ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአውሮፓ ፓርላማ የአውሮፓ ሕዝቦች ፓርቲ (EPP) ቡድን አባላት ጋር እ.አ.አ 2018 በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአውሮፓ ፓርላማ የአውሮፓ ሕዝቦች ፓርቲ (EPP) ቡድን አባላት ጋር እ.አ.አ 2018 በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት   (Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፡ ታላቁ የወንድማማችነት ህልም መልካም የፖለቲካ መንፈስ ያነሳሳ ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአውሮፓ ፓርላማ የአውሮፓ ሕዝቦች ፓርቲ (EPP) ቡድን ፕሬዝዳንት የክርስቲያን ፖለቲከኞችን ኃላፊነት እንዲገነዘቡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል “ታላቁን የወንድማማችነት ህልም ወደ ተጨባጭ የመልካም ፖለቲካ ተግባር በየደረጃው መተርጎም" አለበት ሲሉ ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው አክለው ገለጸዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአውሮፓ ፓርላማ ውስጥ ለአውሮፓ ህዝቦች ፓርቲ (EPP) ቡድን ፕሬዝዳንት ማንፍሬድ ዌበር መልእክት አስተላልፈዋል ። ጽሑፉ ከአውሮፓ ህዝቦች ፓርቲ ፓርላማ አባላት ጋር ለመገናኘት ቀደም ሲል ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ሲሆን ነገር ግን ጳጳሱ ሆስፒታል በመግባታቸው ምክንያት ቀጥሮው በሰኔ 02/2015 ቀን ተሰርዞ ነበር።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመልእክታቸው በርካታ ነጥቦችን አንስተዋል፤ ከእነዚህም መካከል የክርስቲያን ፖለቲከኞች ኃላፊነት፣ የቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ የበለጸጉ ቅርሶች እንደ አጋዥ መመሪያ፣ አውሮፓን አንድነትና የባህል ብዝሃነትን ማስተሳሰር፣ እና ለእያንዳንዱ ሰው የወንድማማችነት እና የመከባበር ህልም ወደ ተጨባጭ እውነታ የሚያመጣ በፖለቲካ ውስጥ የላቀ ራዕይ ያስፈልጋል የሚሉ ጭብጦች በመልእክቱ ውስጥ ተካተዋል።

በዜጎች እና በተቋማት መካከል ያለውን ልዩነት በማጥበብ

እ.ኤ.አ. በህዳር 2014 በአውሮፓ ፓርላማ ያደረጉትን ጉብኝት በማስታወስ በአውሮፓ ፓርላማ ውስጥ የተራ ሰዎች ፍላጎት እየቀነሰ መምጣቱን ከተቋሙ አባላት የመጀመሪያ ምርጫዎች ጋር ሲነፃፀር እየቀነሰ መምጣቱን ተመልክተዋል ። በዜጎች እና በፓርላማ አባላት መካከል ያለው ግንኙነት እጅግ እየሰፋ መምጣቱንም በወቅቱ ቅዱስነታቸው መናገራቸውን አስታውሰዋል። ይህንን በተመለከተ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብሏል...

“ይህ የተለመደ የዴሞክራሲ ችግር ነው። ግንኙነቱን በእያንዳንዱ ሀገር ውስጥ ለማቆየት ቀድሞውንም አስቸጋሪ ከሆነ ለአውሮፓ ፓርላማ የበለጠ 'ሩቅ' ነው። በተመሳሳይም በዛሬው ጊዜ መግባባት እነዚህን ርቀቶች ለማሸነፍ ትልቅ እገዛ ያደርጋል”።

ቀጣይ ጥናት

ሁለተኛው ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ የብዝሃነት ጉዳይ ነው ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመልእክታቸው ያብራሩ ሲሆን ይህ ደግሞ በአንድ ትልቅ የፓርላማ ቡድን ውስጥ የሚጠበቅ ቢሆንም፣ አንድነትን የሚጠይቁ አንዳንድ መርሆዎች እና የሥነ ምግባር እሴቶች አሉ። በአባላቱ ላይ ጥናትና አስተያየት ማሳደግ በዚህ ረገድ ያግዛል ብለዋል። ይህንን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለውን ብሏል ...

እውቀትን ለማጥለቅ እና ከሥነ ምግባር ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት የጥናት እና የማሰላሰል ጊዜዎች መኖራቸው የተለመደ ነው። ይህ ከምንም በላይ በሕሊና ደረጃ የሚጫወት፣ በፖለቲካ ውስጥ የተሰማሩትንም ባሕርያት የሚያጎላ አስደሳች ፈተና ነው። ክርስቲያን ፖለቲከኛ ሊለዩት የሚገባው ጉዳዮች በሚገጥሙት አሳሳቢነት፣ ምቹ መፍትሄዎችን በመተው እና ሁልጊዜም የሰውን እና የጋራ ጥቅምን ክብር በሚወስኑ መስፈርቶች አጥብቀው በመያዝ ነው።

የቤተክርስቲያን ማህበራዊ አስተምህሮ ጠቃሚ ማጣቀሻ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የፓርላማ አባላትን "በጣም የበለጸገ ቅርስ" የቤተክርስቲያኗን የማህበራዊ አስተምህሮ እንዲወስዱ አበረታቷቸዋል፣ ምክንያቱም ሁለቱን የአብሮነት እና የበጎ አድራጎት መርሆዎች ለአውሮፓ ፖለቲካ ልዩ አስተዋፅዖ ለማድረግ የሚረዱ ሀሳቦችን ያጎላል ሲሉ ተናግሯል።

ለአውሮፓ መነሳሳት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመልእክታቸው "አንድነት እና ልዩነትን ያቀፈ የአውሮፓን ራዕይ ማሳደግ ቁልፍ ነው" ብለዋል። ይህ እጅግ የበለጸገ ልዩ ልዩ ቀለማትን ያቀፈ የሰዎችን የተለያዩ ባህሎች እና መለያዎች በተቋሙ እና በተነሳሽነቱ ውስጥ የሚንፀባረቅ ራዕይን ያካትታል ሲሉ በመልእክታቸው ገለጿል። ይህንን በተመለከተ ቅዱስነታቸው ሲናገሩ የሚከተለውን ብሏል ...

“ለዚህም ጠንካራ መነሳሻን፣ ‘ነፍስ’ ይፈልጋል። እናም 'ህልሞች' ያስፈልጋሉ  ማለት እወዳለሁ። የ 21 ኛው ክፍለ ዘመን ታላቅ ዓለም አቀፋዊ ፈተናዎችን የተጋፈጠች አውሮፓን ለማስቀጠል ከፍተኛ እሴቶችን እና ከፍተኛ የፖለቲካ እይታን ይጠይቃል”።

ወንድማማችነት በተጨባጭ ድርጊቶች ይገለጻል

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱም ሀሳባቸውን ወደ አውሮፓ አንድነት መስራች አባቶች ትሩፋት እና ብሄራዊ ጥቅምን ብቻ ከሚመለከት የፖለቲካ ድርጅት ሃሳብ አልፈው ሁሉም "ወንድማማችነት" የሚኖሩበት ማህበረሰቦችን የመገንባት ዓላማ ወደሚለው ጥሪ አዙረዋል። እናም ትክክለኛ ሕይወት ከዚህ አንፃር፣ ወንድማማችነት፣ ከመላው ቤተ ክርስቲያን እና መልካም ፈቃድ ካላቸው ሰዎች ጋር የሚጋራው ታላቁ “ሕልም” ዓለም አቀፋዊ አመለካከትን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለአውሮፓ አዲስ መነሳሳትን ለመፍጠር “የመነሳሳት ምንጭ” ሊሆን እንደሚችል ጳጳሱ አስረድተዋል። ይህንን በተመለከተ ቅዱስነታቸው ሲናገሩ የሚከተለውን ብሏል ...

“በአሁኑ ጊዜ ክርስቲያን ፖለቲከኞች የወንድማማችነትን ታላቅ ህልም በየደረጃው በሚገኙ ተጨባጭ የመልካም ፖለቲካ ተግባራት ማለትም በአገር ውስጥ፣ በብሔራዊ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በመተርጎም ችሎታቸው መታወቅ አለባቸው ብዬ አምናለሁ። ለምሳሌ፡ እንደ ስደት፣ ወይም ፕላኔቷን መንከባከብ የመሳሰሉ ተግዳሮቶች... ሊፈቱ የሚችሉት ከዚህ ታላቅ አነቃቂ መርህ፡ በሰብዓዊ ወንድማማችነት ብቻ ነው”።

የአለም እይታ ያለው አንድ አውሮፓ

በማጠቃለያውም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ባለፈው ምዕተ-ዓመት የተከሰቱትን ጦርነቶች ተከትሎ የተባበረ አውሮፓን ቀስ በቀስ የመገንባቱን አበረታች መርሆ አጽንኦት ሰጥተዋል። ነፃነትን፣ ፍትህን እና ሰላምን የማስፈን እና በልዩነት እርስበርስ የመከባበር ሀሳቦችን አስታውሰዋል። እናም እነዚህ መርሆዎች በግሎባላይዜሽን ዓለም ውስጥ እንዴት እንደሚሟገቱ፣ ነገር ግን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ለአውሮፓ እና ለመላው የሰው ልጅ ቤተሰብ የበለጠ ጠቃሚ ናቸው ያሉ ሲሆን እነዚህን እሴቶች የሚቋምጡ እና ህልማቸውን የሚያሟላ አውሮፓ እና አለም ለመፍጠር የሚፈልጉ ወጣቶችን እንዲያስታውሱ አበረታቷቸዋል።

12 June 2023, 10:48