ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቫቲካን የክረምት ካምፕ ውስጥ ከሚገኙ ልጆች ጋር ተገናኙ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ በ2023 በቫቲካን ላሉ ሰራተኞች በተዘጋጀው የክረምት ካምፕ ተነሳሽነት ላይ የሚሳተፉ 250 የሚሆኑ ከ5 እስከ 13 ዓመት የሆናቸው ታዳጊ ሕጻናት ጋር ተገናኝተው ለታዳጊ ሕጻናት እና ከእነርሱ ጋር በካምፕ ውስጥ ሕጻናቱን ለሚከባከቡ እና ለሚያጫውቱ ሰዎች የማበረታቻ ቃላት አቅርበዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በዘንድሮው የቫቲካን የክረምት ካምፕ ላይ የተገኙት ወጣቶች በቫቲካን ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች ልጆች በማሰባሰብ ማክሰኞ ሐምሌ 11/2015 ዓ.ም ማለዳ ላይ በጳውሎስ ስድስተኛ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር በተገናኙበት ወቅት ባደረጉት ውይይት የተለያዩ ጥያቄዎችን ጠይቀዋል።

ከበርካታ ጥያቄዎች መካከል ታዳጊ ሕጻን የሆነው ሄድዋርዶ የተባለ ልጅ "ጀግኖቻችን ለሆኑት ቤተስቦቻችን ምን መልእክት ማስተላለፍ እንችላለን?" በማለት ለቅዱስነታቸው ጥያቄ አቅርቧል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሁሉም ሰው እናቶቻቸውን እና አባቶቻቸውን ወላጆች ልጆቻቸውን ለማሳደግ ስላሳዩት ቁርጠኝነት ብዙ ጊዜ "አመሰግናለሁ" እንዲሉ በማበረታታት ምላች ሰጥተዋል።

ኤሌና የተባለችው ታዳጊ ሕጻን በበኩሏ ለቅዱስነታቸው ባቀረበችው ጥያቄ "የጳጳሱ ልዕለ ጀግኖች እነማን ናቸው?" ብላ ለቅዱስነታቸው ላቀረበችው ጥያቄ  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ምላሽ ሲሰጡ "አያቶቻቸውን" እንደ ሚያደንቁ በመግለጽ ምላሽ የሰጡ ሲሆን "ጥበባቸውን" እንደሚያደንቁ እና ለምን "ከእነሱ ጋር መነጋገር አስፈላጊ እንደ ሆነ በመግለጽ ምላሽ ሰጥተዋል።

ከሦስቱ ታላቅ የሆነው ራፋኤል የተባለ ታዳጊ ሕጻን ለቅዱስነታቸው ያቀረበው ጥያቄ "በዲጂታል ዓለም ውስጥ እንዴት ጀግኖች ለመሆን እንችላለን?" ሲል ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለእዚህ ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ በዚህ ረገድ ማለትም ዲጂታል ሚድያ ላይ በአዎንታዊ መልኩ እንድንሳተፍ፥ ነገር ግን በእሱ ማለትም በዲጂታል ሚዲያ መጠቀሚያ እንዳንሆን በማሳሰብ ምላሽ ሰጥተዋል።

የአያት ምስል

ጥያቄዎቹን የሚጠይቁት ሦስቱ ልጆች በቫቲካን በሚገኘው የበጋው የልጆች ካምፕ ውስጥ እየተሳተፉ ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በልጅ ልጆቻቸው መካከል እንደ አያት አብረዋቸው በመሆን የጎበኟቸው ሲሆን በአጋጣሚ የእሁድ ቀን ሊከበር ጥቂት ቀናት ሲቀሩት የአያቶች እና የአዛውንቶች ቀን ታላቅ ድጋፍ አድርገዋል።

ካምፑን "ለሁሉም የሕጻናት ተንከባካቢዎች እና ረዳቶቻቸው ውድ ተሞክሮ ነው፣ ምክንያቱም ብዙ ፈገግታ ከሚሰጡን ከእነዚህ ወጣቶች ጋር አብረን እንድናድግ እድል ስለሚሰጥ" ሲሉ ገልፀውታል።

በጣሊያነኛ ቋንቋ “ፍራቴሊ ቱቲ” (ሁላችንም ወንድማማቾች ነን) ከተሰኘው ሐዋርያዊ መልእክት እንዴት መነሳሻ እንዳገኙ ጠቁመው “በጉዟችን እንደ ኮምፓስ ሆኖ ወጣቶች በሰዎች መካከል ወንድማማችነትን መፍጠር ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እንዲገነዘቡ ለመርዳት ሁሉም ሰው በቀላሉ የሚታወቅ እና የተከበረ ሆኖ እንዲሰማው ለማድረግ ነው። እንደ ወንድም ወይም እህት፣ የወንድማማችነት ግንኙነቶችን ኃይል፣ ዋጋ እና ውበት እንደገና በማግኘት ላይ ያተኮረ ነው ሲሉ ተናግሯል።

ጉዞው የግንኙነት እና የመጋራትን አስፈላጊነት የሚያጎላ ነው "ሌላውን ከመፍራት ይልቅ በመተማመን ላይ የተመሰረተ ስሜትን እና መልካም አመለካከቶችን በማግኘት ፣ ከመጋጨት ይልቅ በውይይት ላይ ፣ ከትምክህተኝነት እና ከራስ ወዳድነት ይልቅ ነፃ እና መልካም እንቅስቃሴዎችን ማድረግ እንደሚገባን ያበረታታናል" ብሏል።

የዓለም የወጣቶች ቀን ዝግጅት

በቫቲካን የበጋ ካምፕ ከሚሳተፉ ወጣቶች መካከል አንዳንዶቹ እ.አ.አ በመጪው ነሐሴ 1-6/2023 የዓለም ወጣቶች ቀን ላይ እንደ ሚሳተፉ ይጠበቃል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ አባታችን ሆይ የሚለውን ጸሎት ከታዳጊ ሕጻናት ጋር ከደገሙ በኋላ ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተው ለወላጆቻቸው፣ ለአያቶቻቸው እና ለጓደኞቻቸው የእርሳቸውን ሰላምታ እና ቡራኬ እንዲያደርሱ ጠይቀዋል፣ አንዱ ለአንዱ እርስ በርስ መጸለይ ሁልጊዜ ማስታወስ እንደሚገባ ከገለጹ በኋላ ቅዱስነታቸው ጉብኝታቸውን ቋጭተዋል።

19 July 2023, 12:35