ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከላይ ያለው ሰማይ በወንድማማችነት እንድንራመድ ይጋብዘናል ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮ ቅዳሜ ሰኔ 03/2015 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በተካሄደው የሰብዓዊ ወንድማማችነት ስብሰባ ላይ ባስተላለፉት መልእክት “ከላይ ያለው ሰማይ አንድ ላይ እንድንመላለስ፣ እንደ ወንድሞችና እህቶች እርስ በርሳችን እንድንገናኝ እና ወንድማማችነትን እንድንፈጥር እና ወንድማማቾች መሆናችንን እንድናምን” ይጋብዘናል ማለታቸው ተገልጿል። ለ30 የኖቤል ተሸላሚዎች የተዘጋጀውን እና በስብሰባው ማጠቃለያ ላይ የተፈረመውን የሰብአዊ ወንድማማችነት መግለጫ ሰንድ ቅዱስነታቸው አወድሷል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት በማቅረብ ነበር መልእክታቸውን የጀመሩት፥ በሰኔ 03/2015 ዓ.ም ቅዳሜ ከሰአት በኋላ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በተደረገው የሰብአዊ ወንድማማችነት ስብሰባ ላይ በቅርብ እና በሩቅ ሆነው ዝግጅቱን ለተሳተፉት ሁሉ ጥልቅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ። የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መልዕክት  የቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ካህናት እና የቫቲካን ቄሰ ገበዝ ዋና ተወካይ ብፁዕ ካርዲናል ማውሮ ጋምቤሬቲ ባስተላለፉት መልእክት ነው። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአሁኑ ጊዜ በሆስፒታል ውስጥ ቀዶ ጥገና አድርገው በማገገም ላይ ይገኛሉ እናም እንደታቀደው በዝግጅቱ ላይ መገኘት አልቻሉም ።

ወንድማማችነት እና ሰላም

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "በዓለም ላይ የወንድማማችነት እና የሰላም ፍላጎት" ለማረጋገጥ በስብሰባው ላይ የተገኙትን ሁሉ አመስግነዋል። የዝግጅቱ አለም አቀፋዊ ገጽታ ከአለም ዙሪያ የተውጣጡ በሁሉም የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎች የመከራ እና የስቃይ ልምዳቸውን በሚያካፍሉ አነቃቂ ምስክርነቶች እና ቃለ መጠይቆች ይደመደማል።

በጦርነት፣ በድህነት ወይም በመከራ ጠባሳ የተጎዱትን በሙሉ በመልእክታቸው አስታውሰዋል። (#NotAlone) ብቻችንን ሳይሆን በመደመርና በወዳጅነት በመተሳሰር በሕይወታቸው ወደፊት መግፋት በመቻላቸው ሁላችንም  እንደ ወንድም እና እህት በመሰባሰብ የጋራ ሰብአዊነታችንን እንድንመሰክር እና የወንድማማችነት ጥሪን እንድንቀበል ጥሪ አቅርበዋል።

"በእርግጥም ከላይ ያሉት ሰማያት አንድ ላይ እንድንራመድ፣ እንደ ወንድማማቾች እና እህተማማቾች እርስ በርሳችን እንድንገናኝ እና ወንድማማችነትን እንደ መንፈሳዊ ጉዞ መሠረት እንድናምን ይጋብዘናል” በማለት መልእክታቸውን ያስተላለፉት ቅዱስነታቸው ተሳታፊዎች ልምዳቸውን እና ምስክርነታቸውን ከጣሊያን (ትራፓኒ)፣ ኮንጎ (ብራዛቪል)፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ (ባንጉዊ)፣ ኢትዮጵያ፣ አርጀንቲና (ቦነስ አይረስ)፣ እስራኤል (ኢየሩሳሌምን)፣ ጃፓን (ናጋሳኪ) እና ፔሩ (ሊማ) ጨምሮ በዓለም ዙሪያ ካሉ ከስምንት በላይ ሀገራት የተውጣጡ ሰዎች የተሳተፉበት ስብሰባ ተከናውኗል።

 ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በጣሊያነኛ ቋንቋ “Fratelli tutti” ሁላችንም ወንድማማቾች ነን በተሰኘው ሐዋርያዊ መልእክታቸው ላይ እንደገለጹት ከሆነ ትክክለኛ ወንድማማችነት እንደ ወንድም ወይም እህት እንድንተያይ ይጠራናል -የቁጥር ስሌት  ወይም “ሌላ” ብቻ ሳይሆን ክብር ያለው እና ክብር የሚገባው የሰው ልጅ ነው። በብዝበዛና ግዴለሽነት፣ ዓመጽ እና ጦርነቶች በተሰቃየችው መከራ በተቀበለችው ዓለም ውስጥ፣ “ማስተካከያዎችን ማድረግ  ቢቻ በቂ አይደሉም” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጽፈዋል።

"ከልብ የተወለደ እና በወንድማማችነት ላይ ያተኮረ ታላቅ መንፈሳዊ እና ማሕበራዊ ቃል ኪዳን ብቻ ነው የሰው ልጅ ክብርን እንደ የግንኙነቶች አስኳል መመለስ የሚችለው" ሲሉ በጹሑፋቸው ማስፈራቸው ይታወሳል።

እርምጃ ለሰላም ባህል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “የሰላም ባህልን” ለማራመድ ከንድፈ ሃሳቦች በላይ “ተጨባጭ ምልክቶች” እንደሚያስፈልገን አስምረውበታል። እናም በመጀመሪያ "ለወንድሞቼ እና ለእህቶቼ ምን መስጠት እችላለሁ" ብለን ልንጠይቅ ይገባል ያሉ ሲሆን ህብረተሰቡ እኔን ሊጠቅመኝ በሚችል ነገር ላይ ብቻ ከማተኮር ይልቅ እኔ ለህብረተሰቡ ምን ማድረግ መቻል አለብኝ ብለን መጠየቅ አለብን ብሏል። ወንድማማችነትን ለመገንባት ተጨባጭ ምልክቶችን እናቅርብ፣ ከቤተሰብ አባላት፣ ከጓደኞቻችን እና ከጎረቤቶች ጋር እንኳን ታርቀን፣ ለበደሉን ሰዎች መጸለይ፣ የተቸገሩትን በመርዳት፣ በሁሉም የሕይወታችን ቦታዎች የሰላም ቃል በመናገር እና በማጽናናት ልንተገብረው እንችላለን ብሏል። ብቸኝነት የሚሰማቸውን የእኛ ቅርበት የምያስፈላጋቸውን ሰዎች መርዳት እና ማገዝ ያስፈልጋል ሲሉ አክለው ተናግሯል።

የርኅራኄ ቅባት

በግለሰቦች ወይም በህዝቦች መካከል "ጋንግሪን" የሆኑ ግንኙነቶችን ለመፈወስ እንዲረዳን "የርኅራኄን ቅባት ለመቀባት" ተጠርተናል ሲሉ የተናገሩት ቅዱስነታቸው "በእግዚአብሔር ስም እና ሰላምን ለሚሹ ወንድና ሴት ሁሉ" ለመጮህ አንታክት" ብሏል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወንድማማችነት ውድ በመሆኑ ተሰባሪ መሆኑን በማስታወስ "ከጥላቻ እና ከጥቃት ይልቅ እኛን አንድ የሚያደርግ የወንድማማችነት ስሜት የበለጠ ጠንካራ ነው" ብለዋል። የግጭቶችን ምሽት የሚያቆመውን ብርሃን እንደገና ማብራት ይገባል ሲሉም በመልእክታቸው አስተላልፈዋል።

ከወንድማማችነት ጋር በተሻለ ሁኔታ ይለውጡ

ሁላችንም ወንድማማች እና እህቶች መሆናችንን ማመናችን መከበር የሚገባውን የጋራ ሰብአዊ ክብራችንን ለማየት ከራሳችን ብሄር እና ባህል ባሻገር እንድንመለከት ይረዳናል ሲል አብርቷል። እናም ግለሰቦች እና ማህበረሰቦች ወንድማማችነትን ሲመርጡ ፖሊሲዎች በተሻለ ሁኔታ ሊለወጡ ይችላሉ ብለዋል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ። አካባቢን የሚጠብቁ ፖሊሲዎች፣ ለሥራ ትክክለኛ ደመወዝ የሚያረጋግጡ፣ ወይም ያለፉ ስህተቶችን ለመሸፈን የሚደረጉ ጥረቶች፣ ሁሉም ወደ ተስፋ፣ ብልጽግና፣ ፍትህ እና ፈውስ እንድናመራ ያደርጋል ብሏል።

የኖቤል ተሸላሚዎች

በማጠቃለያም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የስብሰባውን አስተባባሪዎች አመስግነው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተገኙት 30ዎቹ የኖቤል ተሸላሚዎች በዕለቱ የተዘጋጀውን የሰብዓዊ ወንድማማችነት መግለጫ ሰነድ በማመስገን በየቀኑ በተጨባጭ መንገዶች ስለወንድማማችነት ለመመሥከር የሚያስችል መመሪያ ይሰጣል ብለዋል።

"በአንድነት የሰላም ባህል ለመገንባት የአለምን ሴቶች እና ወንዶች የማቀፍ ፍላጎት በልባችሁ እና በትዝታችው እንድትይዙ እመኛለሁ። በእርግጥም ሰላም ወንድማማችነትን ይፈልጋል፣ ወንድማማችነት እንዲፈጠር ያደርጋል” ብሏል።

የኖቤል ተሸላሚዎች ቡድን ተወካዮች ዶ/ር መሀመድ ዩኑስ እና ዶ/ር ናዲያ ሙራድ የሰብአዊ ወንድማማችነት ሰነድ እና መግለጫን በዝግጅቱ ላይ ሲያቀርቡ የቫቲካን ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ፊርማቸውን አስፍረውበታል።

 

ስለ ሰብዓዊ ወንድማማችነት የቀረበ መግለጫ

ሮም፣ ከቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ፣ ሰኔ 03/2015 ዓ.ም

“እኛ ብዝሃነት ያለን፣ የተለያየ ሰዎች ነን፣ የተለያዩ ባህሎች እና ሀይማኖቶች አሉን፣ ነገር ግን ወንድሞች እና እህቶች ነን እናም በሰላም መኖር እንፈልጋለን” (ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ)።

ሁል ጊዜ ሁሉም ወንድ ወንድማችን ነው ፣ ሁሉም ሴት እህታችን ናት። ሁላችንም የአትክልት ሥፍራ በሆነችው በምድር ላይ እንደ ወንድሞች እና እህቶች አብረን እንድንኖር እንፈልጋለን። የወንድማማችነት መንፈስ ያለው የአትክልት ሥፍራ ለሁሉም ህይወት ቅድመ ሁኔታ ነው።

በአለም ጥግ ሁሉ ሰብዓዊ ክብር ሲከበር፣ እንባ ሲታበስ፣ ለሰራነው ስራ በአግባቡ ሲከፈለን፣ ትምህርት ሲረጋገጥ፣ ጤና ሲጠበቅ፣ ብዝሃነት ሲከበር፣ ተፈጥሮ ሲታደስ፣ ፍትህ ሲከበር፣ የጠፋ መግባባት እንዴት እንደገና እንደሚያብብ እና ማህበረሰቦች ብቸኝነታቸውን እና ፍርሃታቸውን እንዴት እንደ ሚጋፈጡ ምስክሮች ነን።

በጋራ ግንኙነታችን በወንድማማችነት ለመኖር እንመርጣለን፣ ውይይት እና ይቅርታ ማድረግ “መርሳት ማለት አይደለም” (Fratelli tutti, n. 250)፣ ነገር ግን መተው ማለት ነው “ለተመሳሳይ አጥፊ ኃይል አይሰጥም” ለሁላችንም የሚደርሰን መዘዝ አይሆንም።

ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር በመሆን “ትክክለኛ እርቅ ከግጭት የሚሸሽ ሳይሆን በግጭት ውስጥ የሚገኝ፣ በውይይት እና ግልጽ፣ ታማኝ እና በትዕግስት ድርድር የሚፈታ ነው” በማለት በድጋሚ ማረጋገጥ እንፈልጋለን። ይህ ሁሉ በሰብአዊ መብቶች ማዕቀፍ ውስጥ ሊተገበር ይገባል።

ዳግም ጦርነት አታድርጉ ብለን በወንድማማችነት ስም ለአለም መጮህ እንፈልጋለን! የሰው ልጆችን እጣ ፈንታ የሚመራው ሰላም፣ ፍትህ እና እኩልነት ነው። ፍርሃት እናስወግድ፣ ወሲባዊ እና የቤት ውስጥ ጥቃትን እንቢ እንላለን! ሁሉም የትጥቅ ግጭቶች መቆም አለባቸው። ከዚህ በኋላ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ፣ ፈንጂ እንዳይኖር እንሻለን።  የግዳጅ ስደት፣ የዘር ማጽዳት፣ አምባገነንነት፣ ሙስና እና ባርነት እንቃወማለን። ቴክኖሎጂን እና ሰው ሰራሽ አብርሆት የሚያመጡትን ጭና እንቃወማለን፥ ወንድማማችነትን ከቴክኖሎጂ እድገት እናስቀድም ፣ ዘልቆ እንዲገባ እንፍቀድለት።

አገሮች የሰላም ማህበረሰብ ለመፍጠር፣ ለምሳሌ የሰላም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን በማቋቋም የጋራ ጥረቶችን እንዲያበረታቱ እናበረታታለን።

በአመፅና በጥላቻ ደም፣ በማህበራዊ እኩልነት እና በልብ መበላሸት የተበከለችውን ምድር ለመፈወስ እራሳችንን ቃል እናስገባለን። ጥላቻን በፍቅር እንለውጥ።

ርኅራኄ፣ መጋራት፣ ልግስና፣ ጨዋነት፣ እና ኃላፊነት የእኛን የግል ወንድማማችነትን፣ የልብ ወንድማማችነትን የሚያሳድጉ ምርጫዎች ናቸው።

የመንፈሳዊ ወንድማማችነት ዘር ማደግ የሚጀምረው ከኛ ነው። በቤታችን፣ በሰፈራችን፣ በትምህርት ቤቶች፣ በስራ ቦታዎች፣ በህዝብ አደባባዮች እና በውሳኔ ሰጪ ተቋማት ውስጥ በግንኙነታችን ውስጥ በየቀኑ ትንሽ ዘር መትከል በቂ ነው።

እንዲሁም ለሁሉም እኩል ክብርን የሚያውቅ፣ ጓደኝነትን እና አባልነትን የሚያጎለብት፣ ትምህርትን፣ እኩል እድልን፣ ጨዋ ሥራን እና ማህበራዊ ፍትህን፣ እንግዳ ተቀባይነትን፣ አብሮነትን እና ትብብርን የሚያበረታታ፣ ማህበራዊ አብሮነት ኢኮኖሚ እና ፍትሃዊ የስነ-ምህዳር ሽግግር፣ ዘላቂ ግብርና የሚረጋገጥበት ማህበራዊ ወንድማማችነት እንዲፈጠር እንሰራለን። ለሁሉም ሰው የሚሆን ምግብ ማግኘት፣ በዚህም እርስ በርስ በመከባበር እና የሁሉንም ደህንነት በመጠበቅ ላይ የተመሰረተ ተስማሚ ግንኙነቶችን እንደግፋለን።

በዚህ አተያይ የቀረቤታ ድርጊቶችን እና የሰውን ሕጎች ማዳበር ይቻላል፣ ምክንያቱም "ወንድማማችነት የግድ ትልቅ ነገርን ይጠይቃል፣ ይህ ደግሞ ነፃነትን እና እኩልነትን ይጨምራል" (FT, n. 103)።

"ሁሉም ነገር ከሌላው ነገር ጋር የተያያዘ ነው" የሚለውን በማወቅ ከተፈጥሮ ጋር ሰላም ለመፍጠር ፣የአለም እጣ ፈንታ ፣የፍጥረት እንክብካቤ ፣የተፈጥሮ ስምምነት እና ዘላቂ የአኗኗር ዘይቤዎች በጋራ በመሆን የአካባቢ ወንድማማችነትን መገንባት እንፈልጋለን። የዘላለም ሕይወት መዝሙር በሆነው በቅዱስ ፍራንችስኮስ የፍጡራን መጽሃፍ ማስታወሻዎች ላይ የወደፊቱን መገንባት እንፈልጋለን። ሁሉም ነገር የተሰላሰለ ነው ፣ እናም ከሁሉም እና ሁሉም ሰው ጋር የተዛመደ ሕይወት ነው የሚለውን የአጽናፈ ዓለማዊ ወንድማማችነት የመዝሙር ጥቅሶች ክብር ይለብሳሉ።

ስለዚህ እኛ በሰብአዊ ወንድማማችነት ላይ የመጀመሪያውን ዓለም አቀፋዊ ስብሰባ ምክንያት በማድረግ የተሰበሰቡት ሴቶች እና በጎ ፈቃድ ያላቸው ወንዶች ሁሉ የወንድማማችነትን ጥሪ እንዲቀበሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን ። የልጆቻችን የወደፊት ህይወታቸው የሚያብበው ሰላም፣ ፍትህ እና እኩልነት በሰፈነበት አለም ውስጥ ብቻ ሲሆን ለአንድ ነጠላ የሰው ቤተሰብ ጥቅም፡ ወንድማማችነት ብቻ የሰው ልጅን ማፍራት ይችላል።

ወንድማማችነትን መሻትና በጋራ በአንድነት መገንባት የኛ ነፃነት ነው። ይህንን ህልም ለመቀበል እና ወደ እለታዊ ተግባራት ለመቀየር ይህንን መግለጫ በመፈረም ይቀላቀሉን፥ ይህም የሁሉንም መሪዎች አእምሮ እና ልብ ይነካ ዘንድ እና በየደረጃው ትንሽም ይሁን ትልቅ የዜግነት ሃላፊነት አለባቸው።

 

12 June 2023, 15:30