ፈልግ

PORTUGAL-RELIGION-CATHOLIC-WYD

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የዓለም የወጣቶች ቀን በጉጉት እየተጠባበቁ መሆናቸው ተገለጸ!

በፖርቹጋል ዋና ከተማ በሊዝበን የሚካሄደው የዓለም የወጣቶች ቀን እውን ሊሆን 40 ያህል ቀናት ቀርተውታል። በእዚህ የዓለም የወጣቶች ቀን ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በቅርቡ ቀዶ ጥገና ተደርጎላቸው ከሳምንት በኋላ አገግመው ከሆስፒታል መውጣታቸው የሚታወስ ሲሆን ከእዚያም በመቀጠል በድጋሚ ቅዱስንታቸው ባደረጉት የጤና ምርመራ ከ40 ቀናት በኋላ በሚከናወነው የዓለም የወጣቶች ቀን ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሐኪሞች ቡድን ማረጋገጫ ስለሰጣቸው መደሰታቸውን ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በፖርቱጋል የሚከበረው የዓለም ወጣቶች ቀን 40 ቀናት ሲቀሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሊዝበን ለሚገኙት ወጣቶች በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት “ዶክተሮች ወደ እዚያ መሄድ እንደምችል ነገሩኝ፣ በእዚህም እጅግ ተደስቻለሁ፣ በጉጉት በመጠባበቅ ላይ እገኛለሁ” በማለት መልእክት አስተላልፏል።

"አንዳንዶች በህመም ምክንያት መሄድ አልችልም ብለው ያስባሉ፣ ነገር ግን ሐኪሙ እንደምችል ነገረኝ ስለዚህ እኔ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ፣ ወጣቶች ኑ እንገናኝ!" በማለት ቅዱስነታቸው ተናግሯል።  

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከየአኅጉሩ የሚመጡ ወጣቶች እ.አ.አ ከነሐሴ 1 እስከ ነሐሴ 6 ባለው የዓለም ወጣቶች ቀን በሊዝበን ለሚሰበሰቡ ወጣቶች መልእክት አስተላልፈዋል። እናም በታላቁ ክስተት ላይ መገኘታቸውን ቅዱስነታቸው አረጋግጦጠዋል።

 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለጉዞው በመዘጋጀት የተጠመዱትን እና የዓለምን የወጣቶች ቀን ስብሰባን ከሩቅ ሆነው ለሚከታተሉት ወጣቶችን ሁሉ መልእክት አስተላልፏል። የዓለም ወጣቶች ቀን አዘጋጅ ኮሚቴ ሁለት ቪዲዮዎችን ለቋል፡ አንደኛው ለተሳታፊዎች የተላለፈ ሲሆን ሁለተኛው ኮሚቴውን ለማቋቋም ለወራት ሲሰሩ ለነበሩት፣ የእንኳን ደህና መጣችሁ እና ለመንፈሳዊ ነጋዲያን የሚሆን ማረፊያ በማዘጋጀት ላይ ለተጠመዱ ሰዎች ነው።

"ቀኑ ለሁሉም ሰው የሚስብ ነጥብ ነው። አሁን እኛ ልንመለከተው የሚገባን ነጥብ ነው፥ እናንተ ወጣቶች ልትመለከቱት ይገባል" ብሏል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "ወጣቶች ኑ!" ህይወትን በሃሳብ የሚቀንሱትን አትስሙ። እነዚያ የህይወት ደስታን እና የመገናኘትን ደስታ ያጡ ምስኪኖች። ጸልዩላቸው” ብሏል።

ሦስቱ ቋንቋዎች

ልክ እንደሌሎች ስብሰባዎች ከአዲሶቹ ትውልዶች ጋር፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ሲገናኙ ወጣቶቹ በጭንቅላት፣ በልብ እና በእጆች "በሶስቱ ቋንቋዎች" ወደ ህይወት እንዲቀርቡ በድጋሚ ጠይቋል፡ ጭንቅላት ምን እንደሚሰማን እና ስለምናደርገው ነገር በግልፅ እንድናስብ፤ ጥሩ ስሜት እንዲሰማን ልብ ደግሞ እኛ የምናስበው እና የምናደርገው እንዲሰማን እና የምናስበውን ለመረዳት ደግሞ እጆች ያስፈልጉናል ብሏል።

"ኑ ደስ ይበላችሁ በሊዝበን እንገናኝ!" ካሉ በኋላ የመጨረሻው ሰላምታ እና ብራኬ ሰጥተው ቅዱስነታቸው የቪዲዮ መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

23 June 2023, 15:13