ፈልግ

TURKEY-SYRIA-QUAKE

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ሰብአዊ ክንድ ላደረጉት እርዳታ አመስግነዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የቅድስት መንበር የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት የእርዳታ ስጪ ተቋማት ጦርነት እና የተፍጥሮ አደጋዎች እየተደቀነባቸው ባሉት ዩክሬን፣ ቱርክ እና ሶርያ፣ ቅድስት ሀገር እና በመላው አሀገራት ያሉትን ስቃይ ለመቅረፍ ላደረገው ትብብር እና ልግስና ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሐሙስ ሰኔ 15/2015 በቫቲካን የROACO (በጣሊያነኛ ቋንቋ Riunione Opere Aiuto Chiese Orientali በአማርኛው የምስራቃዊ አብያተ ክርስቲያናት የእርዳታ ስራዎች ሕብረት) አባላት ባደረጉት ንግግር “የምስራቃውያን አብያተ ክርስቲያናት የእርዳታ ኤጀንሲዎች ውህደት” እና የወጣቶች ኮንፈረንስ ተወካዮች ምልአተ ጉባኤያቸውን በሮም እያካሄዱ ባለው ጉብኝት ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው በሚሰቃዩ ሰዎች ፊት ቁስሎችን በመንከባከብ ለሚረዳው ንቁ አጋርነት ያመስገኑ ሲሆን በግጭት ውዥንብር ውስጥ ተስፋን የሚመልስ እንክብካቤ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው በንግግራቸው ገልጿል።

የተቸገሩትን የዕለት ተዕለት ስቃይ መዋጋት

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ ‹‹የተስፋ ዘር ለማብቀል በደረቃማው ምድር ላይ ተጠምዳችኋል፤›› ያሉት ሲሆን ‹‹በቀናት መካከል በቱርክና በሶሪያ የተከሰተውን የመሬት መንቀጥቀጥ ቁስሎች ለማዳን በቅርቡ ያደረጋችሁትን ጥረት እያሰብኩ ነው። የተጨቆኑ ህዝቦች ስቃይ" ለመቀነስ እየሰራችሁ ነው ብሏል።

"እነሱን መርዳታችንን እንደምንቀጥል ተስፋ አደርጋለሁ፤ ብዙ ተስፋዎች ተሰጥተዋል፣ ነገር ግን አሁንም መደበኛ የባንክ ስርዓቶችን በመጠቀም ለተጎጂዎች እርዳታ ለመላክ አስቸጋሪ ነው" ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግሯል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በዩክሬን በአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን እና ስደተኞችን ለመደገፍ ላደረጉት ታላቅ ጥረት አመስግነዋል። "ከጥቂት አመታት በፊት፣ ያንን ተወዳጅ ሀገር በመወከል የራሴን ጥረት "ከጳጳሱ ለዩክሬን" በተሰኘው ተነሳሽነት እና በኋላም ከሌሎች ቀጣይ ፕሮጀክቶች ጋር አንድ ለማድረግ ፈልጌ ነበር ብሏል።

"ነገር ግን እኔ ደግሞ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ሁሉንም ለማሳሰብ እፈልጋለሁ "እርሱም  የተጨባጭ መቀራረብ፣ የጸሎት እና የበጎ አድራጎት ቅርበት፣ በጦርነት ለተጎዳው የዩክሬን ሕዝብ የተቻለንን ማድረግ" ይኖርብናል ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለቅድስት ሀገር እና ለመካከለኛው ምስራቅ ያላቸውን ትኩረት ጠቁመው የ ROACO ኢራን ፣ ቱርክ እና ኤርትራ የእርዳታ ፕሮጀክቶችን አጉልተው ተናግረዋል ። "እግዚአብሔር ለእነዚያ ውብ አገሮች የሰጣቸው ግዙፍ የሰውና የተፈጥሮ ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ ውሎ ለነዋሪዎቻቸው የተወሰነ ሰላም ያጎናጽፋቸው ዘንድ ምኞቴ ነው” ብሏል።

በእግዚአብሔር እቅፍ የበራ

በአሁኑ ጊዜ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የእግዚአብሔር የሰላም ዕቅድ ፈርሷል። መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ስላዘጋጀው የሰላም ዕቅድ ሲናገር “ከመጀመሪያ ጀምሮ በወንድማማቾች መካከል በቃየንና በአቤል መካከል ግፍና ንጹሑን መገደል ያሳየናል” ብሏል።

“በተለይ ለእኛ ለክርስቲያኖች ቅዱሱን ቃል በቅን ልብ ማዳመጥ እና በራሳችን እቅድ ሳይሆን በእግዚአብሔር መሐሪ እቅድ እንድንበራ እና እንድንመራ መፍቀድ ምንኛ መልካም ነው” ብለዋል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ። ሁሉንም ወንዶች እና ሴቶች፣ ሁሉንም የኢየሱስ ወንድሞች እና እህቶች ማቀፍ እና ማዳን ያስፈልጋል!" ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ይህ ስብሰባ ከምሥራቃዊ አብያተ ክርስቲያናት ወጣቶች በሚጠበቀው ነገር ላይ ያተኮረ መሆኑን አመስግነው ሁሉም ሰው ፍላጎቶቹን ፣ የተናገሩትን እና “በልባቸው የተሸከሙትን” በአንድነት እንዲያዳምጡ ጥሪ አቅርበዋል ። ወጣቶች "የጋራ ጥቅም ዋና ተዋናዮች መሆን ይፈልጋሉ ይህም የማህበራዊ ድርጊት አቅጣጫ ጦቋሚ "ኮምፓስ" መሆን አለበት ብለዋል።

“እዚህ የተገኛችሁ ውድ ወጣቶች፣ የምትኖሩት የጋራ ጥቅምን መልሶ ማቋቋም ለህልውና አስፈላጊ በሆነባቸው ክልሎች ውስጥ ነው። እናንተ ለሁሉ የሰላም ወኪሎች ሁኑ፣ ዓለም ልዩነቶችን ባከበረ መልኩ አንድ ሆና ትቀጥል ዘንድ የሚያደርግ ነቢያት ሁኑ፥ ለአለም መልካም የሰላም አዋጅ አውጁ” ብሏል።  

ከኢየሱስ ጋር ዘላቂ ወዳጅነት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከእርሳቸው በፊት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት በነዲክቶስ 16ኛ በላቲን ቋንቋ “Ecclesia in Medio Oriente” (በመካከለኛው ምስራቅ የምትገኘው ቤተክርስቲያን) በተሰኘው ሐዋርያዊ ማሳሰቢያ ላይ ወጣቶች “በጸሎት ኃይል ከኢየሱስ ጋር እውነተኛና ዘላቂ ወዳጅነት እንዲመሠርቱ” እንዳበረታቱ አስታውሰዋል።

ለክርስቲያኖች፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንዳሉት ከሆነ ይህ ዋነኛው የተግባር ምንጭ ነው ብለዋል።

"የተወጋው የእግዚአብሔር ልብ የበጎ አድራጎት ሥራን እንደ ሙያ ከማሰብ ነፃ ያደርገናል፣ የበለጸገ የበጎ አድራጎት ስሌት የመልካምነት ቢሮክራሲ ወይም ይባስ ብሎ የፖለቲካ ፍላጎቶችን መረብን እንዳናስብ ነው ጸሎት የሚያስፈልገን" ብሏል።

“ለክርስቲያኖች በተለይም ለወጣቶች የሚሹት እውነተኛነት፣ የመመስከር ድፍረትን፣ ጥንካሬን የሚሰጥ፣ በሰው ልጆች ስቃይ ውስጥ የእግዚአብሔር የመጨረሻ ተሳትፎ የሆነው መስቀል ነው” ብለዋል ቅዱስ አባታችን። ዛሬ ሁሉም የቁጣ ምንጭ የሆኑትን ግለሰባዊነትን እና ግዴለሽነትን ማሸነፍ እና ርህራሄን እንዲጨምር የምናደርገው በእዚሁ መልኩ ነው ብሏል።

ቀጣይነት ያለው ርህራሄ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቀጣይነት ያለው ርኅራኄ እንዲጠበቅ ጥሪ አቅርበዋል፥ ይህ "የእምነታችን እምብርት ነው፥ ምክንያቱም በሰው ልጆች ስቃይ ውስጥ ሙሉ በሙሉ የሚሳተፍ የእግዚአብሔር ፍቅር ስለሚያሳየን ነው" ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለአገልግሎታቸው ያላቸውን ምስጋና በማደስ እና በእነርሱ እና በስራቸው ላይ በረከታቸውን በማሳየት ንግግራቸውን አጠቃለዋል።

የረድኤት ኤጀንሲዎች ወደ በምስራቃዊ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ መገኘታቸው (ROACO፡ Riunione Opere Aiuto Chiese Orientali) ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ የገንዘብ እርዳታ ኤጀንሲዎችን በማዋሃድ በሮም የሚገኙ የካቶሊክ ምሥራቃውያን ቀሳውስትን እና አማኞችን በሮም እና በተለያዩ የትውልድ አገሮቻቸው አቅፎ የያዘ ተቋም ነው። ሃያ ሦስቱ የምስራቃውያን (ወይም ምስራቃዊ) ልዩ አብያተ ክርስቲያናት ራሳቸውን የሚያስተዳድሩ ቢሆኑም ሁሉም ከሮም ጋር ሙሉ በሙሉ ግንኙነት አላቸው፣ እናም ሁሉም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አካል ናቸው። በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ቤተ ክርስቲያን ባስተማረችው ትምህርት መሠረት፣ ሁሉም ልዩ አብያተ ክርስቲያናት፣ ምሥራቅም ሆነ ምዕራብ፣ “አንዱም ከሌሎቹ እንዳይበልጥ፣ ሁሉም እኩል ክብር አላቸው” ሲል መደንገጉ ይታወሳል።

23 June 2023, 15:10