ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ሆነው የሚያሳይ ምስል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ሆነው የሚያሳይ ምስል  

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ቅድስት ካቴሪ ተራ ስራዎችን በሚያስደንቅ መንገድ ማድረግ እንድንማር ትረዳናለች አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ሆነው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በነሐሴ 24/2015 ዓ.ም ያደርጉ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ከእዚህ ቀደም “ለስብከተ ወንጌል ያለው ፍቅር፡- የምእመናን ሐዋርያዊ ቅንዓት” በሚል ዐብይ አርዕስት ስያደርጉት ከነበረው አስተምህሮ ቀጣይና “መጸለይ እና በደስታ ማገልገል፡ ካቴሪ ቴካክዊታ፣ የሰሜን አሜሪካ ቀደምት የመጀመሪያ ሕዝቦች ተወላጅ” በሚል ንዑስ አርዕስት የቀረበ የክፍል 19 የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ቅድስት ካቴሪ ቴካክዊታ ተራ ስራዎችን በሚያስደንቅ መንገድ ማድረግ እንድንማር ትረዳናለች ማለታቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በእለቱ የተነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል

“ማንም በክፉ ፈንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን እርስ በርሳችሁም ሆነ ለሌሎች ሰዎች ሁልጊዜ መልካም የሆነውን ነገር ለማድረግ ተጣጣሩ።

ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በማናቸውም ሁኔታ አመስግኑ፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ ይህ ነውና” (1 ተሰሎንቄ 5፡15-18)።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እሕቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ቅዱስ ወንጌልን በሐዋርያዊ ቅንዓት እና ጥልቅ ስሜት መስበክ በሚል መሪ ቃል የጀመርነውን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል፣ ዛሬ የመጀመሪያዋ የሰሜን አሜሪካ ቀደምት ሕዝቦች ተወላጅ የሆነችውን ቅድስት ካትሪ ቴካክዊታ እንመለከታለን። እ.ኤ.አ. በ1656 አካባቢ በኒውዮርክ ሰሜናዊ ክፍል ውስጥ በምትገኝ መንደር የተወለደች፣ ምስጢረ ጥምቀት ካልተቀበለ ‘ሞሃውክ’ በመባል የሚታወቁ የሰሜን አሜሪካ ቀደምት ሕዝቦች አለቃ እና የአንግሎሳክሰን (በካናዳ በኦታዋ ወንዝ እና በገባር ወንዞቹ እና በስተ ምዕራብ ከከፍተኛ ሀይቅ በስተሰሜን የሚኖር የአገሬው ቀደምት ተወላጅ ሕዝቦች አባል ናቸው) ከሆነችው ክርስቲያን እናት የተወለደች ልጅ ነበረች፣ ካቴሪ እንድትጸልይ እና ለእግዚአብሔር መዝሙር እንድትዘምር እናቷ አስተምራታለች። ብዙዎቻችን ከጌታ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቀነው በቤተሰቦቻችን አማካይነት ነው፣ በተለይ በእናቶቻችን እና በአያቶቻችን። ወንጌላዊነት ብዙውን ጊዜ የሚጀምረው በዚህ መንገድ ነው፡- በቀላል፣ በትንንሽ ምልክቶች፣ ለምሳሌ ወላጆች ልጆቻቸውን በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገርን እንዲማሩ መርዳት እና ስለ ታላቅ እና መሐሪ ፍቅሩ በመናገር። ለካቴሪ እና ብዙ ጊዜ ለእኛም የእምነት መሰረት በዚህ መንገድ ተቀምጧል።

ካቴሪ የአራት ዓመት ልጅ እያለች ከባድ የፈንጣጣ ወረርሽኝ ህዝቦቿን መታ። ሁለቱም ወላጆቿ እና ታናሽ ወንድሟ ሞተዋል፣ እናም በእርሷ ካቴሪ በፊቷ ላይ ጠባሳ እና የእይታ ችግሮች ፈጥሮ አልፏል በሽታው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ካቴሪ ብዙ ችግሮች አጋጥሟት ነበር፡ አካላዊ የሆኑትን ከፈንጣጣ በሽታ ውጤቶች ጀምሮ በእርግጠኝነት ገጥመዋት የነበረ ሲሆን ነገር ግን አለመግባባቶች፣ ስደት እና እንዲያውም የሞት ዛቻዎችን በፋሲካ እሁድ እ.አ.አ 1676 ከተጠመቀች በኋላ እነዚህ ሁሉ ችግሮች ገጥመዋት ነበር። ይህ ሁሉ ለካቴሪ ታላቅ ፍቅር የሰጣት ሲሆን ስለ እኛ ራሱን እስከ መጨረሻ የሰጠ የክርስቶስ ፍቅር ምልክት የሆነው መስቀል ለመቀበል ተዘጋጀች። በእርግጥም ስለ ቅዱስ ወንጌል መመስከር የሚያስደስት ነገር ብቻ አይደለም፣ በትዕግስት፣ በመተማመን እና በተስፋ የእለት መስቀሎቻችንን እንዴት እንደምንሸከም ማወቅ አለብን። ቅዱስ ወንጌልን በመስበክ እና በመኖር ውስጥ ችግሮች ሲያጋጥሙን፣ ተስፋ እንድንቆርጥ፣ በእርግጠኝነት ለመሸሸግ ወይም እንደኛ በሚያስቡ ትናንሽ ቡድኖች ራሳችንን ለመዝጋት እንፈተን ይሆናል። በታማኝነት እና በትዕግስት በክርስቲያናዊ ህይወት ጎዳና እንድንቀጥል የሚያስፈልገንን ጸጋ ለሚሰጠን ለኢየሱስ ልባችንን ከከፈትን እያንዳንዱን ፈተና ማሸነፍ እንደሚቻል የካቴሪ ተካክዊታ ህይወት ያሳየናል።

ምስጢረ ጥምቀት ከተቀበለች በኋላ ካቴሪ በሞንትሪያል ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው የኢየሱሳዊያን ምስዮናዊያን ተልዕኮ አካል ከነበሩ በሞሃውክ ሕዝቦች መካከል ለመጠለል ተገደደች። እዚያም በየማለዳው ቅዳሴ ላይ ትገኝ ነበር፣ ከቅዱስ ቁርባን በፊት ለመስገድ ጊዜ ሰጠች፣ የመቁጠሪያ ጸሎት ትጸልያለች፣ እናም የንስሃ ህይወትን ኖረች። እነዚህ የእርሷ መንፈሳዊ ልምምዶች በሚስዮን ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ሰው አስደነቁ፣ ለእግዚአብሔር ካላት ጥልቅ ፍቅር የመነጨ በመሆኑ በካቴሪ ውስጥ ያለውን ደስ የሚል ቅድስናን አውቀዋል። በተመሳሳይ ጊዜ፣ የተልእኮው ልጆች እንዲጸልዩ አስተምራቸዋለች፤ እናም የታመሙትን እና አረጋውያንን መንከባከብን ጨምሮ ኃላፊነቶቿን በቋሚነት በመወጣት፣ ለእግዚአብሔር እና ለጎረቤት የትህትና እና የፍቅር አገልግሎት ምሳሌ በመሆን ቀረበች። እዚህ ጋር ለወንድሞች እና እህቶች በተለይም ለድሆች እና በጣም ለችግረኞች ቀላል የሆኑ ዕለታዊ የምሕረት ሥራዎችን ቁሳዊም ሆነ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን ለመስጠት ከጌታ ጋር ያለን ጠቃሚ ግንኙነት እንዴት ፍሬ እንደሚያፈራ እንመለከታለን።

እንድታገባ ሰዎች ብያበረቷቷትም ካቴሪ ሕይወቷን ለክርስቶስ መወሰንን መርጣለች። ወደ ወደ ገዳም ሕይወት መግባት ስላልቻለች፣ እ.አ.አ በመጋቢት 25/1679 ቃለ መንግሥተ ሰማያትን ለማክበር የዘላለም ድንግልና ቃል ኪዳን ገባች። ይህ የእርሷ ምርጫ ሌላውን የሐዋርያዊ ቅንዓት ገጽታ ያሳያል፡ ሙሉ በሙሉ ለጌታ መገዛት። እርግጥ ነው፣ ሁሉም የተጠራው እንደ ካቴሪ በተመሳሳይ ስልት አይደለም፣ ነገር ግን እያንዳንዱ ክርስቲያን በእግዚአብሔር ለተሰጣቸው ጥሪ እና ተልዕኮ ባልተከፋፈለ ልብ በየቀኑ እራሳቸውን እንዲሰጡ ተጠርቷል፣ እግዚአብሔርን እና ባልንጀራውን በበጎ አድራጎት መንፈስ እንድያገለግል ማለት ነው።

ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ የካቴሪ ሕይወት ሐዋርያዊ ቅንዓት በጸሎት እና በቅዱስ ቁርባን በመመገብ ከኢየሱስ ጋር ያለውን ወሳኝ አንድነት እና ለአንድ ሰው ልዩ ጥሪ ታማኝ በመሆን የክርስቲያን መልእክት ውበት ለማዳረስ ያለውን ፍላጎት እንደሚያመለክት ተጨማሪ ማረጋገጫ ነው። በካቴሪ ቴካክዊታ ውስጥ ቅዱስ ወንጌልን የመሰከረች ሴት አግኝተናል፣ በታላላቅ ሥራ አይደለም፤ ምክንያቱም ሃይማኖታዊ ማኅበረሰብም ሆነ የትምህርት ወይም የበጎ አድራጎት ተቋም መሥርታ አታውቅም፣ ነገር ግን በጸጥታ ደስታና የሕይወት ነፃነት ክፍት ሆኖ ሳለ ማለት ነው፣ ጌታ እና ለሌሎች አገልግሎት መስጠት ማለት ነው። በ24 ዓመቷ እ.አ.አ በሚያዝያ 17/1680 ልትሞት በተቃረበችበት ቀናቶች ውስጥ እንኳን ካቴሪ ስራዋን በትህትና፣ እግዚአብሔርን በመውደድ እና በማመስገን እንዲሁም የምትኖርባቸውንም እንዲሁ እንዲያደርጉ አስተምራለች። እንደውም የመጨረሻ ንግግሯ “ኢየሱስ ሆይ እወድሃለሁ” የሚል ነበር።

እኛም ልክ እንደ ቅድስት ካቴሪ ቴካክዊታ ከጌታ ብርታትን እንውሰድ እና ተራ ስራዎችን በሚያስደንቅ መንገድ ማድረግን እንማር፣ በየቀኑ በእምነት፣ በበጎ አድራጎት እና ስለ ክርስቶስ በቅንዓት በመመስከር እንደግ።

30 August 2023, 10:24

በቅርብ ጊዜ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የተደረገው ግንኙነት

ሁሉንም ያንብቡ >