ፈልግ

2019.02.28 Pio XII e il bombardamento di Roma

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሰው ልጅ ከጦርነት እና ከጥቃት እንዲላቀቅ ጸሎት አቀረቡ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከሰማንያ ዓመታት በፊት በሮማ ከተማ አጠገብ በምገኘው ቅዱስ ሎሬንሶ ሰፈር ላይ የተፈፀመውን የቦምብ ጥቃት በማስታወስ ዛሬም ቢሆን እነዚህ አሳዛኝ ሁኔታዎች እየተደጋገሙ መሆናቸውን አውግዘዋል፡- “ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? ሲሉ ጥያቄ አንስተዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እሁድ እለት ሐምሌ 09/2015 ዓ.ም በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ ለዓለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ተናገሩት ከሆነ ከሰማንያ ዓመታት በፊት እ.ኤ.አ. ሐምሌ 19/1943 አንዳንድ የሮም ወረዳዎች በቦምብ ተደብድበው እንደነበር አስታውሰዋል። ይህ አሳዛኝ የሆነ እለት ሲዘከር ለጦርነት እና ታሪካዊ ትዝታ የጠፋበትን ጠንከር ያለ ጥሪ እንደገና ለማደስ አጋጣሚ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚያን ጊዜ በሮማ ከተማ አከባቢ በምገኘው ቅዱስ ሎሬንዞ አውራጃ ብቻ በቦምብ ጥቃቱ 717 ሰዎች ሲሞቱ 4,000 ሰዎች ቆስለዋል፤ ነገር ግን በከተማዋ በሙሉ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 3,000 ሰዎች ሲሆን 11,000 ቆስለዋል በቦምብ በተመቱ በርካታ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ በርካታ ሰዎች ሰለባ እንደ ነበሩ ይታወሳል። በሮም የሚገኘው የነፃነት ታሪካዊ ሙዚየም በሚገኝበት ቦታ ላይ እንደተገለጸው 10 ሺህ ቤቶች ወድመዋል እና 40 ሺህ ዜጎች ቤት አልባ ሆነዋል። በቅዱስ ሎሬንዞ አውራጃ ላይ የሮም የመጀመሪያው የቦምብ ጥቃት የተፈፀመው እ.ኤ.አ. ሐምሌ 19 ቀን 1943 ነበር።

የማስታወስ ችሎታችንን አጥተናል?

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ "እንደ አለመታደል ሆኖ ዛሬም እነዚህ አደጋዎች ተደጋግመዋል። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ትውስታችንን አጥተናል? ጌታ ምህረትን ያድርግልን እና የሰውን ቤተሰብ ከጦርነት መቅሰፍት ያድን" ብለዋል።

ለዩክሬን ጸሎት

በመጨረሻም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጦርነቱ መሪ ሃሳብ ላይ "በጣም እየተሰቃዩ ላሉ ውድ የዩክሬን ህዝቦች" በተለየ መልኩ ጸልዮዋል።

16 July 2023, 11:29