ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በዓለም የወጣጦች ቀን የመስቀል ጸሎት ላይ ኢየሱስ ከጎናችን መጓዙን ቀጥሏል አሉ!

በሊዝበን ኤድዋርድ ሰባተኛ መናፈሻ ውስጥ በተካሄደው የዓለም ወጣቶች ቀን የመስቀል መንገድ ጸሎት በተደረገበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለወጣቶች ኢየሱስ ዛሬም ከእኛ ጋር መሄዱን እንደቀጠለ፣ ከእያንዳንዳችን ጋር በፍቅር እና በተስፋ መጓዙን እንደሚቀጥል አስታውሰዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅታቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዚህ አርብ ሐምሌ 28/2015 ዓ.ም የዓለም ወጣቶች ቀን አስመልክቶ በተደርገው የመስቀል መንገድ ጸሎት ላይ “ዛሬ ከኢየሱስ ጋር ትሄዳላችሁ” ሲሉ የመስቀል መንገድ መጀመሪያ ላይ ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከልባቸው ሲናገሩ “በመካከላችን በነበረበት ወቅት ኢየሱስ እየተመላለሰ ድውያንን እየፈወሰ፣ ድሆችን እየተንከባከበ፣ ፍትሕን ያደርግ ነበር… ይመላለሳል፣ ይሰብከናል፣ ያስተምረናል” በማለት ወጣቶችን አስታውሰዋል።

ነገር ግን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “በልባችን ውስጥ በጣም የተቀረጸው የቀራንዮ መንገድ፣ የመስቀል መንገድ ነው። ዛሬ ደግሞ በጸሎት ትሄዳላችሁ - እኛ [በጸሎት እንሄዳለን]፣ እናም - በጸሎት የመስቀሉን መንገድ ታድሳላችሁ ብሏል።

በመስቀል መንገድ ላይ የተሳተፉ ወጣቶች
በመስቀል መንገድ ላይ የተሳተፉ ወጣቶች

"ቃልም ሥጋ ሆነ"

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “የኢየሱስ መንገድ እግዚአብሔር ከራሱ የሚወጣ፣ በመካከላችን ሊሄድ ከራሱ የሚወጣ ነው። በቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል መጀመሪያ ላይ ያለውን የድል አድራጊ ቃል በማስታወስ “ቃልም ሥጋ ሆነ በእኛ መካከልም አደረገ። ይህንን ታስውሳላችሁ?" በማለት በቦታው የተገኙትን የጠየቁ ሲሆን “ቃልም ሰው ሆነ በመካከላችንም ሄደ። ይህንንም የሚያደርገው በፍቅር ነው” ሲሉ ተናግሯል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል አድማጮቹን “ኢየሱስ ከእኛ ጋር አለ፣ ከእኛ ጋር ያለቅሳል፣ ምክንያቱም እርሱ ወደ ልቅሶ በሚወስደው ጨለማ ውስጥ ስለሚሆን ከእኛ ጋር አለ” በማለት በማሳሰብ በሕይወታቸው ላይ በገጠሟቸው በሚያሳዝኑ ነገሮች ላይ እንዲያስቡበት ጋብዟቸዋል። እናም በልባቸው ዝምታ ሀዘናቸውን ከኢየሱስ ጋር እንዲካፈሉ ጋበዙ።

ኢየሱስ የመጣው እንባችንን ሊያብስ ነው።

ከትንሽ ዝምታ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለወጣቶቹ “ኢየሱስ በቸርነቱ የተደበቀ እንባችንን ያብሳል” እና ብቸኝነትን፣ ፍርሃታችንን ሊያስወግድ እና መጽናናትን ሊሞላን ሁል ጊዜም እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።

በተመሳሳይ ጊዜ ኢየሱስ ሁል ጊዜ በሕይወታችን በሙሉ አብሮን እያለ “ለመውደድ የሚከለክሉንን ነገሮች እንድንጋፈጥ” ይገፋፋናል ብሏል።

በመጨረሻም ለሁለተኛ ጊዜ በጸጥታ፣ ወጣቶች ስለራሳቸው ስቃይ፣ ጭንቀት እና ሰቆቃ እንዲሁም “ነፍስ እንደገና ፈገግ እንድትል ያለውን ፍላጎት” እንዲያስቡበት በድጋሚ ጥሪ አቅርቧል። ነፍሳችንም ፈገግ እንድትል ወደ መስቀሉ በሚሄደው በመስቀል ላይ በሚሞተው በኢየሱስ ላይ እንደገና በማተኮር የማጽናኛ ቃላትን በመናገር አስተንትኖዋቸውን ደምድመዋል።

የመስቀል መንገድ ጸሎት በተደረገበት ወቅት
የመስቀል መንገድ ጸሎት በተደረገበት ወቅት

የመስቀል መንገድ

እንደ የዓለም የወጣቶች ቀን አዘጋጆች፣ “የመስቀል መንገድ ዓላማ ክርስቶስ የተቀበለውን መከራ ከማስታወስ ያለፈ ነው። የዚህ አይነቱ ጸሎት እንድናስብበት እና በዚህ ፍፁም ለጋስ በሆነው ፍቅር መጠን እንድንበከል እና እራሳችንን ለሌሎች ህይወት አሳልፎ ለመስጠት እንድንችል ይጠቁማል” ሲሉ ተናግሯል።

የዚህ የዓለም የወጣቶች ቀን የመስቀል መንገድ ጸሎት ጭብጦች፣ በወጣቶች እራሳቸው የቀረበው፣ “በአሁኑ ወጣቶች ህይወት ውስጥ ያሉትን ቁስሎች እና ድክመቶች” ድህነትን፣ ብቸኝነትን፣ አለመቻቻልን፣ ተፈጥሮን መጥፋት እና ስደትን ጨምሮ እነዚህን የሰው ልጆች ተጋድሮቶችን ለኢየሱስ ለማቅረብ ያለመ ነው።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የመስቀል ጸሎት በመሩበት ወቅት
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የመስቀል ጸሎት በመሩበት ወቅት

በኢየሱስ ብርታት ማግኘት

ዘመናዊ ድክመቶችን ከ14ቱ የመስቀል መንገድ ማረፊያዎች ጋር ለማገናኘት ያለመ “የጥልቅ ጸሎት ድባብ ለመፍጠር፣ በዚህም ሁሉም ሰው ከኢየሱስ የተቀበሉትን ብርታትና ተነሳሽነት በብርሃንም ሆነ በጨለማ በሕይወታቸው ውስጥ የሚያውቁበት የጸሎት ወቅት ነው።

ይህ ወደ ጸሎቱ ይመራል “ከኢየሱስ ጋር ወደ ቀራኒዮ በሚያደርገው አስቸጋሪ ጉዞ አብሮ መሆናችን ተስፋ እና መነሳሳትን እንዲሞላን፣ ኢየሱስ እንዳደረገው ፈተናዎቹን በመጋፈጥ… በእምነት፣ በተስፋ እና በፍቅር ጥንካሬ እንድንጓዝ ይረዳናል።

የመቀል መንገድ ጸሎት በሊዝበን
የመቀል መንገድ ጸሎት በሊዝበን
የመስቀል መንገድ ጸሎት ሙሉ ቪዲዮ
05 August 2023, 16:43