ፈልግ

በፈረንሳይ አገር በሉርድ ማርያም ቤተመቅደስ 150ኛውን ብሔራዊ መንፈሳዊ ጉዞ በተደረገበት ወቅት በፈረንሳይ አገር በሉርድ ማርያም ቤተመቅደስ 150ኛውን ብሔራዊ መንፈሳዊ ጉዞ በተደረገበት ወቅት  (ANSA)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት 150ኛውን የሉርድ ብሔራዊ መንፈሳዊ ጉዞ የሚያደርጉ ምዕመናን መባረካቸው ተገለጸ!

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በነሐሴ 09/2015 ዓ.ም በፈረንሳይ አገር በሉርድ ማርያም ቤተመቅደስ 150ኛውን ብሔራዊ መንፈሳዊ ጉዞ ለማድረግ በስፍራው ለተገኙ ከ20000 በላይ ለሚሆኑ መንፈሳዊ ነጋዲያን መንፈሳዊ ቡራኬያቸውን መላካቸው የተገለጸ ሲሆን እነዚህ ከ20000 በላይ የሚሆኑ ምዕመናን ከፈረንሳይ እና ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የውጣጡ መሆናቸውም ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

"እሷ እናታችን ናት እኛ ደግሞም ልጆቿ ነንና ወደ ቅድስት እናታችን እንመለስ!" ሲሉ የቡራኬያቸውን መልእክት የጀመሩት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህንን ማሳሰቢያ የሰጡት እ.ኤ.አ. ነሐሴ 15 ቀን 2023 ይህ የማርያም መንፈሳዊ ነጋዲያን ብሔራዊ ማሕበር 150ኛው የምስረታ በአል ቦታው ተገኝቶ ባከበረበት ወቅት ነበር።

"ለምንወዳት እናታችን በተለይም በዚህ በነሐሴ 15 ቀን (እ.አ.አ በነሐሴ 15 ቀን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የፍልሰታ በዓል ተከብሮ ማለፉን ልብ ልንል ይገባል) በምታቀርቡት የልመና እና የምስጋና ጸሎት በመንፈስ አብሬያችሁ ነኝ" ሲሉ ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት ገልጿል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ምእመናን ይህን ለረጅም ጊዜያት የቆየውን የአምልኮና ሥርዓት ጠብቀው መሄዳቸውን በማየታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፣ በሉርድ በፈረንሳይ ካቴድራሎችና አድባራት የሚገኙ በርካታ ምእመናን በታላቅ እምነት ወደ እመቤታችን በመጸለይ ላይ መሆናቸውን አመልክተዋል። በራስ መተማመን ስሜት እያዳበሩ በመሆናቸውም ምዕመናንን አወድሷል።

የማርያም ርኅራኄን በአምልኮት እንደገና ማግኘት

ቅዱስ አባታችን የቤተክርስቲያን አባቶች “ምእመናን ለሚወዷቸው ቅዱሳን የሚሰማቸውን ፍቅር እና ርኅራኄ እንዲያሳድጉ፣ በተለይም ታዋቂ የሆኑ የአምልኮ ተግባራትን በመጠቀም ወይም እንደገና በማግኘት እንዲንከባከቡ እና እንዲያጠናክሩ” አበረታቷቸዋል።

ለምሳሌ በሀገራችሁ አራት መቶ ዓመታት የሚጠጋ ወግ ያለውን እ.አ.አ በነሐሴ 15/2023 የሚከበረውን የፍልሰታ ማርያም በዓል መንፈሳዊ ጉዞ መልካም የሆነ ተሞክሮ ነው በማለት አሞካሽቷል።

"ከምንጊዜውም በላይ ዓለም እና በተለይም ፈረንሣይ ለእርሷ በሥርዓት የተቀደሰች - ሊሻር የማይችል ቅድስና - የማርያምን ጥበቃ ትፈልጋለች በዘመናችን ካሉ ችግሮች፣ ስጋቶች እና ተግዳሮቶች" ለመላቀቅ የማርያም አማልጅነት ያስፈልጋል ብሏል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሰላም ንግሥት ማርያም ከልጇ ዘንድ ታማልድ ዘንድ በመጸለይ "የጦርነት ጫጫታ በሚሰማበት ቦታ ሁሉ የሚፈለግ ሰላም እንዲሰፍን" እርሷን ልንማጸናት ይገባል ብሏል።

ማህበረሰቦች በመከባበር፣ ክብራቸውንና መብቶቻቸውን እንዲጠብቁ እና ማንም በመንገድ ዳር እንዳይቀር “እውነተኛ የወንድማማች ፍቅር ስሜት እንዲያድግ” በሁሉም ሰው ልብ ውስጥ “እንዲነቃ” ጥሪ አቅርቧል።

ቤተሰቦችን በልዩ መንገድ መጠበቅ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የኢየሱስ እናት "በተለየ መንገድ" ቤተሰቦችን እንድትጠብቅ የጸለዩ ሲሆን በተለይም "የዕለት ተዕለት ሸክም የሚሸከሙ ወላጆችን" እና ወጣቶችን "በችሎታ የበለፀጉ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ስለወደፊታቸው የሚጨነቁ ወይም በሚያሳዝን ሁኔታ በብዙ ገደቦች የተደናቀፉ" ሰዎችን አስታውሰዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱም ሐሳባቸውን ወደ አረጋውያን አዙረው "በልምዳቸው እና በጥበባቸው የበለፀጉ" ነገር ግን "ብዙ ጊዜ የተተው እና ችላ ይባላሉ" እነርሱንም በማርያም ጥበቃ ሥር በአደራ እንሰጣለን ሲሉ ተንግሯል።

በዚህ ዐውደ-ጽሑፍ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ድንግል ማርያም በመከራ፣ በህመም፣ በብቸኝነት፣ የተገለሉ ወይም የተሰደዱትን ሁሉ እንድታጽናናቸው ጠይቀዋል።

የማይናወጥ ተስፋ፣ አንደበተ ርቱዕ የእምነት ምስክር

ልዩ በሆነ መልኩ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የማርያምን መፅናኛ ለማግኘት ወደ ሉርድ ማርያም ቤተመቅደስ የተጓዙትን እጅግ በጣም ብዙ ሰዎችን በማስታወስ ለተገኙት በሽተኞች እና አካል ጉዳተኞች ሁሉ ያላቸውን ቅርበት ገልጿል።

አብረዋቸው ከሚሄዱት ጋር በመሆን ለዓለም የእምነት እና የልግስና ምስክርነት ይሰጡታል ብሏል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ምእመናን ሕይወታቸውን እና ማህበረሰባቸውን መገንባት ያለባቸውን "የማይናወጥ ተስፋን" እንዲፈጥርላቸው አሳስበዋል እናም "በታላቅ ደስታ" በሉርድ ማርያም ቤተመቅደስ ለተሰበሰቡት ሁሉ እና ለመላው ምእመናን ቡራኬ ሰጥተዋል።

 

18 August 2023, 10:38