ፈልግ

BRITAIN-POLITICS-ECONOMY-BUDGET

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ለዓለም የድሆች ቀን ባስተላለፉት መልእክት ወደ ኋላ አትመልከቱ ማለታቸው ተገለጸ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ድሃ ሰው ባገኘን ጊዜ ሁሉ የጌታን የኢየሱስን ፊት እንዳናገኝ ስለማይከለክለን ወደ ሌላ ቦታ ዞር ብለን ማየት አንችልም” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ለዓመታዊው ለሰባተኛው የዓለም የድሆች ቀን ባስተላለፉት መልዕክት ገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ "ትልቅ የድህነት ወንዝ ከተሞቻችንን እያቆራረጠ ነው" ሲሉ መልዕክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን እያንዳንዱ ክርስቲያን በጸረ ትግሉ "በግለሰብ" ደረጃ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

እ.አ.አ እሑድ ህዳር 19/2023 ዓ.ም ለሚከበረው የአለም የድሆች ቀን ያስተላለፈው መልእክት በመጽሐፈ ጦቢት ላይ ሰፊ ማብራሪያን ይሰጣል።

የችግሩ መጠን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መልእክታቸውን የጀመሩት “ትልቅ የድህነት ወንዝ ከተሞቻችንን እያቋረጠ እየጎረፈ ነው። የሚከብደን ይመስላል፣ ለእርዳታ፣ ድጋፍ እና አጋርነት የሚለምኑ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በጣም ብዙ ናቸው” በሚል ጭብጥ ዙሪያ ላይ ያተኮረ ነው።

“እየኖርን ነው” ሲሉ መልእክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በመቀጠል “በተለይ የድሆችን ፍላጎት በማይነካባቸው ጊዜያት ነው እየኖርን የምንገኘው ብሏል። የበለፀገ የአኗኗር ዘይቤን የመከተል ግፊት ይጨምራል ፣ በድህነት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ድምፅ ግን የማይሰማ ነው” ሲሉ በመልእክታቸው አስፍረዋል።

በተለይም “አዲስ የድህነት ዓይነቶች” ለምሳሌ “በጦርነት ሁኔታ የተጠቁ ሰዎች”፣ የብዙ ሰራተኞች “ኢሰብአዊ አያያዝ” እና “በተለያዩ ዘርፎች ያሉ መላምቶችን” የመሳሰሉ “አስደናቂ የዋጋ ንረት አስከትሏል” በማለት አፅንዖት ሰጥተው በመልእክታቸው ላይ ያስፈሩት ቅዱስነታቸው ብዙ ቤተሰቦችን የበለጠ ለድህነት የሚያጋልጥ ሁኔታዎች እየጨመሩ መጥተዋል ብሏል።

የእኛ ምላሽ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህን ያህል ችግር ሲገጥመን የእኛ ኃላፊነት ግልጽ ነው። ጦቢት ለጦቢያ ሰዎች እንደ ጻፈው “ከድሀ ፊት ፊትህን አትመልስ” የሚለውን ቃል መከተል አለብን ብሏል።

በመቀጠልም “በአንድ ቃል ድሀን ባገኘን ጊዜ ዞር ልንል አንችልም፤ ምክንያቱም ይህ የጌታን የኢየሱስን ፊት እንድናገኝ ይረዳናልና” ሲሉ ተናግሯል።

ስለዚህ “የደጉ ሳምራዊ (ሉቃስ 10፡25-37) ምሳሌ ያለፈ ታሪክ ብቻ አይደለም፤ በዚህ እና አሁን በዕለት ተዕለት ሕይወታችን እያንዳንዳችንን መገዳደሩ ቀጥሏል። በጎ አድራጎትን ለሌሎች ማድረግ ቀላል ቢሆንም የእያንዳንዱ ክርስቲያን ጥሪ በግል መሳተፍ ነው” ብሏል።

የፖለቲካ ሂደት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመቀጠል በዘንድሮው ዓመት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ 23ኛ በላቲን ቋንቋ “ፓቼም ኢን ቴሪስ” (ሰላም በምድር ላይ ይሁን) የተሰኘው ሐዋርያዊ መልእክት 60ኛው ዓመት የሚዘከርበት አመት መሆኑን ጠቁመው “እያንዳንዱ የሰው ልጅ በህይወት የመኖር፣ የተዋሃደ ስብዕና እና አስፈላጊ መንገዶችን የማግኘት መብት አለው። ምግብ፣ ልብስ፣ መጠለያ፣ ሕክምና፣ ዕረፍት፣ እና በመጨረሻም አስፈላጊ የሆኑትን ማህበራዊ አገልግሎቶችን ጨምሮ ለትክክለኛው የህይወት እድገት አስፈላጊ ናቸው” ሲሉ ተናግሯል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እነዚህን መሰረታዊ ጉዳዮች እውን ለማድረግ እና ለሁሉም ለማዳረስ   በፖለቲካው ሂደት ውድቀት ውስጥ እንዴት እርምጃ መውሰድ እንዳለብን ጠይቀዋል።

መልሱ ሁለት ዓይነት ሊሆን ይችላል በማለት በመልእክታቸው ያሰፈሩት ቅዱስነታቸው በአንድ በኩል፣ “የሕዝብ ተቋማት ተግባራቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ማበረታታት አልፎ ተርፎም ጫና ማድረግ ያስፈልጋል”፣ በሌላ በኩል ግን “ከላይ ከኃላፊዎች የሚመጡትን ነገሮች ብቻ በቅንነት ለመቀበል መጠበቅ ዋጋ ወይም ፋይዳ የለውም ብሏል።

በድህነት ውስጥ የሚኖሩ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንዳሉት በዚህ “ለውጥ እና ኃላፊነት” ፍለጋ ውስጥ መካተት አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል።

ይህ በእንዲህ እያለ ከታወጀ ስድስት ዓመታትን ያስቆጠረውን ዓለም አቀፍ የድሆች ቀን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዓለም አቀፍ የድሆች ቀን እንዲከበር፣ በምሕረት ዓመት ኢዮቤልዩ ማገባደጃ ላይ ማለትም እ. አ. አ. በ2016 ዓ. ም. ማወጃቸው ይታወሳል። ዓላማው ክርስቲያኖች በሙሉ በተለያዩ ማኅበራዊ ችግሮች ውስጥ ወድቀው ወደሚገኙ ሰዎች ዘንድ ደርሰው  የኢየሱስ ክርስቶስን ፍቅር በተጨባች አገልግሎት እንዲገልጹ ለማበረታታት በቅድስት መንበር የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪነት በየዓመቱ የሚከበር መሆኑን የጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤቱ ፕሬዚዳንት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሪኖ ፊዚኬላ ከእዚህ ቀደም ማስረዳታቸው ይታወሳል።

ድሆች የቅዱስ ወንጌል ምስክሮቻችን ናቸው!

ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሪኖ ፊዚኬላ ለድሆች የጤና አገልግሎቶችን ለማቅረብ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተቋቋሙ ክሊኒኮችን ኅዳር 1/2015 ዓ. ም. መርቀው በከፈቱበት ሥነ ሥርዓት እንደተናገሩት፣ ድሆች ወደ እግዚአብሔር የቀረቡ ብቻ ሳይሆን የእርሱ ምስክሮች መሆናቸውንም አስረድተዋል። በማከልም ድሆች ለሚያምኑት ሆነ ለማያምኑት የወንጌል ትርጉም በዛሬው ዓለም አቅመ ደካማ ለሆኑት ሰዎች አገልግሎት መስጠት መሆኑን እንድንረዳ ያግዛሉ ብለዋል።

ድህነት በዓለም እየጨመረ ይገኛል

በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ኅዳር 1/2015 ዓ. ም. ተመርቆ የተከፈተው ክሊኒክ በተለያዩ ሕመሞች ማለትም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ እና ኤችአይቢን ጨምሮ በሌሎች ሕመሞች ለሚሰቃዩ ድሃ ማኅበረሰብ ነጻ የምርመራ እና የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመ መሆኑ ታውቋል። ነጻ አገልግሎቱ የድሆች ቁጥር በአሥር እጥፍ እየጨመረ ባለበት በዚህ ወቅት ይበልጥ አንገብጋቢ መሆኑን ገልጸው፣ ችግሩ በሮም እና አካባቢዋ የሚኖሩ ሰዎች ብቻ ሳይሆን በዓለም ዙሪያ የሚገኙትም ጭምር መሆኑን ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ፊዚኬላ አስረድተዋል።

ጤና ፣ ምግብ ፣ ገንዘብ

ቫቲካን በሮም እና አካባቢዋ ለሚገኙ ድሆች ምግብ ማደል ብቻ ሳይሆን ወርሃዊ ወጭዎችንም የሚሸፍንላቸው መሆኑን፣ ይህን ዕርዳታ ምንም ለሌላቸው ድሆች ብቻ ሳይሆን ከወር ወር መድረስ ለማይችሉ ቤተሰቦችም የሚያቀርብ መሆኑን ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሪኖ ፊዚኬላ አስረድተዋል። በጣሊያን ብቻ ከአምስት ሚሊዮን በላይ ተረጂዎች እናዳሏቸው ያስታወቁት አቡነ ፊዚኬላ፣ ጣሊያን ከስድስት ሃብታም አገሮች መካከል አንዷ መሆኗን ገልጸው፣ በማደግ ላይ በሚገኙ የእስያ፣ የላቲን አሜሪካ እና የአፍሪካ አገራት መካከል ችግሩ ምን ያህል ሊበረታ እንደሚችል መገመት ይቻላል ብለዋል።

ከባዱ ፈተናችን ድህነት ነው!

ከዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሀገር ጎብኚዎች ወደ ቫቲካን እንደሚመጡ የተናገሩት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፊዚኬላ፣ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ሲደርሱ የቦታውን ውበት ከማድነቅ በተጨማሪ በአደባባዩ የተቋቋሙ የነጻ ሕክምና መስጫ ክሊኒኮችን ሲመለከቱ ድህነት ዓለማችንን ምን ያህል እንደጎዳው እና ከባዱ ፈተናችን መሆኑን በቀላሉ ሊገነዘቡት ይችላሉ ብለዋል።

 

14 June 2023, 10:52