ ሁሉም፣ ሁሉም፣ ሁሉም፣ ሁሉም ሰዎች፣ “በቤተክርስቲያን ውስጥ ለሁሉም ቦታ አለ” በማለት ቅዱስ አባታችን መናገራቸው ይታወሳል።

04 August 2023, 14:49