ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን ከአጎስቲናዊያን ማሕበር አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን ከአጎስቲናዊያን ማሕበር አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት  (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፡- ጦርነቱ በአውሮፓ ያለውን የሲቪልና ሃይማኖታዊ ሚዛን አደጋ ላይ ይጥላል አሉ!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቫቲካን አሱምሽኒስት (አሱምሺኒስት በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጥላ ሥር የሚተዳደሩ የቅዱስ አጎስጢኖስ ተከታይ ማሕበር ገዳም አባላት የሆኑት ወንድ መንኩሴ አባላትን የሚወክል ማሕህበር ሲሆን እ.አ.አ በ1845 ዓ.ም በአማኑኤል ዲ አልዞን የተቋቋመው መንፈሳዊ ማሕበር ነው) ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከእነዚህ አሱምሺኒስት ማሕበር አባላት ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት የሐዋርያዊ ቁልፍ ገጽታዎች መካከል ከመንፈሳዊ ንግደት ጀምሮ ለሚዲያዎች ያላቸውን ቁርጠኝነት እና በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ስለሚሠሩት ሥራ አጉልተወ ተናግሯል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሮም ለ34ኛ አጠቃላይ ጉባሄያቸውን በማድረግ ላይ ለሚገኙት ለአጎስጢናዊያን መነኩሳት ማሕበር አባላት ባደረጉት ንግግር “የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለች” የሚለው የጉባሄያቸውን ሥራ በሚመራው ጭብጥ ላይ አንዳንድ አስተያየቶችን ለማካፈል መርጠዋል። ከሐዋርያዊ ሃይማኖታዊ ሕይወት መሪ ቃል በተመለከተ እና ዋና ተልእኮዎች አንዱ “እጅግ በተጨባጭ”፣ ከመንግሥቱ ጋር መቀራረብን “ለእያንዳንዱ ሰው እና ለመላው ዓለም ያለው ተስፋ” መግለጥ መሆኑን ጠቁመዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "የትም ብትሆኑ የት በተላካችሁበት ቦታ ከሚገኙ ሕዝቦች ጋር በመቀራረባችሁ የመንግሥቱ ምልክቶች ናችሁ" በማለት ለመነኩሳቱ አሳስበዋል።

መቀራረብ በተግባር ብቻ አይደለም።

በመቀጠልም ይህ መቀራረብ በተፈጥሮው በድርጊት የሚያልፍ ከመንፈሳዊ ማኅበራችሁ ጋር የተቆራኘ እና ከቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ አነሳሽነት ጋር የተያያዘ መሆኑን አስረድተዋል። ነገር ግን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል እንደ ተናገሩት ከሆነ “ከድርጊቶቹ ባሻገር፣ የድጋፍ እና የወንድማማችነት መገኘት ከሚያስፈልጋቸው ሰዎች ጀምሮ ራሳችሁን ወደ ሕዝቡ ማቅረብ ነው፣ ይህም የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ ፊት መቃረቡን ያሳያል። እያንዳንዳችሁ በእናንተ እና በወንጌላዊ ምስክነታችሁ" ይህንን መመስከር ይኖርባችኋል ብሏል።

መንፈሳዊ ንግደት እና ለሚዲያ ቁርጠኝነት

በዚህ ረገድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የጉባኤው ሁለት ልዩ ድሎችን ጠቅሰዋል። የመጀመርያው መንፈሳዊ ንግደት ነው፡ ከሀገር አቀፍ መንፈሳዊ ንግደት ወደ ሉርድ ማርያም ከሚደረገው ጀመሮ ማለት ነው “እስከ ላቲን አሜሪካ ድረስ በሩቅ አገሮች የተዛመታችሁበት ግለት። በዚህ ረገድ፣ ቅዱስ አባታችን፣ ሲናገሩ፣ በሕፃንነታቸው ከቦነስ አይረስ ወደ ሉርድ ማርያም የሚደርገውን መንፈሳዊ ጉዞ ያደራጁትን የአጎስቲናዊያን ማሕበር አባላት የሆኑ ገዳማዊያት እህቶች ያስታውሳሉ። "በልጅነቴ... ልንከተለው የሚገባን አንደ ኮከብ ነበር... በደንብ አስታውሳለሁ..." ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ትውስታቸውን ገልጿል።

ሁለተኛው ስኬት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል ለመገናኛ ብዙኃን ያላቸውን ቁርጠኝነት ነው፣ “ይህም ዛሬ በሁሉም አህጉራት፣ ለተለያዩ ሕዝባዊ፣ ከቤተ ክርስቲያን ርቀው ላሉትም” የእግዚአብሔር ቃል እንዲዳረስ እያደረገ ነው የሚል ነው።

በግጭት ጊዜ ሐዋርያ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህንን ሐዋርያዊ ተግባር ከእነዚህ ሃይማኖቶች መካከል “በታሪክ እጅግ ቀስቃሽ” ከሚባሉት አንዱ እንደሆነ አድርገው ይመለከቱታል። "ይህ እውነተኛ ፈተና ነው" ሲሉ ተናግሯል "በዚህም በከባድ አሳሳቢነት ዘመን በመካሄድ ላይ ባሉ ግጭቶች ምክንያት" ሐዋርያዊ ተግባራችንን መቀጠል ይኖርብናል ብሏል።

ይህንን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ አበረታታችኋለሁ ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ይህን ተልእኮ እንድትከታተሉ፣ የክርስቲያኖች ችግር በይፋ በተገለጠበት መካከለኛው ምሥራቅ፣ እና በምሥራቅ አውሮፓ፣ በዩክሬን ያለው ጦርነት የአካባቢውን ሲቪልና ሃይማኖታዊ ሚዛን አደጋ ላይ ይጥላል” ብለዋል። ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አያይዘውም “በቡልጋሪያ ለምትገኘው የባይዛንታይን ትንሽ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ታማኝ ቁርጠኝነት እና ከኦርቶዶክስ ጋር ያላችሁ የረዥም ጊዜ የውይይት ልምድ ከእስልምና እና ከአይሁድ እምነት ጋር ስላደረጋችሁት ውይይት የቅድስት መንበርን ምስጋና አቅርበዋል። ይህ ተግባር ለቤተክርስቲያን ውድ ነው፤ ዛሬ ከምንጊዜውም በላይ ለሰላም አገልግሎት አንድነትና ኅብረትን መሸመን የምትችሉ የዕደ ጥበብ ባለሙያዎች እንድትሆኑ ያድርጋችሁ ብሏል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመቀጠል የጎስጢናዊያን ማሕበር አባላት አጠቃላይ ጉባሄ ዓላማን ገልፀዋል፣ እሱም “ለሚቀጥሉት ስድስት ዓመታት የእርምጃችሁን ሰፊ መስመሮች መግለፅ” ነው። ቅዱስ አባታችን ይህንን ተልእኮ በማሰብ በጸሎታቸው ላይ የተገኙት እና ያላቸውን እምነት "ምርጥ ኃይሎችን ኢንቨስት ማድረግ ትችላላችሁ" እና በተለይም ከደቡብ የዓለም ሀገራት "በእናንተ ተቋማት ውስጥ ያሉትን" በማለት አረጋግጠዋል። እንደሌሎችም ሁሉ አሁን በሰሜን ያለውን የሰው ሀብት እየቀነሰ ነው” ብለዋል።

"ሶስትዮሽ ፍቅር" ማዳበር

የማኅበሩ መስራች አባት የሆኑት አባ አማኑኤል አልዞን፣ ክርስቶስን ውደዱ፣ ድንግል ማርያምን ውደዱ፣ እና ቤተ ክርስቲያንን ውደዱ በማለት ያስተማሩትን 'ሦስትዮሽ ፍቅር' ባንተና በአካባቢያችሁ ለማዳበር አትፍሩ ያሉ ሲሆን በዚህ መንገድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ንግግራቸውን ወደ ማጠቃለያ ሲያቀርቡ፣ “ለፍቅራችሁ ታማኝ ትሆናላችሁ እናም ወደ ሕይወት ለማምጣት ታማኝ እና አዲስ መንገዶችን ፈልጉ” ብለዋል ።

በእነዚህ ሁሉ መንገዶች፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት ከሆነ “ውድ ወንድሞች፣ አሮጌ እና አዲስ፣ በጸሎቴና በመተማመን መታመን ትችላላችሁ” በማለት ንግግራቸውን ደምድመዋል። በመጨረሻም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለተሰበሰቡት ሁሉ "ጌታ በተልዕኳችሁ  ቦታ ሁሉ መልካም አገልጋዮች እንድትሆኑ እና መልካም ተልዕኮ ለሁላችሁም" እመኝላችኋለሁ ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን ቋጭተዋል።

23 June 2023, 15:06