ፈልግ

Pope Francis hospitalized at Rome's Gemelli hospital

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሆስፒታል ውስጥ ሆነው በጥሩ ሁኔታ እያገገሙ መሆናቸው ተገለጸ!

የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሆዳቸው ላይ የቀዶ ሕክምና ማድረጋቸውን የዘገበ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ቅዱስነታቸው በሮም ከተማ ውስጥ በሚገኘው ጂሜሊ በመባል በሚታወቀው የዩኒቬርሲቲ ሆስፒታል ውስጥ ሆነው በጥሩ ሁኔታ እያገገሙ መሆናቸውን ገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሰኔ 01/2015 ዓ.ም በተደረገላቸው የላፕራቶሚ ቀዶ ጥገና እና በሆድ ግድግዳ ላይ ከተደረገላቸው ሕክምና በኋላ ቅዱስነታቸው በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት ቅዳሜ ማለዳ ላይ ዜናውን ያሳወቀ ሲሆን፥ ተጨማሪ መረጃም በእየቀኑ ይፋ እንደሚያደርግ የገለጸ ሲሆን "የእርሳቸው የደም ግፊት መለኪያ የተለመደውን አካሄድ ያሳያል" በማለት ዶክተሮቹ መግለጻቸውን ይፋ ያደረገ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከሰዓት በኋላ ላይ በጸሎት ማሳለፋቸውን ገልጿል።

አርብ ማምሻውን የወጣው መግለጫም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ምዕመናን እና እንዲሁም ሌሎች ሰዎች በነዚህ ወቅት እያስተላለፏቸው ባሉት በርካታ መልእክቶች ልባቸውን ተነክተዋል፤ በተለይም አሁን በሆስፒታል ላሉ ህጻናት ሃሳባቸውን እና ምስጋናቸውን ለማቅረብ አስበዋል፤ ለተደረገላቸው ፍቅር እና እንክብካቤ ያመሰገኑ ሲሆን በሆስፒታሉ ውስጥ የሚገኙ ሕጻናት በስዕሎቻቸው እና በመልእክቶቻቸው ላደረሷቸው የመልካም ምኞት መልእክቶች ሁሉ አመስግነዋል።

በተጨማሪም ለህፃናቱ “እንዲሁም የህክምና ባለሙያዎች፣ ነርሶች፣ ማህበራዊና ጤና አጠባበቅ ሰራተኞች እና በየቀኑ የሰዎችን ህመም በእጃቸው ለሚነኩ ሸክሙን እያነሱ ለሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች እና ለመንፈሳዊ ረዳቶች” በቅርብ እና በሩቅ የሚገኙ ሰዎች እያደረጉላቸው ለሚገኘው ጸሎት ያላቸውን ምስጋና ገልጿል።

12 June 2023, 10:45