ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ምድር ዝናብ እንደሚያስፈልጋት ሁሉ ቤተክርስቲያን እና ዓለም ወጣቶች ያስፈልጓቸዋል አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሊዝበን በተካሄደው የዓለም ወጣቶች ቀን ማጠቃለያ ላይ ባሳረጉት መስዋተ ቅዳሴ ላይ ባደረጉት ስብከት፣ ወጣቶች ብርሃን እንዲሰጡ፣ እንዲያዳምጡ እና እንዳይፈሩ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ምድር ዝናብ እንደሚያስፈልጋት ሁሉ ቤተክርስቲያን እና ዓለም ወጣቶች ያስፈልጓቸዋል ማለታቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዘንድሮው የዓለም ወጣቶች ቀን ማጠቃለያ ቅዳሴ ላይ በወቅቱ ከማቴዎስ ወንጌል ተወስዶ በተነበበውና ኢየሱስ “ጴጥሮስንና ያዕቆብን እንዲሁም የያዕቆብን ወንድም ዮሐንስን ወደ አንድ ረዥም ተራራ ብቻቸውን ይዟቸው ወጣ። በዚያም በፊታቸው መልኩ ተቀየረ፤ ፊቱ እንደ ፀሓይ አበራ፤ ልብሱም እንደ ብርሃን አንጸባረቀ። ወዲያውም ሙሴና ኤልያስ ከኢየሱስ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለወጣቶች ሰላምታ ስያቀርቡ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለወጣቶች ሰላምታ ስያቀርቡ

ጴጥሮስም ኢየሱስን፣ “ጌታ ሆይ፤ በዚህ ብንሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ፈቃድህ ከሆነ፣ አንድ ለአንተ፣ አንድ ለሙሴ፣ አንድ ለኤልያስ ሦስት ዳሶች ልሥራ” አለው። እርሱ እየተናገረ ሳለ፣ ብሩህ ደመና ሸፈናቸው፤ ከደመናውም ውስጥ፣ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” የሚል ድምፅ ተሰማ” (ማቴዎስ 17፡1-9) በሚለው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ ተመርኩዘው ባደረጉት ስብከት የኢየሱስ ታምራዊ በሆነ ሁኔታ መልኩ መለወጡን  የተመለከቱት ሐዋርያት “በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው!” በማለት የተናገሩትን አስተጋብተዋል።

ከዚሁ ጋር “ከእኛ ጋር ወደ ዕለታዊ ኑሮአችን ሸለቆ ምን ይዘን እንሄዳለን?” በማለት ወጣቶቹ ራሳቸውን እንዲጠይቁ መክረዋል። ቅዱስ አባታችን በእለቱ ወንጌል ላይ ተንተርሰው ሦስት ግሦችን አቅርበዋል፡- ማብራት፣ ማዳመጥ እና አለመፍራት የተሰኙት ናቸው።

ለማብራት

የወንጌል ንባብ ደቀ መዛሙርቱን በጌቴሴማኒ እና በቀራንዮ ለሚያጋጥሟቸው የጨለማ ሰዓታት ለማዘጋጀት ፊቱ እንደ ፀሀይ የበራ እና ልብሱ ነጭ ሆኖ የተገለጸበትን ሁኔታ ለሦስቱ የቅርብ ደቀ መዛሙርቱ የተገለጠበትን ክስተት ይተርካል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “እኛ ደግሞ፣ ብርሃን እንፈልጋለን፣ በሕይወታችን ውስጥ እኛን የሚያጠቃን ብዙ ጨለማን መጋፈጥ የሚያስችል ተስፋ ያለው የብርሃን ፍንጣቂ ያስፈልገናል” ብለዋል። ያ ብርሃን “ኢየሱስ ነው፣ እርሱ የማይጠፋ ብርሃን፣ በሌሊትም የሚያበራ ብርሃን ነውና። ዓይኖቻችንን የሚያበራ፣ ልባችንን የሚያበራ፣ አእምሮአችንን የሚያበራ፣ በሕይወታችን ውስጥ አንድ ነገር ለማድረግ ያለንን ፍላጎት የሚያበራልን፣ ሁልጊዜም በጌታ ብርሃን የሚያበራ ኢየሱስ ነው” ብሏል።

ከዚሁ ጋርም “በራሳችን ላይ ትኩረት ስናደርግ ብሩህ አንሆንም” ሲሉ አስጠንቅቋል። ይልቁንስ "ብርሃን ስንሆን፣ ስናበራ፣ ኢየሱስን ስንቀበል፣ እንደ እርሱ መውደድን እንማራለን። እንደ ኢየሱስ መውደድ፥ ያ ብሩህ ያደርገናል፣ ይህም ወደ ፍቅር ስራዎች ይመራናል" ሲሉ በአጽኖት ተናግሯል።

“ብሩህ እንሆናለን፣ እናበራለን፣ ኢየሱስን ስንቀበል፣ እንደ እርሱ መውደድን እንማር። እንደ ኢየሱስ መውደድ፡- ያ ብርሃን ያደርገናል፣ ወደ ፍቅር ሥራ የሚመራናል” ብሏል።

መስማት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በኢየሱስ መልክ መለወጥ ላይ እየሰጡት ያሉትን አስተያየት የቀጠሉት የእግዚአብሔር አብ ቃል ለሐዋርያት የተናገረውን በመጥቀስ የሚወደውን ልጁን እንዲሰሙ አዘዛቸው ያሉ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "ይህ ሁሉ እዚህ ነው፣ በህይወት ውስጥ መደረግ ያለበት ሁሉ: እርሱን ስሙት። ኢየሱስን አድምጡ፣ ሁሉም ምስጢር እዚያ አለ" ሲሉ ተናግሯል።

አንድ ሰው አምላክ የሚናገራቸውን ነገር እርግጠኛ ካልሆኑ ኢየሱስ የሚናገረውን ለመስማትና የሚናገረውን በልባቸው ለማዳመጥ ቅዱሳት ወንጌሎችን ማንበብ እንደሚችሉ የገለጹ ሲሆን "እርሱ ለእኛ የዘላለም ሕይወት ቃል አለውና። እግዚአብሔር አብ መሆኑን እና እርሱ ፍቅር እንደሆነ ይገልጣል። የፍቅርን መንገድ ያስተምረናል” ሲሉ አክለው ገልጿል።

የዓለም ወጣቶች ቀን ማብቅያ ላይ መስዋዕተ ቅዳሴ በተካሄደበት ወቅት
የዓለም ወጣቶች ቀን ማብቅያ ላይ መስዋዕተ ቅዳሴ በተካሄደበት ወቅት

አትፍራ

በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን ኢየሱስ በተአምራዊ ለውጥ ወቅት ለደቀ መዛሙርቱ የተናገረውን የመጨረሻ ቃል ለወጣት አድማጮቹ አሳስቧቸዋል ይህም “ተነሡ አትፍሩ” የሚለው ቃል ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ታላቅ ህልም ያላቸው” ነገር ግን እውን ላይሆኑ ይችላሉ ብለው የሚፈሩ፣ በተስፋ መቁረጥ ወይም በተስፋ ማጣት ስሜት ሊፈተኑ የሚችሉ ወይም ጥረታቸው በቂ እንዳልሆነ የሚሰማቸውን ወጣቶች ፍርሃታቸውን አምነዋል።

ነገር ግን ዓለምን መለወጥ መፈለግ ለፍትህና ለሰላም መታገል ጥሩ ነው በማለት አበረታቷቸዋል። "ምድር ዝናብ እንደሚያስፈልጋት" አለም እናንተን ወጣቶች ይፈልጋል ብሏል። እናም እያንዳንዳቸዉ ይህንን ቃል በልባቸው በዝምታ እንዲደግሙ ጋብዘው ነበር።

"ውድ ወጣቶች" አሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል የእያንዳንዳችሁን ዓይን ተመልክቼ: - አትፍሩ፣ አትፍሩ፣ ልላቸው እፈልጋለሁ ብሏል።

ኢየሱስ ራሱ እየተመለከታቸው እንደሆነ አረጋግጠውላቸው “ከዚህም በላይ፣ አንድ የሚያምር ነገር እነግራችኋለሁ፡ እኔ አይደለሁም፣ በዚህ ጊዜ እናንተን የሚመለከታችሁ ኢየሱስ ራሱ ነው። እርሱ እኛን ይመለከታል። እርሱ ያውቃችኋል የእያንዳንዳችሁን ልብ ያውቃል የእያንዳንዳችሁን ህይወት ያውቃል ደስታችሁን ያውቃል ሀዘናችሁን ስኬታችሁን እና ውድቀቶቻችሁን ያውቃል ልባችሁን ያውቃል እና እንዲህ ይላችኋል። እናንተ ዛሬ እዚህ በሊዝበን በዚህ የዓለም ወጣቶች ቀን ‘አትፍሩ፣ አትፍሩ፣ አይዞኋችሁ አትፍራ ልላችሁ እፈልጋለሁ ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን አጠቃሏል።

37ኛው የዓለም የወጣቶች ቀን መደምደሚያ ላይ የቀረበው የመስዋዕተ ቅዳሴ ሙሉ ይዘት
06 August 2023, 16:42